የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ህይወት እና ጉዞ

መንግሥት ለኢንዱስትሪው ዘርፍ በሰጠው ልዩ ትኩረት የማምረት አቅማችን እየጨመረ ነው - አምራች ኢንዱስትሪዎች

Apr 21, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 13/2018 (ኢዜአ)፦መንግሥት ለኢንዱስትሪው ዘርፍ በሰጠው ልዩ ትኩረት የማምረት አቅማቸው እየጨመረ መሆኑን አምራች ኢንዱስትሪዎች ገለጹ።

የሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያው የማምረት አቅምን ከማሳደግ ባሻገር የወጪ ንግድን በማስፋፋትና የውጭ ምንዛሬ ገቢ እንዲጨምር በማድረግ በኩል አስተዋጽኦ እያደረገ መሆኑንም ጠቁመዋል።

ከሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ዋና ትኩረቶች መካከል የአምራች ኢንዱስትሪውን አቅም በማሳደግ፣ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ምርቶች መተካትና የውጭ ምንዛሬን ማዳን ነው።

ይህ ስትራቴጂ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ይወጣባቸው የነበሩ ምርቶች በሀገር ውስጥ እንዲመረቱ በማስቻል ረገድ ተጨባጭ ውጤቶችን እያስመዘገበ ይገኛል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) “የሉዓላዊነት ልብ” በሚል ርዕሰ ጉዳይ ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ ኢትዮጵያ ባለፉት ጥቂት ዓመታት ያጋጠሟትን ፈተናዎች ወደ ዕድል በመቀየር በኢንዱስትሪው ዘርፍ ተጨባጭ ለውጥ እያስመዘገበች ነው ብለዋል፡፡


በዚህ የለውጥ እርምጃ ማግስት 8 ሺህ ገደማ የነበሩት አነስተኛና መካከለኛ ኢንዱስትሪዎች፣ በአሁኑ ወቅት ከ26 ሺህ በላይ መድረሳቸውን ገልጸዋል።

ኢዜአ ያነጋገራቸው አምራቾች እንደገለጹት፤ መንግስት ለዘርፉ በሰጠው ልዩ ትኩረት የማምረት አቅማቸው በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መጥቷል።

ምርቶችን በማምረት ወደ ውጭ ገበያ ከመላክ ባለፈ የገቢ ምርቶችን በማስቀረት ረገድም ትልቅ ስኬት እያገኙ መሆኑን ጠቁመዋል።

በሁዋጃን ልዩ ኢኮኖሚክ ዞን የጎበዝ የፀሐይ ኃይል ሶላር ሴል ማምረቻ ሥራ አስኪያጅ በረከት ኃይሉ እንደገለጹት፤ ድርጅታቸው ምርቶቹን ወደ አሜሪካ፣ ካናዳ፣ ቬትናም እና መካከለኛው ምሥራቅ ሀገራት እየላከ ነው፡፡ በዚህም ከ600 በላይ ለሚሆኑ ዜጎችም የሥራ ዕድል መፍጠሩን ተናግረዋል።


በመንግስት በኩል የሚደረገው ድጋፍ የማምረት አቅማቸውን እንዲያድግ ላቅ ያለ አስተዋጽኦ ማድረጉንም አክለዋል።

የዳቼ የምግብ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ ፕላንት ማኔጀር ዐቢይ በቀለ በበኩላቸው፤ በመንግሥት በየጊዜው በሚደረግላቸው ድጋፍና ክትትል ምርቶቻቸውን በጥራትና በፍጥነት ለገበያ ማቅረብ እንዳስቻላቸው ገልጸዋል።


በአሁኑ ወቅት በአራት ፋብሪካዎች 46 ዓይነት የታሸጉ ምግቦችን በማምረት ለሀገር ውስጥና ለውጭ ገበያ በተመጣጣኝ ዋጋ እያቀረቡ እንደሚገኙ አንስተዋል።

የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ ታረቀኝ ቡሉልታ እንደገለጹት፤ መንግሥት ለማኑፋክቸሪንግ ዘርፉ የሰጠው ትኩረት የምርትና ምርታማነት ለውጥ እንዲመጣ አድርጓል።


ከዚህ ቀደም አምራች ኢንዱስትሪዎች ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ይወጣባቸው የነበሩ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በመተካትና የውጭ ምንዛሬ ግኝት እንዲኖር በማስቻል ትልቅ ውጤት እያመጡ ነው ብለዋል።

በቀጣይም መንግሥት የፋይናንስ አቅርቦትን ጨምሮ ሌሎች አስፈላጊ ድጋፎችን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ሚኒስትር ዴኤታው አረጋግጠዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መጥቷል

ጋምቤላ፤ ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መምጣቱን የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት...

Sep 4, 2026

በክልሉ ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት ተኪ ምርቶችን የማምረት ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል -ርዕሰ መስተዳድር አሻደሊ ሀሰን

አሶሳ፤ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ)፡- በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት ተኪ ምርቶችን የማምረት ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የክልሉ ርዕሰ ...

Sep 3, 2026

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሥራ ዕድል ፈጠራ በተከናወኑ ሥራዎች ውጤት ተገኝቷል

ሆሳዕና፤ ነሀሴ 5/2018 (ኢዜአ)፡-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ዜጎችን በሥራ ዕድል ተጠቃሚ ለማድረግ በተከናወኑ ሥራዎች ውጤት መመዝገ...

Aug 12, 2026

በሙስናና ሕገ ወጥ ድርጊት የተሰማሩ አካላትን ተጠያቂ የማድረግ ርምጃ ቀጣይነት ሊኖረው ይገባል

አዲስ አበባ፤ነሐሴ 5/2018 (ኢዜአ)፦የመንግሥት በሙስናና ሕገ ወጥ ድርጊት የተሰማሩ አካላትን በሕግ ተጠያቂ የማድረግ ርምጃ ቀጣይነት ሊኖረው እንደሚገባ ኢዜአ...

Aug 12, 2026