🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ የካቲት 23/2018(ኢዜአ)፦ በዓድዋ ድል የታየውን አርበኝነት፣ የባቡር መሰረተ ልማት ስራዎችን በራስ አቅም በፍጥነትና በውጤታማነት በማጠናቀቅ ደግመን እናሳያለን ሲሉ የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር ትራንስፖርት አክሲዮን ማህበር ዋና ስራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ገለጹ።
ከዐድዋ ተራሮች እስከ ጉባ፤ ዐድዋ በልኩ ሲዘከር!
የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር ትራንስፖርት አክሲዮን ማህበር 130ኛውን የዓድዋ ድል በዓል አክብሯል።
በዓሉን በማስመልከት በራስ አቅም እየተገነባና እየተጠናቀቀ የሚገኘው የኤ.ኤም.ጂ ኢንዱስትሪ ፓርክን ከኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር መስመር የሚያገናኘው የሶስት ኪሎ ሜትር የባቡር መሰረተ ልማት ተጎብኝቷል።

በጉብኝቱ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ ደንጌ ቦሩ፣ የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር ትራንስፖርት አክሲዮን ማህበር ዋና ስራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ታከለ ኡማ እና ሌሎች የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
ኢንጂነር ታከለ ኡማ ፤ አባቶቻችን በከፈሉት መስዋዕትነት ታላቁን የዓድዋ ድል ታሪክ አስረክበውናል ብለዋል።

እኛ ደግሞ ለቀጣዩ ትውልድ ስንቅ የሚሆን አኩሪ የባቡር ትራንስፖርት መሠረት ልማት በራስ አቅም እየገነባን እንገኛለን ብለዋል።
እየተገነቡ የሚገኙት የባቡር መሰረተ ልማቶች ነገ ላይ ከዚህ የተሻለና የበለጠ ሥራ መሥራት እንደምንችል ማሳያ ናቸው ሲሉም ተናግረዋል።
በቀጣይም ትልልቅ የባቡርና ሌሎች መሠረተ ልማቶችን ለመገንባት ሰፊ ዕቅድ መያዙን ጨምረው ገልጸዋል።
ጋምቤላ፤ ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መምጣቱን የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት...
Sep 4, 2026
አሶሳ፤ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ)፡- በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት ተኪ ምርቶችን የማምረት ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የክልሉ ርዕሰ ...
Sep 3, 2026
ሆሳዕና፤ ነሀሴ 5/2018 (ኢዜአ)፡-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ዜጎችን በሥራ ዕድል ተጠቃሚ ለማድረግ በተከናወኑ ሥራዎች ውጤት መመዝገ...
Aug 12, 2026
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 5/2018 (ኢዜአ)፦የመንግሥት በሙስናና ሕገ ወጥ ድርጊት የተሰማሩ አካላትን በሕግ ተጠያቂ የማድረግ ርምጃ ቀጣይነት ሊኖረው እንደሚገባ ኢዜአ...
Aug 12, 2026