🔇Unmute
ሮቤ፤ ሚያዝያ 8/2018 (ኢዜአ)፡- በኦሮሚያ ክልል ባሌ ዞን በዘንድሮው የበልግ እርሻ ገበያ ተኮር ሰብሎችን ጨምሮ ከ246 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በተለያየ ሰብል ዘሮች መሸፈኑን የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት ገለፀ።
የጽህፈት ቤቱ ምክትል ኃላፊ አቶ ሙአዊያ ፉአድ ለኢዜአ እንዳሉት፣ በክልሉ የበልግ እርሻ በስፋት ከሚተገበርባቸው አካባቢዎች መካከል የባሌ ዞን በቀዳሚነት ይጠቀሳል።
በዞኑ የዘንድሮውን የበልግ እርሻ ለማሳካት በተደረገው ከፍተኛ ርብርብ ከ246 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በዘር መሸፈን መቻሉን ተናግረዋል።
በዞኑ የምግብ ፍጆታ ሰብሎችን ጨምሮ በአብዛኛው ለውጭ ገበያ እና ለኢንዱስትሪ ግብዓት የሚሆኑ የሰብል ምርቶች በስፋት እንደሚመረቱ አስታውቀዋል።
በተለይ አርሶ አደሩ በአጭር ጊዜ ውስጥ የምግብ ዋስትናውን እንዲያረጋግጥ ገበያ ተኮር ሰብሎችን ለማልማት የሚያስችለውን የቴክኒክ ድጋፍ በየደረጃው እየተደረገ መሆኑን አውስተዋል።
በዚህ ረገድ ዘንድሮ በበልግ ብቻ ከለማው መሬት ከ60 ሺህ ሄክታር የሚበልጠው ገበያ ተኮር በሆኑ ሰሊጥ፣ ማሾ፣ ቦሎቄና ለውዝ ሰብሎች መሸፈኑን ለአብነት ጠቅሰዋል።
በዓመቱ የበልግ እርሻ አተገባበር ወቅት ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የሚያስችሉ ቴክኖሎጂዎችን ለመተግበር ትኩረት ተሰጥቶ መሰራቱን ተናግረዋል።
በዚህም በምርት ዘመኑ ከለማው አጠቃላይ መሬት ውስጥ ከ80 በመቶ በላይ የሚሆነው በሙሉ ፓኬጅ በኩታ ገጠም ማልማት መቻሉን አስረድተዋል።
የበልግ እርሻውን ውጤታማ ለማድረግም ከ289 ሺህ ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበርያ ጥቅም ላይ መዋሉን አክለዋል።
እንደ ምክትል ኃላፊው ገለጻ ከበልግ የሰብል ልማት እንቅስቃሴም 8 ነጥብ 3 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ለመሰብሰብ ታቅዷል።
በዞኑ የበልግ እርሻ ወቅት ከመጋቢት አጋማሽ እስከ ነሐሴ መጨረሻ ያለውን ጊዜ እንደሚያጠቃልልም ለማወቅ ተችሏል።
ጋምቤላ፤ ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መምጣቱን የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት...
Sep 4, 2026
አሶሳ፤ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ)፡- በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት ተኪ ምርቶችን የማምረት ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የክልሉ ርዕሰ ...
Sep 3, 2026
ሆሳዕና፤ ነሀሴ 5/2018 (ኢዜአ)፡-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ዜጎችን በሥራ ዕድል ተጠቃሚ ለማድረግ በተከናወኑ ሥራዎች ውጤት መመዝገ...
Aug 12, 2026
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 5/2018 (ኢዜአ)፦የመንግሥት በሙስናና ሕገ ወጥ ድርጊት የተሰማሩ አካላትን በሕግ ተጠያቂ የማድረግ ርምጃ ቀጣይነት ሊኖረው እንደሚገባ ኢዜአ...
Aug 12, 2026