🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ ጥር 7/2018(ኢዜአ)፦ ባለፉት የለውጥ ዓመታት በገቢዎች ዘርፍ ተቋማዊ የማስፈጸም አቅም የማሳደግ፣ዘመናዊ የታክስ አስተዳደር ስርዓት የመገንባት፣ የታክስ ህግ ተገዢነትት የማረጋገጥ እና ዘላቂ የገቢ እድገትን የማረጋገጥ ስራዎች ተከናውነዋል ሲሉ የገቢዎች ሚኒስትር ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ ተናገሩ።
ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር በተገናኘ ዘመናዊ የግብር ስርዓትን ለመዘርጋት መሰራቱን ያስታወሱት ሚኒስትሯ በ2011 በኤሌክትሮኒክስ ዘዴ ታክስ በማሳወቅ ረገድ 10.1 % በመቶ ብቻ የነበረው አሰራር በ2017 ዓ.ም 94 በመቶ የሚሆኑ ግብር ከፋዮች ግብራቸውን በኢ-ፋይል ማሳወቃቸውን ተናግረዋል።
በተመሳሳይ በኤሌክትሮኒክስ ዘዴ ግብር የከፈሉ የግብር ከፋዮች በ2011 ከነበረበት ዝቅተኛ ደረጃ በ2017 ወደ 64 በመቶ ማሳደግ ተችሏል ነው ያሉት።
ዘመናዊ የግብር ስርዓትን በማጠናከር ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት እና የታክስ ተደራሽነትን ለማስፋት የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጠሉም ሚኒስትሯ አረጋግጠዋል።
በ2018 ባለፉት ስድስት ወራት 709 ቢሊየን ብር ገቢ መሰብሰብ ተችሏል ብለዋል። ይህ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ256 ቢሊየን ብር ብልጫ ያለው መሆኑን ጠቁመዋል።
በ2018 በጠቅላላው 2 ነጥብ 1 ትሪሊየን ብር ገቢ ለመሰብሰብ ታቅዶ እየተሰራ እንደሚገኝ አስታውቀዋል።
በቀጣይም ቴክኖሎጂ መር የታክስ አስተዳደርን የበለጠ በመዘርጋት የታክስ ስወራን መከላከል፣ በግብር ከፋዩ እና በታክስ አስተዳደሩ መካከል መተማመን ላይ የተመሰረተ የታክስ ስርዓትን ለመከተል የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ማለታቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል።
ጋምቤላ፤ ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መምጣቱን የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት...
Sep 4, 2026
አሶሳ፤ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ)፡- በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት ተኪ ምርቶችን የማምረት ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የክልሉ ርዕሰ ...
Sep 3, 2026
ሆሳዕና፤ ነሀሴ 5/2018 (ኢዜአ)፡-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ዜጎችን በሥራ ዕድል ተጠቃሚ ለማድረግ በተከናወኑ ሥራዎች ውጤት መመዝገ...
Aug 12, 2026
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 5/2018 (ኢዜአ)፦የመንግሥት በሙስናና ሕገ ወጥ ድርጊት የተሰማሩ አካላትን በሕግ ተጠያቂ የማድረግ ርምጃ ቀጣይነት ሊኖረው እንደሚገባ ኢዜአ...
Aug 12, 2026