የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ህይወት እና ጉዞ

የኢትዮጵያን የዲጂታል ኢኮኖሚ የሚያፋጥኑ ውጤታማ የቴክኖሎጂ አሰራሮች ተግባራዊ እየተደረጉ ነው 

Jun 17, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 9/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያን የዲጂታል ኢኮኖሚ ሥርዓት የሚያፋጥኑ ውጤታማ የቴክኖሎጂ አሰራሮች ተግባራዊ እየተደረጉ መሆኑን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) ገለጹ።

የኢትዮጵያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት ዘመናዊ የቤተ መጻሕፍት ሥርዓት መዘርጋት የሚያስችለውን የጽሑፍ ሃብቶችን ወደ ዲጂታል የመቀየር ሥራ በይፋ ጀምሯል።


የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር)፤ ዘመናዊት ኢትዮጵያን ለመገንባትና የተሟላ ዲጂታል ኢኮኖሚ እውን ለማድረግ በርካታ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ገልጸዋል።

የዲጂታል ሥነ-ምህዳርን መገንባት፣ መሰረተ ልማትን ማሟላትና ምቹ ፖሊሲ በመንደፍ ከመንግሥታዊና መንግሥታዊ ካልሆኑ ተቋማት ጋር በቅንጅት መስራትን ያጠቃልላል።

የኢትዮጵያን የዲጂታል ኢኮኖሚ ሥርዓት የሚያፋጥኑ ውጤታማ የቴክኖሎጂ አሰራሮች ተግባራዊ እየተደረጉ መሆኑን ተናግረዋል።

በዋናነት ሀገሪቱን ወደ ዘመናዊ የኢኮኖሚ ስርዓት በማስገባት ተከታታይነት ያለው ዕድገት ለማስመዝገብ ያለመ እንደሆነም ጠቁመዋል።

ለአብነትም ከወረቀት አሠራር ወደ ዲጂታል የመሸጋገር እና የታሪክ ሀብቶችን ወደ ዲጂታል ቋት በማስገባት ለቀጣይ ትውልድ የማስተላለፍ ሥራ እየተሠራ ይገኛል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት የጀመረው ጉዞ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ አካል ሲሆን፣ በቀጣይ በሁሉም ዘርፎች ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቅሰዋል።

በቤተ መጻሕፍቱ የሚገኙ የሀገር ሀብቶችን ጠብቆና ተንከባክቦ ለቀጣይ ትውልድ ለማሻገር የዲጂታላይዜሽን ሥራው ወሳኝ መሆኑን ሚኒስትሩ አብራርተዋል።

የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ በበኩላቸው፤ የኢትዮጵያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት የሀገር ታሪክ፣ ባህል እና ማንነት የተሰነደበት ማዕከል መሆኑን ገልጸዋል።


ይህ የተጀመረው የዲጂታላይዜሽን ሥራ ታሪካችንን ለቀጣይ ትውልድ በታማኝነት ለማስተላለፍና ማንኛውም ሰው የሚፈልገውን መረጃ በቀላሉ እንዲያገኝ ያስችላል ብለዋል።

ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት የኢትዮጵያውያንን ባህል፣ ታሪክ፣ ትውስታዎች፣ ፍልስፍናዎች በተገቢ መንገድ ሰንዶ የያዘ ተቋም ነው ሲሉም ተናግረዋል።

እዚህ ተቋም ላይ ኢንቨስት የምናደርጋቸው ሀብቶች በሙሉ ለሚቀጥለው ትውልድ የምትሆን ኢትዮጵያ ግንባታ ሂደት ላይ ትልቅ አበርክቶና አስተዋጽኦ ያለው ስራ ነው ብለዋል።

የኢትዮጵያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሰርፀ ፍሬስብሐት እንደገለጹት፤ አገልግሎቱ ከ83 ዓመታት በፊት ጀምሮ መረጃዎችን በመሰነድና በማስቀመጥ ለትውልድ እያስተላለፈ የሚገኝ ተቋም ነው።


የጽሑፍ ሀብቶችን ወደ ዲጂታል የመቀየር ሥራ የኢትዮጵያን የመረጃ ሃብቶች በማሰባሰብና በማደራጀት ለቀጣይ ትውልድ ለማስተላለፍ ዕድል ይፈጥራል ነው ያሉት።

በወረቀት ላይ የሰፈሩ ታሪካዊ መረጃዎች ከጊዜ ብዛትና ከአያያዝ ጉድለት እንዳይጠፉና እንዳይበላሹ ዘላቂ ጥበቃ ለማድረግ እንደሚያስችልም ተናግረዋል።

በመጀመሪያው ምዕራፍ 20 ሚሊየን ገጾችን ወደ ዲጂታል የመቀየር ስራ እንደሚከናወን በመድረኩ ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መጥቷል

ጋምቤላ፤ ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መምጣቱን የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት...

Sep 4, 2026

በክልሉ ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት ተኪ ምርቶችን የማምረት ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል -ርዕሰ መስተዳድር አሻደሊ ሀሰን

አሶሳ፤ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ)፡- በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት ተኪ ምርቶችን የማምረት ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የክልሉ ርዕሰ ...

Sep 3, 2026

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሥራ ዕድል ፈጠራ በተከናወኑ ሥራዎች ውጤት ተገኝቷል

ሆሳዕና፤ ነሀሴ 5/2018 (ኢዜአ)፡-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ዜጎችን በሥራ ዕድል ተጠቃሚ ለማድረግ በተከናወኑ ሥራዎች ውጤት መመዝገ...

Aug 12, 2026

በሙስናና ሕገ ወጥ ድርጊት የተሰማሩ አካላትን ተጠያቂ የማድረግ ርምጃ ቀጣይነት ሊኖረው ይገባል

አዲስ አበባ፤ነሐሴ 5/2018 (ኢዜአ)፦የመንግሥት በሙስናና ሕገ ወጥ ድርጊት የተሰማሩ አካላትን በሕግ ተጠያቂ የማድረግ ርምጃ ቀጣይነት ሊኖረው እንደሚገባ ኢዜአ...

Aug 12, 2026