🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ ህዳር 27/2018(ኢዜአ)፦ በአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና ሴቶችን የሥራ ዕድል ተጠቃሚ ለማድረግ የተጀመሩ ሥራዎች ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ የልደታ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ፡፡
በህዝባዊ ውይይቱ በአዲስ አበባ ከተማ ደረጃ በሁሉም ክፍለ ከተሞች ህዝባዊ ውይይት የተካሄደ ሲሆን፤ በልደታ ክፍለ ከተማም የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ(ዶ/ር)፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ(ዶ/ር) እና የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዘላለም ሙላቱ(ዶ/ር) ተገኝተዋል፡፡

በህዝባዊ የውይይት መድረኩ ከሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች የተውጣጡ የክፍለ ከተማዋ ነዋሪዎች ተሳትፈዋል፡፡
ነዋሪዎቹ ከመንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር ባደረጉት ውይይት እንደ ሀገርም ሆነ በከተማዋ የተሰሩ የልማት ሥራዎች የነዋሪዎችን ተጠቃሚነት እያረጋገጡ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በከተማዋ በመንግስትና በህዝብ ትብብር የተሰሩ የልማት ስራዎች የከተማዋን ገጽታ የቀየሩ የነዋሪዎችን ተጠቃሚነት እያረጋገጡ ያሉ መሆናቸውንም እንዲሁ፡፡
ላለፉት 30 አመታት ኢትዮጵያ ያጣችውን የባህር በር ለማስመለስ የተጀመረው ጥያቄና ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ እየተደረገ ያለው የሰላም ስምምነት ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባም ነዋሪዎቹ አንስተዋል።
መንግስት የጀመራቸው የለውጥ ስራዎች በተጠናከረ መልኩ ሊቀጥሉ እንደሚገባ ጠቁመው ስራዎቹ የስራ እድል ፈጠራ፣ የጤና አገልግሎትና የኮሪደር ልማት ተደራሽነት በቀጣይ ትኩረት ሊሰጣቸው እንደሚገባ ጠቁመዋል።
ውይይቱን የመሩት የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ(ዶ/ር) በሰጡት ማብራሪያ በሁሉም ዘርፍ የተገኙ ውጤቶችን ለማስቀጠል መንግስት ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ ገልጸው በጋራ ከቆምን በርካታ ሀገራዊ ፕሮጀክቶችን ማሳካት አንችላለን ብለዋል፡፡
ሌላው የውይይቱ መሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጌዲዮን ጢሞቲዎስ(ዶ/ር) በበኩላቸው፤ እንደ ሀገር ብሎም እንደ አዲስ አበባ ከተማ የተገኙ ስኬቶች በህዝብ አብሮነት እና ተሳትፎ የተመዘገቡ መሆናቸውን ተናግረዋል።
የበለጸገች ኢትዮጵያን እውን ለማድርግ መተባበር እና አብሮ መቆም እንደሚያስፈልግም ሚኒስትሩ ገልጸዋል።
የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዘላለም ሙላቱ(ዶ/ር) እንደገለጹት፤ ህዝባዊ የውይይት መድረኩ ከዚህ በፊት በተካሄዱ የህዝብ መድረኮች ለተነሱ ጥያቄዎች የተሰጡ ምላሾችና የወደፊት አቅጣጫዎችም የተመላከቱበት ነው።
አዲስ አበባ ፤የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት ተገልጋዮች ፋይዳ መታወቂያን ተጠቅመው በዲጂታል አማራጭ ትኬት የሚቆርጡበት አሰራር ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 03/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን የለማ የትራንስፖርት ኦፕሬተሮችንና የጭነት ባለቤቶችን የሚገናኝ መተግበሪያ አስጀምሯል። ...
Feb 12, 2025