የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ህይወት እና ጉዞ

ዘርፉ ኢኖቬሽን እና ስራ ፈጠራን በመደገፍ ለሃገራዊ እድገቱ የበኩሉን እንዲወጣ ለማድረግ የተጀመሩ የለውጥ ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ

Jan 16, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ ጥር 7/2018(ኢዜአ)፦ ዘርፉ ኢኖቬሽን እና ስራ ፈጠራን በመደገፍ ለሃገራዊ እድገቱ የበኩሉን እንዲወጣ ለማድረግ የተጀመሩ የለውጥ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ‎የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተርሃና ተኹልቁ ገለጹ፡፡

ሃገራዊ ለውጡ ለኢኮኖሚው ስርዓት ካስተዋወቃቸው ተቋማት መካከል የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን አንዱ ነው። ‎

ይህ ባለስልጣን የካፒታል ገበያ ስርዓትን ፈጠራን በማበረታታት በካፒታል ፈላጊዎች እና ካፒታል አቅራቢዎች መካከል ድልድይ የሚሆን ስርዓት እየገነባ መሆኑ ተመላክቷል።

‎‎በኢትዮጵያ በ2011 ዓ.ም በሃገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያው ለመጀመሪያ ጊዜ የተዋወቀው የካፒታል ገበያ ስርዓት ባለፉት ዓመታት የተለያዩ ሂደቶችን አልፎ ሶስት ቁልፍ ተቋማትን መፍጠር መቻሉን ‎የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተርሃና ተኹልቁ ተናግረዋል።

እነዚህም የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን፣ የኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለንዋዮች ገበያ እና የማዕከላዊ ሰነደ ሙዓለንዋዮች ግምጃ ቤት መሆናቸውን ጠቁመዋል።

እነዚህ ተቋማት ከማቋቋም ባለፈ የካፒታል ገበያ አገልግሎት የሚሰጡ 15 ተቋማት ፈቃድ አግኝተው ወደ ስራ መግባታቸውንም አስታውቀዋል።

ተቋማቱም የተከፈለ ካፒታላቸው 1.5 ቢሊየን ብር መድረሱን እና በተጨማሪም 10 ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለንዋይ ገበያ ላይ ለመመዝገብ ሂደት ላይ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

በባንኮች መካከል በገበያ ላይ የተመሰረተ የገንዘብ ልውውጥ እያደገ መጥቷልም ብለዋል። በቀጣይ ዘርፉ ኢኖቬሽን እና ስራ ፈጠራን በመደገፍ ለሃገራዊ እድገቱ የበኩሉን እንዲወጣ ለማድረግ የተጀመሩ የለውጥ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ መናገራቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መጥቷል

ጋምቤላ፤ ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መምጣቱን የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት...

Sep 4, 2026

በክልሉ ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት ተኪ ምርቶችን የማምረት ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል -ርዕሰ መስተዳድር አሻደሊ ሀሰን

አሶሳ፤ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ)፡- በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት ተኪ ምርቶችን የማምረት ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የክልሉ ርዕሰ ...

Sep 3, 2026

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሥራ ዕድል ፈጠራ በተከናወኑ ሥራዎች ውጤት ተገኝቷል

ሆሳዕና፤ ነሀሴ 5/2018 (ኢዜአ)፡-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ዜጎችን በሥራ ዕድል ተጠቃሚ ለማድረግ በተከናወኑ ሥራዎች ውጤት መመዝገ...

Aug 12, 2026

በሙስናና ሕገ ወጥ ድርጊት የተሰማሩ አካላትን ተጠያቂ የማድረግ ርምጃ ቀጣይነት ሊኖረው ይገባል

አዲስ አበባ፤ነሐሴ 5/2018 (ኢዜአ)፦የመንግሥት በሙስናና ሕገ ወጥ ድርጊት የተሰማሩ አካላትን በሕግ ተጠያቂ የማድረግ ርምጃ ቀጣይነት ሊኖረው እንደሚገባ ኢዜአ...

Aug 12, 2026