የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ህይወት እና ጉዞ

በአዲስ አበባ የተፈጠረው ምቹ የኢንቨስትመንት ምኅዳር መዲናዋን የኢንዱስትሪ ማዕከል እያደረጋት ነው

Dec 3, 2025

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ ህዳር 23/2018(ኢዜአ)፦ በአዲስ አበባ በመፍጠርና በመፍጠን የተፈጠረው ምቹ የኢንቨስትመንት ምኅዳር መዲናዋን ተወዳዳሪና ተመራጭ የኢንዱስትሪ ማዕከል እያደረጋት መሆኑን ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ ጃንጥራር ዓባይ ገለጹ፡፡

የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ ጃንጥራር ዓባይ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የኢንዱስትሪ ምርታማነት ለፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገትና ለሥራ ዕድል ፈጠራ ወሳኝ ሚና አለው፡፡

ባለፉት የለውጥ ዓመታትም በመዲናዋ ምቹ የኢንቨስትመንት ከባቢ ለመፍጠር ስኬታማ የኢንዱስትሪ የኃይል አቅርቦትና ተያያዥ የመሠረተ ልማት ተግባራት መከናወናቸውን ገልጸዋል።

የመሠረተ ልማት መሟላት የኢንዱስትሪዎችን ምርታማነት በማሻሻል ከሀገር ውስጥ ገበያ ባለፈ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ የሚያደርጋቸውን አቅም እንዲገነቡ ማገዙን አብራርተዋል።

ይህም መዲናዋን የኢንቨስትመንት ዐይን ማረፊያ እያደረጋት መምጣቱን አንስተዋል።

በአምራች ኢንዱስትሪው የተፈጠረው የምርት ስብጥርና ጥራት አዲስ አበባ በሀገሪቱ የኢኮኖሚ ዕድገት የበኩሏን ድርሻ እንድትወጣ እያደረጋት መሆኑን ጠቅሰዋል።

የኢንዱስትሪዎቹን ተወዳዳሪነት ማጎልበት፣ የምርት ጥራትና ስብጥርን ማስጠበቅ እና ኢንቨስትመንትን ማበረታታት ከፍተኛ ትኩረት እንደተሰጠው አስረድተዋል።

በአዲስ አበባ ጥቃቅኖችን ሳይጨምር የኢንዱስትሪዎች ቁጥር ከ3ሺህ 800 በላይ መድረስ ለተመዘገበው ተጨባጭ ውጤት ማሳያ መሆኑን አስገንዝበዋል።

የኢትዮጵያን የተሟላ ብልጽግና እውን ለማድረግ የመፍጠርና መፍጠን አቅጣጫ፣ የኢንዱስትሪ የግብዓት አቅርቦት፣ የገበያ ትስስር፣ የድጋፍና ክትትል ተግባራት በስፋት እየተከናወኑ መሆኑን አስታውቀዋል።

በመዲናዋ በእንጨት፣ ብረታብረት፣ አልባሳት እና የምግብ ማቀነባበር ዘርፍ የተሰማሩ አምራቾች ሀገር አቀፍ የተኪ ምርት ንቅናቄን በመደገፍ ወሳኝ ሚና እየተወጡ እንደሚገኙ ገልጸዋል።

የዜጎች በሀገር ምርት የመጠቀም ባህል እያደገ መምጣት የአምራች ኢንዱስትሪዎችን ምርታማነት ለማስፋት አቅም መፍጠራቸውን አብራርተዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መጥቷል

ጋምቤላ፤ ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መምጣቱን የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት...

Sep 4, 2026

በክልሉ ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት ተኪ ምርቶችን የማምረት ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል -ርዕሰ መስተዳድር አሻደሊ ሀሰን

አሶሳ፤ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ)፡- በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት ተኪ ምርቶችን የማምረት ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የክልሉ ርዕሰ ...

Sep 3, 2026

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሥራ ዕድል ፈጠራ በተከናወኑ ሥራዎች ውጤት ተገኝቷል

ሆሳዕና፤ ነሀሴ 5/2018 (ኢዜአ)፡-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ዜጎችን በሥራ ዕድል ተጠቃሚ ለማድረግ በተከናወኑ ሥራዎች ውጤት መመዝገ...

Aug 12, 2026

በሙስናና ሕገ ወጥ ድርጊት የተሰማሩ አካላትን ተጠያቂ የማድረግ ርምጃ ቀጣይነት ሊኖረው ይገባል

አዲስ አበባ፤ነሐሴ 5/2018 (ኢዜአ)፦የመንግሥት በሙስናና ሕገ ወጥ ድርጊት የተሰማሩ አካላትን በሕግ ተጠያቂ የማድረግ ርምጃ ቀጣይነት ሊኖረው እንደሚገባ ኢዜአ...

Aug 12, 2026