🔇Unmute
አሶሳ፤ መጋቢት 1/2018(ኢዜአ)፦ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የግልገል በለስ ከተማ የኮሪደር ልማት በፍጥነት እየተከናወነ መሆኑን የከተማዋ ከንቲባ አሳዬ አበበ ተናገሩ።
የኮሪደር ልማት ከተሞችን ከማዘመን ባለፈ ለኑሮና ለንግድ አመቺ እንዲሆኑ አስችሏቸዋል።

ልማቱ ከአዲስ አበባ ጀምሮ በመላ የሀገሪቱ ከተሞች በመስፋት የከተሞቹን ገጽታ በእጅጉ እየለወጠ ይገኛል።
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ከተማን ጨምሮ በባምባሲ እና ግልገል በለስ ከተሞች የኮሪደር ልማት ስራው ተጠናክሮ ቀጥሏል።

ግልገል በለስ ከተማ 3 ነጥብ 6 ኪሎ ሜትር የኮሪደር ልማት ስራ ከተጀመረ ሁለት ወራትን ያስቆጠረ ሲሆን ግንባታው በፍጥነት እየተከናወነ መሆኑን የከተማዋ ከንቲባ አሳዬ አበበ ለኢዜአ ተናግረዋል።
የኮሪደር ልማቱ የከተማዋን ገፅታ በመቀየር ለነዋሪዎቿ እና ለጎብኚዎች ተመራጭ በማድረግ ላይ ይገኛል ብለዋል።
ከተማዋ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መዳረሻ በመሆኗ የኮሪደር ልማቱ የተለያዩ አገልግሎት መስጫ ማዕከላትን አካቶ እየተከናወነ መሆኑንም ገልጸዋል።
የአረንጓዴ ቦታዎች፣ የህዝብ መጸዳጃ ቤት፣ ካፍቴሪያና የመዝናኛ ማዕከላትን የያዘው የኮሪደር ልማት በፍጥነት እየተከናወነ እንደሚገኝም ተናግረዋል።
አሁኑ ላይ የእግረኞች እና የብስክሌት መንገድ በመጠናቀቅ ላይ እንደሆነና የአገልግሎት መስጫ ማዕከላቱንም በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ እየተሰራ ነው ብለዋል።
የከተማዋ ነዋሪዎች የኮሪደር ልማቱን በጉልበት እና በገንዘብ መደገፋቸውን ጠቁመው፤ ድጋፋቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉም ከንቲባው ጠይቀዋል።
የኮሪደር ልማቱ በፍጥነት እና በጥራት እንዲከናወን አመራሩ የቅርብ ክትትል እያደረገ መሆኑንም ጨምረው አስታውቀዋል።
ጋምቤላ፤ ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መምጣቱን የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት...
Sep 4, 2026
አሶሳ፤ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ)፡- በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት ተኪ ምርቶችን የማምረት ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የክልሉ ርዕሰ ...
Sep 3, 2026
ሆሳዕና፤ ነሀሴ 5/2018 (ኢዜአ)፡-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ዜጎችን በሥራ ዕድል ተጠቃሚ ለማድረግ በተከናወኑ ሥራዎች ውጤት መመዝገ...
Aug 12, 2026
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 5/2018 (ኢዜአ)፦የመንግሥት በሙስናና ሕገ ወጥ ድርጊት የተሰማሩ አካላትን በሕግ ተጠያቂ የማድረግ ርምጃ ቀጣይነት ሊኖረው እንደሚገባ ኢዜአ...
Aug 12, 2026