የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ህይወት እና ጉዞ

በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ሀብት የሚያፈሩበትን አቅም ለመፍጠር ተችሏል

Apr 3, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ባህር ዳር/ጎንደር ፣መጋቢት24/2018(ኢዜአ)፡-በከተማዋ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ሀብት ለማፍራት እንዲችሉ የተከናወኑ ተግባራት ስኬታማ መሆናቸውን የባሀርዳር ከተማ አስተዳዳር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው ገለጹ።

በባሀርዳር ከተማ በልማታዊ ሴፍትኔት ፕሮጀክት በመታቀፍ ሃብት ለማፍራት የቻሉ 3 ሺህ 686 ዜጎች ዛሬ ተመርቀዋል።


የባህርዳር ከተማ አስተዳዳር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ጎሹ እንዳላማው በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤በከተማዋ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ሀብት እንዲያፈሩ የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ ናቸው።

ለአብነትም በርካታ ዜጎች በከተማ ሴፍቲኔት ፕሮጀክት ታቅፈው ሃብት በማፍራታቸውም ወደ ሌሎች የስራ ዘርፎች በመሸጋገር ላይ መሆናቸውን ነው የገለጹት።

በፐሮግራሙ የታቀፉት ዜጎች ሰርተው ካገኙት በመቆጠብና በሌሎች ተጨማሪ የገቢ ማስገኛ ስራዎች በመሳተፍ ጥሪት ማፍራት መቻላቸውን ጠቅሰዋል።

በዛሬው እለትም በከተማ ሴፍቲኔት ፕሮጀክት ተሰማርተው ሃብት ያፈሩ ሶስት ሺህ 686 አባውራና እማውራዎችን ማስመረቅ መቻሉን አስገንዝበዋል።

በፕሮጀክቱ የታቀፉ ወገኖች በአረንጓዴ ልማት፣ በጽዳትና ውበት፤ በከተማ ግብርና እና በመሳሰሉተ የልማት ስራዎች መሳተፋቸውን ነው ያመለከቱት ።

ተመራቂዎቹ በፕሮግራሙ ታቅፈው ካፈሩት ሀብት በተጨማሪ በዘላቂነት እንዲቋቋሙ ለማድረግም 248 ሚሊዮን 335 ሺህ ብር መመደቡንም ነው የገለጹት።


የአማራ ክልል ልማታዊ ሴፍቲኔት ማስተባበሪያ ስትሪንግ ኮሚቴ አባል ወይዘሮ መሰረት አዱኛ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፤ በልማታዊ ሴፍቲኔት የተሰማሩ ወገኖችን ውጤታማ ለማድረግ የሚከናወኑ ተግባራት ተጠናክረው ይቀጥላሉ።

ከዚህ ውስጥም ተመራቂዎቹ የሚሰጣቸውን ገንዝብ ተጠቅመው በተሰማሩበት መስክ ውጤታማ እንዲሆኑ የክትትልና የድጋፍ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ነው የገለጹት።

የመርሃ- ግብሩ ተሳታፊዎች በበኩላቸው በስራ ቆይታቸው ያገኙትን የቁጠባ፣ የስራ ልምድና ገንዘብ በመጠቀም በዘላቂነት ኑሯቸውን ለመቀየር እንደሚሰሩም ነው የጠቀሱት።

ከተመራቂዎች መካከልም ወይዘሮ እንያት ጌትነት እንዳሉት፤ በልማታዊ ሴፍቲኔት ፐሮግራም በመታቀፍ ካገኙት ገቢ በመቆጠብና በንግድ ስራ በመሰማራት ገቢያቸውን በከፍተኛ ሁኔታ ለማሳደግ መቻላቸውን ይናገራሉ።

በአሁን ወቅትም ባገኙት ተጨማሪ ድጋፍ ተጠቅመው የንግድ ስራቸውን በማስፋፋት ትልቅ ደረጃ ለመድረስ አልመው እንደሚሰሩም ነው የጠቀሱት።

በሌላ በኩል በጎንደር ከተማ በመርሃ ግብሩ ታቅፈው ጥሪት በማፍራት ወደ ተሻለ ህይወት የተሸጋገሩ ከ4ሺ በላይ የከተማ ልማታዊ ሴፍቲኔት ተጠቃሚ የህብረተሰብ ክፍሎች በዛሬ እለት ለምረቃ በቅተዋል፡፡


በምረቃ ስነ ስርአቱ ላይ የክልሉ ከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ ሃላፊ ሞላ መልካሙ (ዶ/ር) እንደተናገሩት መንግስት በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ዜጎችን ከድህነት ለማውጣት የከተሞች የምግብ ዋስትና ስትራቴጂዎችን ቀርጾ እየተገበረ ይገኛል፡፡

በክልሉ ጎንደር ከተማን ጨምሮ በ18 ከተሞች በአካባቢ ልማት፤ በቀጥታ ድጋፍ፣ በልዩ ድጋፍና በወጣቶች ፕሮጀክት 239ሺህ 437 በላይ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ዜጎችን ተጠቃሚ የማድረግ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን ተናግረዋል።

የክልሉ መንግስት በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ዜጎችን ከተረጂነት ወደ አምራችነት ለማሸጋገር ከ60 ቢሊዮን ብር በላይ መድቦ ሰትራቴጂካዊ የሆኑ የድህነት ቅነሳ የልማት ስራዎችን ሲያከናወን መቆየቱን ጠቁመዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.