🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ ሕዳር 30/2018(ኢዜአ)፡- የአሶሳ ግብርና ምርምር ማዕከል ምርታማነታቸው በምርምር የተረጋገጡ የማሽላ እና አኩሪ አተር ዝርያዎችን እያስተዋወቀ ነው።
በማዕከሉ በምርምር የተሻሻሉ የማሽላ እና የአኩሪ አተር ሰብሎች በማዕከሉና በአርሶ አደር ማሳ በኩታ ገጠም በማልማት የማስተዋወቅ ሥራ እየተከናወነ መሆኑን የማዕከሉ ዳይሬክተር ደስታ በቀለ ለኢዜአ ተናግረዋል።
በዚህም መሠረት በምርምር ማዕከሉ በ81 ሔክታር ላይ በኩታ ገጠም ማሽላ እየለማ መሆኑን ጠቁመዋል።
እነዚህ በምርምር የተሻሻሉት ‘አሶሳ አንድ’ እና ‘አሶሳ ሁለት’ የተሰኙ የማሽላ ዝርያዎች በአርሶ አደር ማሳ ላይ በሔክታር እስከ 35 ኩንታል ምርት እንደሚሰጡ ጠቁመዋል።
በሌላ በኩል በአሶሳ ዞን በተለያዩ ወረዳዎች በ32 ሔክታር ላይ በኩታ ገጠም የለማ የአኩሪ አተር ሰብልን ለአርሶ አደሩ እየተዋወቀ ነው ብለዋል።
እስካሁን ጥቅም ላይ እየዋለ ያለውን የግሻማ አኩሪ አተር ዝርያ የሚተኩ ‘አንድነት’ እና ‘ጣና በለስ’ የተሰኙ ዝርያዎችን በዚህ ዓመት በማልማት ለአርሶ አደሩ የማስተዋወቅ ሥራ እየተከናወነ እንደሚገኝ አመላክተዋል።
እነዚህ የአኩሪ አተር ዝርያዎች መካከለኛ መድረሻ ጊዜ ያላቸው፣ ምርታማነታቸው የተረጋገጠ፣ ከ700 እስከ 1 ሺህ 860 ሜትር ከባሕር ጠለል በላይ የሚላመዱና በሽታን የመቋቋም ዐቅማቸውም ከፍተኛ መሆኑን አብራርተዋል።
88 በማሽላ እንዲሁም 76 አርሶ አደሮች በአኩሪ አተር ዝርያ ማልማትና ማስተዋወቅ ሥራው ላይ ተሳታፊ መሆናቸውን ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።
በአጠቃላይ ማዕከሉ በተለያዩ ሰብሎችና እንስሳት ዘርፎች ቴክኖሎጂዎችን የማስተዋወቅ ሥራዎች በተለያዩ ወረዳዎች እያከናወነ እንደሚገኝም አስታውቀዋል።
አምቦ፤ ሰኔ 6/2018(ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ሸዋ ዞን ባለፉት ዓመታት በተከናወኑ የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ስራዎች ለንብ ማነብ ምቹ ሁኔታ በመፍጠሩ...
Jun 14, 2026
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 3/2018(ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል የበጋ መስኖ ልማት በምግብ ራስን ከመቻል ባለፈ የአርስ አደሩን ተጠቃሚነት እያሳደገ መሆኑን የክልሉ ምክት...
Jun 11, 2026
ሐረማያ፤ ግንቦት 20/2018 (ኢዜአ)፦ ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት የሚያሳድጉ የምርምር ቴክኖሎጂዎችን እያጎለበተ እንደሚገኝ አስታወቀ። ዩኒቨ...
Jun 1, 2026
ሆሳዕና፣ግንቦት 17/2018 (ኢዜአ)፦በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት የሚያሳድጉ የሕብረት ሥራ ማህበራትን ደግፎ የማብቃት ሥራው ተጠናክሮ እ...
May 26, 2026