🔇Unmute
አዲስ አበባ፤መጋቢት 30/2018 (ኢዜአ)፦ቬሎሲቲ የትራንስፖርት አገልግሎት በመዲናዋ የብዙሃን ትራንስፖርት ፍሰትን በማሳለጥ እና ተደራሽነቱን በማስፋት ረገድ ጉልህ ሚና እያበረከተ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ ያብባል አዲስ ገለጹ።
በመንግስት እና በግል አጋርነት ተመስርቶ አገልግሎት እየሰጠ የሚገኘው የቬሎሲቲ ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት የተመሰረተበትን 1ኛ ዓመት በዛሬው እለት አክብሯል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ ያብባል አዲስ፥ ድርጅቱ ከአንድ ዓመት በፊት በ100 የኤሌክትሪክ አውቶብሶች ወደ ስራ እንደገባ አስታውሰዋል።
ባለፈው አንድ ዓመትም በቀን እስከ 120 ሺህ እንዲሁም በዓመት እስከ 40 ሚሊዮን ዜጎችን በማመላስ አስተዋፅኦ ማድረጉን ተናግረዋል።
የነዋሪዎችን የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ፈጣን እና ቀልጣፋ በማድረግና የብዙሃን ትራንስፖርትን ተደራሽነት በማስፋት ረገድም ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን ጠቅሰዋል።
በዚህም የከተማዋን የብዙሃን ትራንስፖርት ድርሻ ከነበረበት 36 በመቶው ወደ 42 በመቶው ከፍ ማድረጉን ነው የተናገሩት፡፡
ከተማ አስተዳድሩ ከብክለት ነጻ የሆነ አረንጓዴ ትራንስፖርትን ለማስፋፋት እየሠራ መሆኑን ጠቅሰው፥ በዚህ ረገድ ቬሎሲቲ ትራንስፖርት በኤሌክትሪክ በሚሠሩ ተሽከርካሪዎች አገልግሎት በመስጠት ትልቅ ሚና እየተወጣ ነው ብለዋል።
ከተማ አስተዳደሩ ለአረንጓዴ ትራንስፖርት ቀዳሚ አማራጭ የሆነውን የቬሎሲቲ ትራንስፖርት ሰጭ አውቶብሶችን ቁጥር ወደ 500 ከፍ ለማድረግ አቅዶ እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
የአረንጓዴ ትራንስፖርት ማሳያ የሆነው ቬሎሲቲ ለበርካታ ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠሩንም አመላክተዋል፡፡

በበላይነህ ክንዴ ግሩፕ የትራንስፖርት ቢዝነስ አድቫይዘርና የግሬት ትራንስፖርት ዋና ስራ አስኪያጅ ግዛው አለሙ በበኩላቸው፤ በላይነህ ክንዴ ግሩፕ የአውቶብሶችን ኦፕሬሽንና አገልግሎት እንደሚያስተዳደር ተናግረዋል፡፡
በዚህም አጠቃላይ የአውቶብሶችን ስምሪትና አገልግሎት አሰጣጥ መከታተልና መቆጣጠር የሚያስችል የዲጂታል ስርዓት ወደ ስራ ማስገባቱን ገልጸዋል፡፡
የትኬትና የክፍያ ስርዓቱንም ሙሉ በሙሉ በቴክኖሎጂ የታገዘ እንዲሆን ማድረጉን ነው የጠቆሙት፡፡
አምቦ፤ ሰኔ 6/2018(ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ሸዋ ዞን ባለፉት ዓመታት በተከናወኑ የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ስራዎች ለንብ ማነብ ምቹ ሁኔታ በመፍጠሩ...
Jun 14, 2026
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 3/2018(ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል የበጋ መስኖ ልማት በምግብ ራስን ከመቻል ባለፈ የአርስ አደሩን ተጠቃሚነት እያሳደገ መሆኑን የክልሉ ምክት...
Jun 11, 2026
ሐረማያ፤ ግንቦት 20/2018 (ኢዜአ)፦ ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት የሚያሳድጉ የምርምር ቴክኖሎጂዎችን እያጎለበተ እንደሚገኝ አስታወቀ። ዩኒቨ...
Jun 1, 2026
ሆሳዕና፣ግንቦት 17/2018 (ኢዜአ)፦በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት የሚያሳድጉ የሕብረት ሥራ ማህበራትን ደግፎ የማብቃት ሥራው ተጠናክሮ እ...
May 26, 2026