የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ህይወት እና ጉዞ

ኢትዮጵያ በዓድዋ ድል ያሳየችውን አህጉራዊ ምሳሌነት ዛሬም በልማት እየደገመችው ነው-አፍሪካውያን

Apr 12, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ሚያዝያ 2/2018 (ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ በዓድዋ ድል ያሳየችውን አህጉራዊ ምሳሌነት ዛሬም በልማት እየደገመችው ነው ሲሉ የዓድዋ ድል መታሰቢያን የጎበኙ አፍሪካውያን ገለጹ።

ኢትዮጵያ የጀግንነት ታሪክ መፍለቂያ ሀገር መሆኗን በመጥቀስ፥ የዓድዋ ድል መታሰቢያ የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የአፍሪካውያንና የመላው ጥቁር ሕዝቦች አኩሪ የታሪክ ዓምድ መሆኑን ጠቅሰዋል።

በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት የተካሄደው የ16ኛው የአፍሪካ አደጋ ስጋት አቅም ጉባኤ ተሳታፊዎች የኢትዮጵያና የአፍሪካውያን የጀግንነት የታሪክ ማህደር የሆነውን የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጎብኝተዋል።


በጉብኝታቸውም የድል ታሪክ ምስክር የሆኑ ቅርሶችንና የጀግንነት አሻራዎችን የተመለከቱ ሲሆን፣ የድል መታሰቢያው ከሀገር ባለፈ ለአፍሪካ የሚተርፍ ትልቅ ትምህርት የያዘ መሆኑን ገልጸዋል።

የዓድዋ ድል ድህነትን ለማሸነፍና ለአፍሪካ ብልጽግና በትብብር ለመሥራት ትልቅ መነሳሳትን የሚፈጥር መሆኑንም ተናግረዋል።

ከጎብኚዎቹ መካከል ጅቡቲያዊው ኢሳም አብዱልሃኪም በሰጡት አስተያየት፤ ኢትዮጵያ የጀግንነት ታሪክ መፍለቂያ መሆኗን በሙዚየሙ ውስጥ ካየኋቸው ታሪኮች ተረድቻለሁ ብለዋል።

የዓድዋ ድል ኢትዮጵያውያን ሲተባበሩ ለየትኛውም ፈተና የማይበገሩ መሆናቸውን ያረጋገጠ ደማቅ አሻራ መሆኑንም ተናግረዋል።

ይህም ለሁሉም አፍሪካውያን የአይበገሬነትን ትምህርት የሚሰጥ ነው ብለዋል።

ከዛምቢያ የመጡት መሲ ችሉ በበኩላቸው፤ የዓድዋ ድል መታሰቢያ የጦርነት ድልን የሚዘክር ብቻ ሳይሆን በዚህ ዘመን ለልማት መትጋትን የሚያስተምርና ወኔ የሚያስታጥቅ እንደሆነ ጠቁመዋል።


አፍሪካውያን ከዓድዋ ደማቅ ታሪክ ተምረን ከተባበርን፤ ልክ እንደ ጦርነቱ ሁሉ ድህነትንም ድል ማድረግ እንችላለን ነው ያሉት።

በአዲስ አበባ የተመለከቱት ውበትና ዕድገትም ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ያላትን ምሳሌነት በተግባር ማሳየቱን ገልጸዋል።

በተመሳሳይ ሱዳናዊው እስማዔል አሊ፤ ዓድዋ ትክክለኛ የአመራር ብቃትና የሕዝብ ቁርጠኝነት የታየበት መሆኑን ገልጸዋል።


ኢትዮጵያ በጥንቱ ጀግንነቷ ብቻ ሳይሆን ዛሬም እያስመዘገበቻቸው በሚገኙ የልማት ስኬቶች ለአፍሪካ አርዓያ ሆና ቀጥላለች ብለዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መጥቷል

ጋምቤላ፤ ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መምጣቱን የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት...

Sep 4, 2026

በክልሉ ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት ተኪ ምርቶችን የማምረት ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል -ርዕሰ መስተዳድር አሻደሊ ሀሰን

አሶሳ፤ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ)፡- በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት ተኪ ምርቶችን የማምረት ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የክልሉ ርዕሰ ...

Sep 3, 2026

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሥራ ዕድል ፈጠራ በተከናወኑ ሥራዎች ውጤት ተገኝቷል

ሆሳዕና፤ ነሀሴ 5/2018 (ኢዜአ)፡-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ዜጎችን በሥራ ዕድል ተጠቃሚ ለማድረግ በተከናወኑ ሥራዎች ውጤት መመዝገ...

Aug 12, 2026

በሙስናና ሕገ ወጥ ድርጊት የተሰማሩ አካላትን ተጠያቂ የማድረግ ርምጃ ቀጣይነት ሊኖረው ይገባል

አዲስ አበባ፤ነሐሴ 5/2018 (ኢዜአ)፦የመንግሥት በሙስናና ሕገ ወጥ ድርጊት የተሰማሩ አካላትን በሕግ ተጠያቂ የማድረግ ርምጃ ቀጣይነት ሊኖረው እንደሚገባ ኢዜአ...

Aug 12, 2026