የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ህይወት እና ጉዞ

የሀዋሳ ከተማ የኮሪደር ልማት ለመዝናኛና ለንግድ እንቅስቃሴ ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል 

Mar 4, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ሀዋሳ፤ የካቲት 24/2018(ኢዜአ)፦ የሀዋሳ ከተማ የኮሪደር ልማት ለከተማዋ ድምቀት ከመሆን ባለፈ በተለያዩ የከተማዋ አካባቢዎች ለመዝናኛና ለንግድ እንቅስቃሴ ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን ነዋሪዎች ገለጹ።

በሀዋሳ ከተማ በምዕራፍ ሁለት የተከናወነው የኮሪደር ልማት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በተገኙበት በይፋ ተመርቆ ለአገልግሎት መብቃቱ የሚታወስ ነው።

ልማቱን በማስመልከት ኢዜአ ያነጋገራቸው የከተማዋ ነዋሪዎች እንደገለጹት የኮሪደር ልማት አማራጭ መዝናኛ ከመፍጠር ባለፈ ለኑሮና ለንግድ እንቅስቃሴ ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል።


ከአስተያየት ሰጪዎቹ መካከል ኮሪደር ልማቱን ተከትሎ በተገነቡ የንግድ ሱቆች የካፌ አገልግሎት ሥራ የጀመሩት ብፅዕት ዮሴፍ፣ ልማቱን ተከትሎ ለእሳቸውና በስራቸው ላሉ ወጣቶች የሥራ ዕድል መፈጠሩን ተናግረዋል።

የካፌ አገልግሎት የሚሰጡበት ቦታ ቀደም ሲል ለምንም አገልግሎት ሳይውል መቆየቱን ገልጸው፣ በኮሪደር ልማቱ አካባቢው ለምቶ ለሰዎች ምዝናኛ ስፍራ እንዲሆን ተደርጓል ብለዋል።

በዚህም በምሽት ጭምር ሰዎች የእግር ጉዞ በማድረግና እየተዝናኑ መሆኑን ገልጸው፣ የተፈጠረላቸው የሥራ ዕድል የሥራ ባህላቸውንም እንደቀየረው ተናግረዋል።

የኮሪደር ልማት በተከናወነባቸው አካባቢዎች በተገነቡ ካፌዎች ሲዝናኑ ከነበሩ ነዋሪዎች መካከል ዘሪሁን ዘርፉ፣ ከዚህ በፊት በአካባቢው ከመንገዱ ጥበት የተነሳ በእግር ለመጓዝ ሲቸገሩ ቆይተዋል።


በዚህም ከተሽከርካሪ ጋር በመጋፋት ይተላለፉ እንደነበር አስታውሰው፣ በአሁኑ ወቅት መንገዱ ከመስፋቱ ባለፈ የእግረኛ መንገድና መዝናኛዎችን አካቶ መገንባቱ ምቹ ሁኔታ ተፈጥሯል ብለዋል።

በኮሪደር ልማቱ የተካተቱ የስፖርት ማዘውተሪያዎች፣ የልጆች መጫወቻዎችና መናፈሻዎች ለሥራ ዕድል ፈጠራና ለመዝናናት ምቹ ሁኔታ ፈጥረዋል ሲሉም ገልጸዋል።

ከቤተሰባቸው ጋር ለመዝናናት እንደመጡ የተናገሩት ደረሰ ደምሴ በአካባቢያቸው አዋቂንና ልጆችን ታሳቢ ያደረገ መዝናኛ ስፍራ በመገንባቱ ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸዋል።


የኮሪደር ልማቱ ሀዋሳ ከተማ ባላት የተፈጥሮ መስህብ ላይ ሌላ ድምቀት እንደፈጠረላት ገልጸው፣ ከሥራ በኋላ ከነቤተሰባቸው ለመዝናናት ቦታውን እንደሚመርጡት ተናግረዋል።

በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር የከተማና መሠረተ ልማት መምሪያ ኃላፊ ቸርነት ፍላቴ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ጥሪን ተከትሎ የሀዋሳ ከተማ የቱሪስት ፍሰት እየጨመረ መጥቷል ብለዋል፡፡


የኮሪደር ልማት ሥራው በተጠናቀቀባቸው አካባቢዎች ደረጃቸውን የጠበቁ የካፌና ሌላ አገልግሎት መስጫ ሥፍራዎች መገንባታቸውንም አመልክተዋል።

የኮሪደር ልማቱ በሌሎች የከተማዋ አካባቢዎችም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀው፣ በአሁኑ ወቅት በሀዋሳ ሐይቅ ዳርቻ እና ሌሎች ሥፍራዎች ልማቱ እየተከናወነ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

በከተማዋ በተለይ የኮሪደር ልማት በተከናወነባቸው አካባቢዎች የንግድ እንቅስቃሴዎች እየተስፋፉ መምጣታቸውን ጠቅሰው፣ ከተማዋን ለመዝናናም ሆነ ለንግድ ሥራ ምቹ የማድረግ ተግባር ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መጥቷል

ጋምቤላ፤ ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መምጣቱን የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት...

Sep 4, 2026

በክልሉ ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት ተኪ ምርቶችን የማምረት ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል -ርዕሰ መስተዳድር አሻደሊ ሀሰን

አሶሳ፤ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ)፡- በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት ተኪ ምርቶችን የማምረት ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የክልሉ ርዕሰ ...

Sep 3, 2026

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሥራ ዕድል ፈጠራ በተከናወኑ ሥራዎች ውጤት ተገኝቷል

ሆሳዕና፤ ነሀሴ 5/2018 (ኢዜአ)፡-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ዜጎችን በሥራ ዕድል ተጠቃሚ ለማድረግ በተከናወኑ ሥራዎች ውጤት መመዝገ...

Aug 12, 2026

በሙስናና ሕገ ወጥ ድርጊት የተሰማሩ አካላትን ተጠያቂ የማድረግ ርምጃ ቀጣይነት ሊኖረው ይገባል

አዲስ አበባ፤ነሐሴ 5/2018 (ኢዜአ)፦የመንግሥት በሙስናና ሕገ ወጥ ድርጊት የተሰማሩ አካላትን በሕግ ተጠያቂ የማድረግ ርምጃ ቀጣይነት ሊኖረው እንደሚገባ ኢዜአ...

Aug 12, 2026