🔇Unmute
ሠመራ፤ ታህሳስ 28/2018(ኢዜአ)፦ በሰመራ ሎጊያ ከተማ የበዓል ገበያ የእርድ እንስሳት አቅርቦቱ የተሻለ በመሆኑ በተመጣጣኝ ዋጋ እየሸመቱ እንደሚገኙ ሸማቾች ተናገሩ።
ለገና በዓል የእርድ እንስሳት አቅርቦትን በተመለከተ ኢዜአ ያነጋገራቸው የሰመራ ሎጊያ ከተማ ነዋሪዎች ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር የተሻለ አቅርቦት በመኖሩ በዓሉን ማክበር የሚያስችለንን የእርድ እንስሳት መግዛት ችለናል ብለዋል።

በከተማዋ በሚገኘው ገበያ ለእርድ የሚሆኑ ፍየሎችና በጎች በብዛት በማግኘታቸው አማርጠው መግዛት መቻላቸውን የተናገሩት አቶ ወንደሰን እምሩ ናቸው።
በዓሉን ማክበር የሚያስችሉ በተለይ ለእርድ የሚሆኑ ፍየሎችን በተሻለ አማራጭ ማግኘታቸውን ተናግረዋል።
በዚሁ ዕለት ለበዓል የሚሆን የእርድ እንስሳ የሸመቱት ሳሙኤል አየለ ከባለፈው ዓመት ብዙም ባልተራራቀ ዋጋ የሚፈልጉትን መግዛታቸውን ገልጸዋል።

በተለይ የፍየል ገበያው የተሻለ አቅርቦት ስላለው አማርጠው መግዛታቸውን ነው የተናገሩት።
ሌላኛዋ ሸማች ወይዘሮ ብዙአየሁ አወቀ በገበያው የፈለጉትን መሸመታቸውን ገልጸው፤ አቅርቦቱ የተሻለ መሆኑን ቁመዋል።
የሚያረቡትን ፍየሎች ለገበያ ይዘው የቀረቡት አሩሱ ዑመር በበኩላቸው ገበያው ከባለፈው ዓመት ጋር በዋጋ ረገድ ተመሳሳይነት ያለው መሆኑን ተናግረዋል።
ይዘው ገበያ የወጡትን ፍየሎች በተሻለ ዋጋ እየሸጡ መሆናቸውን ገልፀዋል።
ጋምቤላ፤ ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መምጣቱን የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት...
Sep 4, 2026
አሶሳ፤ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ)፡- በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት ተኪ ምርቶችን የማምረት ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የክልሉ ርዕሰ ...
Sep 3, 2026
ሆሳዕና፤ ነሀሴ 5/2018 (ኢዜአ)፡-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ዜጎችን በሥራ ዕድል ተጠቃሚ ለማድረግ በተከናወኑ ሥራዎች ውጤት መመዝገ...
Aug 12, 2026
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 5/2018 (ኢዜአ)፦የመንግሥት በሙስናና ሕገ ወጥ ድርጊት የተሰማሩ አካላትን በሕግ ተጠያቂ የማድረግ ርምጃ ቀጣይነት ሊኖረው እንደሚገባ ኢዜአ...
Aug 12, 2026