የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ህይወት እና ጉዞ

በምዕራብ ሸዋ ዞን ከመስኖ ልማት ከ5 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ተሰበሰበ

Mar 27, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አምቦ፣ መጋቢት 17/2018 (ኢዜአ)፦ በምዕራብ ሸዋ ዞን በዘንድሮ የበጋ መስኖ ልማት በመጀመሪያ ዙር ከለማው መሬት ከ5 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት መሰብሰቡን የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

በጽህፈት ቤቱ የመስኖ ልማት ባለሙያ አቶ ገዛኸኝ ዲንሳ ለኢዜአ እንደገለፁት፤ በዞኑ በመስኖ የሚለማ መሬትን በማስፋት ምርትና ምርታማነትን በመጨመር የተሻለ ውጤት እየተገኘ ነው።


በዘንድሮ የበጋ መስኖ ልማት በአንደኛው ዙር 30 ሺህ ሄክታር መሬት ለማልማት ታቅዶ ከእቅድ በላይ 32 ሺህ ሄክታር በተለያዩ የሰብል አይነቶች፣ በአትክልትና ፍራፍሬ ማልማት ተችሏል ብለዋል።

በልማቱም ከ31 ሺህ በላይ አርሶ አደሮችን በማሳተፍ በመስኖ እየለማ ካለው መሬት ከ5 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት መሰብሰቡን ተናግረዋል፡፡

የተሰበሰበው ምርት ገበያን በማረጋጋት ረገድ ትልቅ አስተዋጽኦ እያበረከተ ሲሆን በአሁኑ ወቅትም ሁለተኛው ዙር የበጋ መስኖ ልማት ስራ ተጠናክሮ መቀጠሉን አስረድተዋል።


በሁለተኛው ዙር የመስኖ ልማት ስራም ከ22 ሺህ በላይ ሄክታር መሬት በማልማት 3 ነጥብ 4 ሚሊዮን ኩንታል የአትክልት ምርት ለመሰብሰብ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

በመስኖ ልማቱ ከተሳተፉት መካከል የቶኬ ኩታዬ ወረዳ አርሶ አደር ተሾመ በቀለ፤ በዘመናዊ የመስኖ ልማት ታግዘው ማልማት ከጀመሩ ወዲህ ተጠቃሚነታቸው እያደገ መምጣቱን ተናግረዋል።

ዘንድሮም የተሻለ ዝግጅት አድርገው እያለሙ መሆኑን አንስተው፣ ካለፈው የበለጠ ምርት እንደሚጠብቁ ነው የተናገሩት።

የዚሁ ወረዳ አርሶ አደር ተፈራ በንቲ በበኩላቸው፤ በበጋ መስኖ ልማት ያገኙት ምርት ከፍጆታቸው አልፎ ለገበያ በማቅረብ ኢኮኖሚያቸውን እያሳደጉ መሆኑን ገልፀዋል።

በዞኑ ባለፈው ዓመት በአንደኛውና በሁለተኛው ዙር በመስኖ ከለማው መሬት 10 ሚሊዮን ኩንታል ምርት መገኘቱም ታውቋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መጥቷል

ጋምቤላ፤ ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መምጣቱን የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት...

Sep 4, 2026

በክልሉ ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት ተኪ ምርቶችን የማምረት ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል -ርዕሰ መስተዳድር አሻደሊ ሀሰን

አሶሳ፤ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ)፡- በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት ተኪ ምርቶችን የማምረት ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የክልሉ ርዕሰ ...

Sep 3, 2026

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሥራ ዕድል ፈጠራ በተከናወኑ ሥራዎች ውጤት ተገኝቷል

ሆሳዕና፤ ነሀሴ 5/2018 (ኢዜአ)፡-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ዜጎችን በሥራ ዕድል ተጠቃሚ ለማድረግ በተከናወኑ ሥራዎች ውጤት መመዝገ...

Aug 12, 2026

በሙስናና ሕገ ወጥ ድርጊት የተሰማሩ አካላትን ተጠያቂ የማድረግ ርምጃ ቀጣይነት ሊኖረው ይገባል

አዲስ አበባ፤ነሐሴ 5/2018 (ኢዜአ)፦የመንግሥት በሙስናና ሕገ ወጥ ድርጊት የተሰማሩ አካላትን በሕግ ተጠያቂ የማድረግ ርምጃ ቀጣይነት ሊኖረው እንደሚገባ ኢዜአ...

Aug 12, 2026