🔇Unmute
ሚያዝያ 8/2018 (ኢዜአ)፦ በሸገር ከተማ የህብረተሰቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት የበለጠ ለማሳደግ በተከናወኑ ተግባራት ውጤት መገኘቱን የከተማው አስተዳደር አስታወቀ።
በሸገር ከተማ ያለውን የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴን አስመልክቶ የመስክ ምልከታ እየተካሄደ ነው።
በመስክ ምልከታው ላይም የሸገር ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ጉዮ ገልገሎ እንደገለፁት፤ በሸገር ከተማ የህብረተሰቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት የበለጠ ለማሳደግ በተከናወኑ ተግባራት ውጤት ተገኝቷል።
ከተማዋ ከተመሰረተች በኋላ እየተከናወኑ ያሉ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴዎች የህብረተሰቡን ህይወት የቀየሩ ከመሆናቸውም በላይ ኢኮኖሚያዊ ሽግግርን እውን ከማድረግ አኳያ ውጤቶች ተመዝግበዋል።
ከለውጡ በኋላ በከተማዋ የምግብ ዋስትናን በማረጋገጥ፣ ዘመናዊ አገልግሎቶችን በማስፈን፣ ክህሎትን በማዳበር እና ሁለንተናዊ ብልጽግናን በማረጋገጥ ረገድ በተሰራው ስራ ውጤት መገኘቱን አክለዋል።

በኢንቨስትመንት ዘርፍ የሚስተዋሉ ችግሮችን ከመፍታትና አገልግሎት አሰጣጥን ከማዘመን ጎን ለጎን በከተማዋ የኢንቨስትመንት አማራጮችን በምርምር በመለየት መሰራቱን አመልክተዋል።
የአርሶ አደሮችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከ ከ1 ሺህ 300 በላይ አርሶ አደሮች ክህሎታቸውን ለማጠናከር የሚያስችል ስልጠና መሰጠቱን ተናግረዋል።
በዚህም መሰረት የኢንቨስትመንት እድገቱን ከተማው ከመመስረቱ በፊት ከነበረው በእጥፍ ማሳደግ መቻሉንም አስረድተዋል።
ባለፉት ሶስት ዓመታት የሀገር ውስጥና የውጪ ባለሀብቶች፣ አርሶ አደሮችና ሌሎችን ጨምሮ አጠቃላይ 1 ሺህ 504 ኢንቨስትመንቶች 4 ሺህ 493 ሄክታር መሬትን ማልማት ችለዋል ብለዋል።
ጋምቤላ፤ ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መምጣቱን የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት...
Sep 4, 2026
አሶሳ፤ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ)፡- በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት ተኪ ምርቶችን የማምረት ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የክልሉ ርዕሰ ...
Sep 3, 2026
ሆሳዕና፤ ነሀሴ 5/2018 (ኢዜአ)፡-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ዜጎችን በሥራ ዕድል ተጠቃሚ ለማድረግ በተከናወኑ ሥራዎች ውጤት መመዝገ...
Aug 12, 2026
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 5/2018 (ኢዜአ)፦የመንግሥት በሙስናና ሕገ ወጥ ድርጊት የተሰማሩ አካላትን በሕግ ተጠያቂ የማድረግ ርምጃ ቀጣይነት ሊኖረው እንደሚገባ ኢዜአ...
Aug 12, 2026