🔇Unmute
ከሚሴ፤ ሕዳር 23/2018(ኢዜአ)፡-በሀገሪቱ ከተሞች መሰረተ ልማትን በማሟላት ለነዋሪዎች እና ለኢንቨስትመንት ምቹ የማድረጉ ተግባር ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ ገለጹ።
ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ እና ሌሎች የፌዴራል ከፍተኛ አመራሮች በአማራ ክልል ኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ከሚሴና ጨፋ ሮቢት ከተሞች የልማት ሥራ እንቅስቃሴዎችን ዛሬ ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።

በጉብኝቱ ወቅት ሚኒሰትሯ እንዳመለከቱት፤ በከተሞች የኮሪደር ልማትን ጨምሮ የተለያዩ የመሰረት ልማት ግንባታዎች በመካሄድ ላይ ይገኛሉ።
በሀገሪቱ ከተሞች መሰረተ ልማትን በማስፋፋት ለነዋሪዎች እና ለኢንቨስትመንት ምቹ የማድረጉ ተግባር ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
በኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን የተጀመሩ የልማት ስራዎች አበረታች መሆናቸውንና ይበልጥ ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸውም ምክረ ሀሳብ አቅርበዋል።
የኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አህመድ አሊ በበኩላቸው ፣ በዞኑ ሰው ተኮር ፕሮጀክቶች እየተከናወኑ ነው ብለዋል።
በዞኑ ከተሞችም መሰረተ ልማትን በማሟላት ለነዋሪዎች፣ ለኢንቨስትመንትና ለቱሪዝም ምቹ ለማድረግ ስራው ተጠናክሮ ቀጥሏል ብለዋል።
በጉብኝቱም የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ፣ የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና ሌሎችም ከፍተኛ አመራሮች ተሳትፈዋል።
ጋምቤላ፤ ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መምጣቱን የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት...
Sep 4, 2026
አሶሳ፤ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ)፡- በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት ተኪ ምርቶችን የማምረት ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የክልሉ ርዕሰ ...
Sep 3, 2026
ሆሳዕና፤ ነሀሴ 5/2018 (ኢዜአ)፡-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ዜጎችን በሥራ ዕድል ተጠቃሚ ለማድረግ በተከናወኑ ሥራዎች ውጤት መመዝገ...
Aug 12, 2026
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 5/2018 (ኢዜአ)፦የመንግሥት በሙስናና ሕገ ወጥ ድርጊት የተሰማሩ አካላትን በሕግ ተጠያቂ የማድረግ ርምጃ ቀጣይነት ሊኖረው እንደሚገባ ኢዜአ...
Aug 12, 2026