🔇Unmute
አምቦ ፤ የካቲት 24/2018 (ኢዜአ)፦የአምቦ ከተማ አስተዳደር የህብረተሰቡን የመኖሪያ ቤት ችግር ለማቃለል ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ገለጸ፡፡
በአምቦ ከተማ ያለውን የመኖሪያ ቤት ችግር ለማቃለል በማህበር ለተደራጁ 1 ሺህ 516 ነዋሪዎች የቤት መስሪያ ቦታ ተሰጥቷል።
ለከተማው ነዋሪዎች ዛሬ የቤት መስሪያ ቦታ የተሰጠው በከተማው ማዘጋጃ ቤት በተከናወነ እጣ የማውጣት መርሀግብር ነው።
በሸገር ከተማ የጤና አገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል የተከናወኑ ተግባራት ውጤት እያመጡ ነው
የቦታ ርክክብ መርሀግብሩ ላይ የተገኙት የአምቦ ከተማ ከንቲባ ሃጫሉ ገመቹ እንደገለጹት፤ የቤት መስሪያ ቦታ የተሰጠው በከተማዋ ያለውን የመኖሪያ ቤት ፍላጎት ታሳቢ በማድረግ ነው።
የቤት መስሪያ ቦታ መሰጠቱ በነዋሪዎች ዘንድ ሲነሳ የነበረን ቅሬታ እንደሚያቃልል ገልጸው፣ በበጀት ዓመቱ የቤት መሰሪያ ቦታ ከተሰጣቸው ነዋሪዎች መካከል አብዛኞቹ የመንግስት ሠራተኞች ናቸው ብለዋል።
ነዋሪዎቹ በከተማዋ ማስተር ፕላን መሰረት ደረጃውን የጠበቀ ቤት መስራት እንደሚጠበቅባቸው ገልጸው፣ በቀጣይም የህብረተሰቡን የመኖሪያ ቤት ችግር ለማቃለል አስተዳደሩ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ አረጋግጠዋል።

የአምቦ ከተማ መሬት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ መርጋ ወዳጆ በበኩላቸው፤ በወጣው ዕጣ መሰረት ለማህበራቱ የቦታ ርክክብ መደረጉን ገልጸዋል።
ዛሬ የቤት መስሪያ ቦታ የተሰጠው በ75 የቤት ማህበራት ለተደራጁ 1 ሺህ 516 ነዋሪዎች ሲሆን ነዋሪዎቹም በተለያዩ ማህበራት ተደራጅተው ከሦስት እስከ ሰባት ዓመት ሲጠባበቁ የቆዩ መሆናቸውን ተናግረዋል።
እንደ ኃላፊው ገለጻ ቦታው የተዘጋጀው በአምቦ ከተማ አዋሮ ቆራ ቀበሌ ሲሆን በእዚህም ለእያንዳንዱ ተጠቃሚ 140 ካሬ ሜትር ቦታ ተሰጥቷል።
ከዕድሉ ተጠቃሚዎች መካከል መምህራን፣ የመከላከያ ሠራዊት አባላት፣ የጤና ባለሙያዎች፣ የጸጥታና የህግ ባለሙያዎች ይገኙበታል ተብሏል።
የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ ከተሰጣቸው መካከል ቆንጅት ዱጉማ በሰጡት አስተያየት፤ በተለያዩ ጊዜያት የተሰጣቸውን ግዳጅ እንደተወጡና ለሀገር ላበረከቱት ውለታም የቤት መስሪያ ቦታ በማግኘታቸው መደሰታቸውን ገልጸዋል።

የቦታ አሰጣጡ ተግባር ፍትሃዊና ግልጽ መሆኑን የተናገሩት ደግሞ አቶ ጌቱ አዱኛ የተባሉ የጤና ባለሙያ ናቸው።
በማህበር ተደራጅተው ለዓመታት ገንዘብ እንደቆጠቡና ከመንግስት ምላሽ ሲጠባበቁ እንደነበር አስታውሰው፣ ከተማ አስተዳደሩ ለጥያቄያቸው ምላሽ በመስጠቱ ደስተኛ መሆናቸውን ተናግረዋል።

አስተዳደሩ ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ከማህበራቸው አባላት ጋር በመተባበር የቤት ግንባታውን ለመጀመር እየተዘጋጁ መሆኑንም ገልጸዋል።
ጋምቤላ፤ ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መምጣቱን የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት...
Sep 4, 2026
አሶሳ፤ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ)፡- በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት ተኪ ምርቶችን የማምረት ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የክልሉ ርዕሰ ...
Sep 3, 2026
ሆሳዕና፤ ነሀሴ 5/2018 (ኢዜአ)፡-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ዜጎችን በሥራ ዕድል ተጠቃሚ ለማድረግ በተከናወኑ ሥራዎች ውጤት መመዝገ...
Aug 12, 2026
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 5/2018 (ኢዜአ)፦የመንግሥት በሙስናና ሕገ ወጥ ድርጊት የተሰማሩ አካላትን በሕግ ተጠያቂ የማድረግ ርምጃ ቀጣይነት ሊኖረው እንደሚገባ ኢዜአ...
Aug 12, 2026