የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ህይወት እና ጉዞ

የአማራ ክልልን የግብርና ትራንስፎርሜሽን ለማሳካት ሁላችንም በቁጭት ልንሠራ ይገባል- ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

Apr 16, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 7/2018 (ኢዜአ)፦የአማራ ክልልን የግብርና ትራንስፎርሜሽን ለማሳካት ሁላችንም በቁጭት ልንሠራ ይገባል ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።

​የአማራ ክልልን የግብርና ዘርፍ ወደ ዘመናዊ፣ ምርታማና ተወዳዳሪነት ለማሸጋገር የሚያስችል የ10 ዓመት የግብርና ሽግግር ፍኖተ ካርታ ዛሬ ይፋ ተደርጓል።


የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህን ጨምሮ ከፍተኛ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ አመራሮች በመርሃ ግብሩ ላይ ተገኝተዋል።

​ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን በመድረኩ ላይ ባደረጉት ንግግር፤ የአማራ ክልል ሰፊ የተፈጥሮ ሀብት፣ የእንስሳት ሀብትና ለግብርና አመቺ የሆኑ መሬትና ውሃ ቢኖረውም እስካሁን ባለው ሂደት ዘርፉ ወደኋላ ቀርቶ መቆየቱን አውስተዋል።

ዛሬ ይፋ የሆነው ፍኖተ ካርታ በክልሉ ውስጥ ያለውን የልማትና የለውጥ ፍላጎት ማስተሳሰሩን ጠቅሰው፤ ዕቅዱ ማህበረሰቡንና አመራሩን ወደ አንድ የጋራ ዓላማ ማምጣት መቻሉን እንደ ትልቅ ስኬት አንስተዋል።

​ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም፤ ​እንደ ሀገር በአምስቱ የብዝኃ ዘርፎች የታቀዱ ሥራዎች ውጤት እያመጡ መሆኑን አንስተዋል።

በአማራ ክልል ​ከሸዋ ሮቢት እስከ ቆቦና ዋግ መስመር እጅግ ሰፊ የአትክልትና ፍራፍሬ ክላስተር የመሆን አቅም እንዳለው በማንሳት፤ ይህን ማልማት ከሀገር ያለፈ አበርክቶ ይኖረዋል ብለዋል።

​አርሶ አደሩ የሚጠቅመውን ነገር ካገኘ ለመተግበር ዝግጁ መሆኑን በማንሳት፤ የ10 ዓመቱን ፍኖተ ካርታ ወደ መሬት ማውረድ እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል።

​ለዚህም ሁላችንም በቁጭት መነሳት አለብን ነው ያሉት።


​የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አረጋ ከበደ በበኩላቸው፤ ፍኖተ ካርታው የዜጎችን ሕይወት ለመቀየርና የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ወሳኝ መሣሪያ መሆኑን ገልጸዋል።

ፍኖተ ካርታው አራት ዋና ዋና ምሰሶዎች ላይ ያተኮረ መሆኑን በማንሳት፤ የተሻሻሉ ዝርያዎችን፣ ግብዓቶችንና ቴክኖሎጂን በመጠቀም በሰብልና በእንስሳት ዘርፍ ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ፣ ​የእሴት ሰንሰለትና ኢንቨስትመንትን ማስፋት፣ ​የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃን በማጎልበት የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋም ግብርና መገንባት እንዲሁም ​ተቋማዊ የመፈጸም አቅምን ማሳደግ ናቸው ብለዋል።


​የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ መለስ መኮንን (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ሚኒስቴሩ የክልሎችን ጸጋ መሠረት ያደረገ የ10 ዓመት ስትራቴጂክ እቅድ ማዘጋጀቱን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መጥቷል

ጋምቤላ፤ ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መምጣቱን የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት...

Sep 4, 2026

በክልሉ ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት ተኪ ምርቶችን የማምረት ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል -ርዕሰ መስተዳድር አሻደሊ ሀሰን

አሶሳ፤ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ)፡- በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት ተኪ ምርቶችን የማምረት ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የክልሉ ርዕሰ ...

Sep 3, 2026

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሥራ ዕድል ፈጠራ በተከናወኑ ሥራዎች ውጤት ተገኝቷል

ሆሳዕና፤ ነሀሴ 5/2018 (ኢዜአ)፡-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ዜጎችን በሥራ ዕድል ተጠቃሚ ለማድረግ በተከናወኑ ሥራዎች ውጤት መመዝገ...

Aug 12, 2026

በሙስናና ሕገ ወጥ ድርጊት የተሰማሩ አካላትን ተጠያቂ የማድረግ ርምጃ ቀጣይነት ሊኖረው ይገባል

አዲስ አበባ፤ነሐሴ 5/2018 (ኢዜአ)፦የመንግሥት በሙስናና ሕገ ወጥ ድርጊት የተሰማሩ አካላትን በሕግ ተጠያቂ የማድረግ ርምጃ ቀጣይነት ሊኖረው እንደሚገባ ኢዜአ...

Aug 12, 2026