የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ህይወት እና ጉዞ

ግብጽ በዓባይ ወንዝ ላይ የምታራምደው የቅኝ ግዛት ትርክት አክትሟል - ቢቂላ ሁሪሳ(ዶ/ር)

Dec 11, 2025

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 2/2018(ኢዜአ)፦ ግብጽ በዓባይ ወንዝ ላይ የምታራምደው የቅኝ ግዛት ትርክት አክትሟል ሲሉ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማዕከል አስተባባሪ ሚኒስትር ቢቂላ ሁሪሳ(ዶ/ር) ገለጹ።

በቅኝ ግዛት ዘመን አስተሳሰብ ጥቅምን ማረጋገጥ እንደማይቻልም ነው ቢቂላ ሁሪሳ(ዶ/ር) የተናገሩት።

በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማዕከል አስተባባሪ ሚኒስትር ቢቂላ ሁሪሳ(ዶ/ር) ከፐልስ ኦፍ አፍሪካ ሚዲያ ጋር ባደረጉት ቆይታ የግብጹ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መሐመድ አብደላቲ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን በተመለከተ የሰጡትን አስተያየት በጽኑ አውግዘዋል።

ግብጽ ሰላም እና መረጋጋትን አደጋ ላይ ከሚጥሉ አፍራሽ ንግግሮች እና ድርጊቶች መቆጠብ እንደሚገባት ቢቂላ ሁሪሳ(ዶ/ር) ጠቁመዋል።

በተጨማሪም ግብጽ በዓባይ ወንዝ ላይ የምታራምደው የቅኝ ግዛት ትርክት አክትሟል ሲሉም ነው የገለጹት።

የግብጽ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የኢትዮጵያ አቋም የተናጠል እርምጃ ነው ማለታቸው የዘመኑን እውነታ የማይመጥን የቅኝ ግዛት እሳቤ መሆኑን አመልክተዋል።

ሚኒስትሩ ግብጽ በናይል ወንዝ እኔ ብቻ የበላይነቱን ልውሰድ የሚል ጊዜ ያላፈበት ትርክት ተቀባይነት እንደሌለው ገልጸው መሰል እሳቤዎች ከሀገር ባለፈ ቀጣናዊ መረጋጋትን ስጋት ውስጥ የሚከቱ ናቸው ብለዋል።

አስተያየቱ የኢትዮጵያን ብሄራዊ ጥቅም የሚቃረን ተቀባይነት የሌለው ሀሳብ መሆኑንም አመልክተዋል።

ግብጽ ኢትዮጵያ እንዳትረጋጋ ተላላኪ ቡድኖችን በመመልመል እና በማሰማራት እየደገፈች መሆኑን ገልጸው ይህን አካሄድ ኃላፊነት የጎደለውና ጠብ አጫሪ ድርጊት ሲሉም ገልጸውታል።

ከውሃ መብቶች እና ቀጣናዊ ትብብር አንጻር ሀሳባቸውን ያነሱት ሚኒስትሩ የናይል ወንዝ አብዛኛው ድርሻ የምትወስደው ኢትዮጵያ ሀብቷን የመጠቀም ህጋዊ መብት እንዳላትም ተናግረዋል።

በሌላ በኩል የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ ሕጋዊና በመርህ ላይ የተመሰረተ መሆኑን ቢቂላ ሁሪሳ(ዶ/ር) አመልክተዋል።

ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ይህን የኢትዮጵያ መብት እውቅና እየሰጠው እንደሚገኝም ነው የተናገሩት።

ግብጽ በናይል ውሃ ላይ ብቻዬን ልጠቀም በሚል እያራመደች ያለችው አቋም ጊዜ ያለፈበትና የቅኝ ግዛት አስተሳሰብ መሆኑን ጠቁመው ወቅቱ ከሚጠይቀው አስተሳሰብ እና አካሄድ ጋር የማይሄድ ነው ብለዋል።

ግብጽ በዓባይ ወንዝ ላይ የምታራምደው የቅኝ ግዛት ትርክት አክትሟል ሲሉም ነው ያስገነዘቡት።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መጥቷል

ጋምቤላ፤ ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መምጣቱን የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት...

Sep 4, 2026

በክልሉ ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት ተኪ ምርቶችን የማምረት ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል -ርዕሰ መስተዳድር አሻደሊ ሀሰን

አሶሳ፤ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ)፡- በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት ተኪ ምርቶችን የማምረት ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የክልሉ ርዕሰ ...

Sep 3, 2026

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሥራ ዕድል ፈጠራ በተከናወኑ ሥራዎች ውጤት ተገኝቷል

ሆሳዕና፤ ነሀሴ 5/2018 (ኢዜአ)፡-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ዜጎችን በሥራ ዕድል ተጠቃሚ ለማድረግ በተከናወኑ ሥራዎች ውጤት መመዝገ...

Aug 12, 2026

በሙስናና ሕገ ወጥ ድርጊት የተሰማሩ አካላትን ተጠያቂ የማድረግ ርምጃ ቀጣይነት ሊኖረው ይገባል

አዲስ አበባ፤ነሐሴ 5/2018 (ኢዜአ)፦የመንግሥት በሙስናና ሕገ ወጥ ድርጊት የተሰማሩ አካላትን በሕግ ተጠያቂ የማድረግ ርምጃ ቀጣይነት ሊኖረው እንደሚገባ ኢዜአ...

Aug 12, 2026