የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ህይወት እና ጉዞ

የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ ምላሽ እንዲያገኝ ሁላችንም ሃላፊነት ወስደን እንሰራለን- የፖለቲካ ፓርቲዎች

Mar 26, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ሆሳዕና፤መጋቢት16/2018 (ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ ምላሽ እንዲያገኝ ሁላችንም ሃላፊነት ወስደን በዘላቂነት እንሰራለን ሲሉ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ገለጹ።

በዚሁ ጉዳይ ላይ ኢዜአ ያነጋገራቸው በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አመራሮች፤ ኢትዮጵያ ተዘግቶባት ልትኖር የማትችል በመሆኑ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄዋ ምላሽ እንዲያገኝ የሁላችንም ሃላፊነት ሆኖ እንሰራለን ብለዋል።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የኢዜማ ሰብሳቢ እና በክልሉ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ደምስ ገብሬ፤ የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ ከብሄራዊ ጥቅምም ባለፈ የሀገርና የዜጎች የህልውና ጉዳይ መሆኑን ገልጸዋል።

በዚህ ጉዳይ ላይ ፓርቲያቸው የጸና አቋም ያለው መሆኑን አረጋግጠው በጋራ ምክር ቤቱም ለሀገር ብሄራዊ ጥቅም ተቀራርበን እየሰራን እንገኛለን ብለዋል።


በብልጽግና ፓርቲ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት የዴሞክራሲ ባህል ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ እና የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ምክትል ሰብሳቢ አቶ በረከት ከድር፤ የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ ከጥቅም ባለፈ የህልውና ጉዳይ መሆኑን አንስተዋል።

በመሆኑም ይህንን የትውልድ ጥያቄ ሆኖ እየተነሳ ያለ ጉዳይ ምላሽ እንዲያገኝ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤትም አጀንዳ አድርጎ እየሰራበት መሆኑን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ ምላሽ እንዲያገኝ ሁላችንም ሃላፊነት ወስደን በዘላቂነት እንሰራለን ሲሉ አረጋግጠዋል።


ያጋራ ምክር ቤቱ አባልና የጉራጌ አንድነትና ፍትህ ፓርቲ (ጎጎት) አመራር የሆኑት አብድልአዚዝ ሙሰማ (ዶ/ር)፤ የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ የዚህ ትውልድ የጋራ አጀንዳ በመሆኑ ለምላሹ በጋራ ቆመን እንሰራለን ብለዋል።

በዚህ ረገድ ፓርቲያቸው ጠንካራ አቋም ያለው መሆኑን አረጋግጠው ለሀገር ህልውና እና ብሄራዊ ጥቅም መሳካት ትብብርና አብሮነታቸን ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጉዳይ የታሪክ፣ የመልከአ ምድር እና ዓለም አቀፍ ህጎችን መሰረት ያደረገ ተገቢ ጥያቄ መሆኑ ይታወቃል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መጥቷል

ጋምቤላ፤ ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መምጣቱን የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት...

Sep 4, 2026

በክልሉ ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት ተኪ ምርቶችን የማምረት ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል -ርዕሰ መስተዳድር አሻደሊ ሀሰን

አሶሳ፤ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ)፡- በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት ተኪ ምርቶችን የማምረት ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የክልሉ ርዕሰ ...

Sep 3, 2026

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሥራ ዕድል ፈጠራ በተከናወኑ ሥራዎች ውጤት ተገኝቷል

ሆሳዕና፤ ነሀሴ 5/2018 (ኢዜአ)፡-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ዜጎችን በሥራ ዕድል ተጠቃሚ ለማድረግ በተከናወኑ ሥራዎች ውጤት መመዝገ...

Aug 12, 2026

በሙስናና ሕገ ወጥ ድርጊት የተሰማሩ አካላትን ተጠያቂ የማድረግ ርምጃ ቀጣይነት ሊኖረው ይገባል

አዲስ አበባ፤ነሐሴ 5/2018 (ኢዜአ)፦የመንግሥት በሙስናና ሕገ ወጥ ድርጊት የተሰማሩ አካላትን በሕግ ተጠያቂ የማድረግ ርምጃ ቀጣይነት ሊኖረው እንደሚገባ ኢዜአ...

Aug 12, 2026