🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ የካቲት 23/2018(ኢዜአ)፦የዓድዋ ድል ለመላው ጥቁር ሕዝብ የነፃነት ፋና ወጊ ከመሆኑም ባለፈ በልማት ሥራዎች ታሪክን ለመድገም ትልቅ መነሳሳት የሚፈጥር መሆኑን የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ ዴንጌ ቦሩ ገለጹ።
በኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር ትራንስፖርት አክሲዮን ማህበር 130ኛው የዓድዋ ድል በዓል ተክብሯል።
በዓድዋ ድል የታየውን አርበኝነት፣ የባቡር መሰረተ ልማትን በራስ አቅም በውጤታማነት በመገንባት እንደግመዋለን
ሚኒስትር ዴኤታ ዴንጌ ቦሩ በዚሁ ወቅት፤ የዓድዋ ድል ለፓን አፍሪካኒዝም እንቅስቃሴ መሠረት የጣለ ታላቅ ድል ነው ብለዋል።

የአሁኑ ትውልድ የአባቶቹን አርበኝነት በልማት ሥራዎች ሊደግመው እንደሚገባ ጠቁመው አሁን ላይ ድህነትን ታሪክ ለማድረግ በጋራ መረባረብ ይገባል ብለዋል፡፡
በዘርፉ እየተከናወኑ ያሉ ውጤታማ የልማት ሥራዎች የሀገሪቱን ብልጽግና ለማረጋገጥ ወሳኝ መሆናቸውንም አብራርተዋል።
በተለይም በባቡር መሰረተ ልማት ረገድ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት አስደናቂ የአርበኝነት ሥራ መሆናቸውን ጠቅሰው ዘርፉ ለሀገሪቱ የኢኮኖሚ ትስስር ትልቅ መሠረት እየጣለ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የተጀመሩ የልማት ሥራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር ትራንስፖርት አክሲዮን ማህበር ሠራተኞች በቁርጠኝነትና በከፍተኛ መነሳሳት እንዲረባረቡ ጥሪ አቅርበዋል።
ጋምቤላ፤ ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መምጣቱን የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት...
Sep 4, 2026
አሶሳ፤ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ)፡- በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት ተኪ ምርቶችን የማምረት ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የክልሉ ርዕሰ ...
Sep 3, 2026
ሆሳዕና፤ ነሀሴ 5/2018 (ኢዜአ)፡-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ዜጎችን በሥራ ዕድል ተጠቃሚ ለማድረግ በተከናወኑ ሥራዎች ውጤት መመዝገ...
Aug 12, 2026
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 5/2018 (ኢዜአ)፦የመንግሥት በሙስናና ሕገ ወጥ ድርጊት የተሰማሩ አካላትን በሕግ ተጠያቂ የማድረግ ርምጃ ቀጣይነት ሊኖረው እንደሚገባ ኢዜአ...
Aug 12, 2026