🔇Unmute
ሆሳዕና፤ ሰኔ 9/2018 (ኢዜአ)፡-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን በማስፋት ለህብረተሰቡ ዘመናዊና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት የተጀመሩ ተግባራት ይጠናከራሉ ሲሉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) ገለጹ።
የሆሳዕና ከተማ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) ተመርቆ ሥራ ጀምሯል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በዚህ ወቅት እንዳሉት በክልሉ የማዕከሉን ተደራሽነት በማስፋት መንግስታዊ አገልግሎቶችን በጥራትና በፍጥነት ለመስጠት የተጀመሩ ተግባራት ይጠናከራሉ።
መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የተለያዩ አገልግሎቶችን በአንድ ማዕከል በማቅረብ የማህበረሰቡን እንግልት በማስቀረት በኩል ያለው አስተዋጽኦ ጉልህ መሆኑንም ተናግረዋል።
ማዕከሉ ዜጎች መንግስታዊ አገልግሎቶችን ለማግኘት ወደተለያዩ ቢሮዎች የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ ከማስቀረት በተጨማሪ ለከተሞች ፈጣን እድገት መረጋገጥ በጎ ተፅዕኖ እንዳለውም አመልክተዋል።

በመሆኑም በክልሉ በሚገኙ የተለያዩ ከተሞች ማዕከላቱ ተገንብተው ለአገልግሎት እንዲበቁ በክልሉ መንግስት በኩል ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
የክልሉ መንግስት ከማህበረሰቡ ለተነሱ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት የጀመረውን ተግባር አጠናክሮ ይቀጥላልም ብለዋል።
የሀድያ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማቲዎስ አኒዮ በበኩላቸው እንዳሉት፤ በዞኑ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ በርካታ የልማት ሥራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ።

መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ብልሹ አሰራርን በማስቀረት ለማህበረሰቡ ፈጣን፣ ዘመናዊና ከሙስና የጸዳ አገልግሎት ለመስጠት ጠቀሜታው የጎላ መሆኑንም ተናግረዋል።
ዛሬ ተመርቆ ለአገልግሎት የበቃው የሆሳዕና ከተማ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ገቢን በአግባቡ በመሰብሰብ ለህዝብ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት ጉልህ ጠቀሜታ እንዳለውም ገልጸዋል።
የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ሳሙኤል ሽጉጤም መንግስት የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ዘርፈ ብዙ ተግባራት እያከናወነ ይገኛል ብለዋል።

በከተማ አስተዳደሩ ከ220 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ተደርጎበት ዛሬ የተመረቀው መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የተለያዩ አገልግሎቶችን በአንድ ቦታ በማቅረብ የማህበረሰቡን እንግልት እንደሚያስቀር ገልጸዋል።
በምረቃ መርሐ ግብሩ ላይ የክልል፣ የሀድያ ዞን እና የሆሳዕና ከተማ ከፍተኛ አመራሮችና ነዋሪዎች ተሳትፈዋል።
ጋምቤላ፤ ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መምጣቱን የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት...
Sep 4, 2026
አሶሳ፤ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ)፡- በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት ተኪ ምርቶችን የማምረት ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የክልሉ ርዕሰ ...
Sep 3, 2026
ሆሳዕና፤ ነሀሴ 5/2018 (ኢዜአ)፡-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ዜጎችን በሥራ ዕድል ተጠቃሚ ለማድረግ በተከናወኑ ሥራዎች ውጤት መመዝገ...
Aug 12, 2026
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 5/2018 (ኢዜአ)፦የመንግሥት በሙስናና ሕገ ወጥ ድርጊት የተሰማሩ አካላትን በሕግ ተጠያቂ የማድረግ ርምጃ ቀጣይነት ሊኖረው እንደሚገባ ኢዜአ...
Aug 12, 2026