🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 16/2018 (ኢዜአ)፡- በሳይንስና ፈጠራ የበለፀገ ትውልድ መገንባት ለሀገር ብልጽግና እና ሁለንተናዊ እድገት መሰረት በመሆኑ የከተማ አስተዳደሩ ለዘርፉ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መሆኑን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ “በሳይንስና ፈጠራ የተካነ ትውልድ ለተምሳሌታዊ ሀገር” በሚል መሪ ሐሳብ ያዘጋጀው 11ኛው የሳይንስና የፈጠራ ሥራ ዐውደ-ርዕይ በአራዳ ፓርክ እየተካሄደ ይገኛል።
በዚህ መድረክ ላይ በርካታ ተማሪዎችና መምህራን የፈጠራ ሥራዎቻቸውን ለዕይታ አቅርበዋል።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ዐውደ-ርዕዩን በጎበኙበት ወቅት እንደተናገሩት፤ መድረኩ ተማሪዎችና መምህራን የፈጠራ ሥራዎቻቸውን የሚያስተዋውቁበትና እርስበርስ የፈጠራ ሐሳባቸውን የሚለዋወጡበት ወሳኝ ድልድይ ነው።
በዐውደ-ርዕዩ የቀረቡት የፈጠራ ውጤቶች ከተማዋን ወደ ስማርት ሲቲ ለመቀየር እየተደረገ ላለው ጥረት ትልቅ ተስፋ የሚሰጥና የምሥራች መሆናቸውንም ገልጸዋል።
ማንኛውም የፈጠራ ሥራ ውጤት በትንሽ ጅማሮ የሚነሳ መሆኑን ጠቅሰው፤ መንግሥት እነዚህን የፈጠራ ሥራዎች በፋይናንስና በሙያ በመደገፍ ወደ ላቀ ደረጃ እንዲሸጋገሩ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል።
በአሁኑ ወቅት በከተማዋ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ሥራዎች በሳይንስና በቴክኖሎጂ የታገዙ እንዲሆኑ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ መሆኑንም አክለዋል።
ዐውደ-ርዕዩ የፈጠራ ውጤቶችን ወደ ተግባር በመቀየር የሀገርን ብልጽግና ለማረጋገጥ የሚደረገውን ጉዞ እንደሚያፋጥን ታምኖበታል ነው ያሉት።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዘላለም ሙላቱ (ዶ/ር) እንደገለጹት መድረኩ ተማሪዎች ዕውቀት የሚያገኙበት ብቻ ሳይሆን፤ የጥበብ ባለቤት መሆናቸውን በተግባር የሚያሳዩበት ነው።
ባለፉት ዓመታት ጥቂት ተማሪዎች ይሳተፉበት የነበረው የምርምርና ፈጠራ ሥራ ዛሬ የብዙዎች ባህልና ጉጉት መሆኑን መድረኩ ማረጋገጡንም ጠቁመዋል።
ይህ የፈጠራ እድገት በከተማዋ በስፋት ከሚከናወኑ መሠረተ-ሰፊ የልማት ሥራዎችና ፕሮጀክቶች ጋር በጥብቅ የተሳሰረ መሆኑንም አብራርተዋል።

የቅድመ-1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በዓይነትና በጥራት መስፋፋታቸው ሕፃናት በራስ የመተማመን ስሜት ትምህርታቸውን እንዲጀምሩና ለሳይንስ ሥራዎች ጠንካራ መሠረት እንዲጥሉ እያደረገ ነው ብለዋል።
ጋምቤላ፤ ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መምጣቱን የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት...
Sep 4, 2026
አሶሳ፤ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ)፡- በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት ተኪ ምርቶችን የማምረት ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የክልሉ ርዕሰ ...
Sep 3, 2026
ሆሳዕና፤ ነሀሴ 5/2018 (ኢዜአ)፡-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ዜጎችን በሥራ ዕድል ተጠቃሚ ለማድረግ በተከናወኑ ሥራዎች ውጤት መመዝገ...
Aug 12, 2026
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 5/2018 (ኢዜአ)፦የመንግሥት በሙስናና ሕገ ወጥ ድርጊት የተሰማሩ አካላትን በሕግ ተጠያቂ የማድረግ ርምጃ ቀጣይነት ሊኖረው እንደሚገባ ኢዜአ...
Aug 12, 2026