የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ህይወት እና ጉዞ

ማዕከሉ በምርምር ያወጣቸውንና ለቆላማ አካባቢዎች ተስማሚ የሆኑ የቡና ዝርያዎችን እያስፋፋ ነው

Jun 17, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ቴፒ፤ ሰኔ 9/2018 (ኢዜአ)፡-የቴፒ ግብርና ምርምር ማዕከል በምርምር ያወጣቸውንና ለቆላማ አካባቢዎች ተስማሚ የሆኑ የቡና ዝርያዎችን እያስፋፋ መሆኑን አስታወቀ።

የምርምር ማዕከሉ በሸካ ዞን የኪ ወረዳ አላሞ ቀበሌ ላይ በአርሶ አደሮች ማሳ ያላመዳቸውን የቡና ተክሎች ምልከታና የልምድ ልውውጥ አድርጓል።

በማዕከሉ የሰብል ምርምር ሥራ ሂደት አስተባባሪ ሸሐሚል አሎ እንደገለጹት፤ ማዕከሉ ከቡና ልማት ተጠቃሚነትን ለማሳደግ በምርምር ያወጣቸውን የተሻሻሉ የቡና ዝርያዎች በአርሶ አደሮች ማሳ ላይ የማላመድ ሥራ እየሰራ ነው።


በምርምር የተገኙት ውጤታማ የቡና ዝርያዎችም በአጭር ጊዜ ምርት የሚሰጡና ለቆላማ አየር ንብረት ተስማሚ መሆናቸውን ተናግረዋል።

የቡና ዝርያዎቹ በምርታማነታቸው የተረጋገጡ ከመሆናቸውም በላይ አርሶ አደሮች በጥራት በማምረት በገበያ ተወዳዳሪ የሚሆኑበትን እቅም እንደሚያጠናክሩም ጠቁመዋል።

እነዚህ በምርምር የተገኙ "K-1"፣ "K-2" እና " I-2" የተሰኙ የቡና ዝርያዎች ምርታማነታቸው ከነባሩ ዝርያ በእጥፍ ከፍ ያሉ መሆኑን አስተባባሪው ገልጸዋል።

የቡናው ዝርያ ውጤታማነት በማሳ ላይ በመረጋገጡ ወደ ሌሎች የአርሶ አደሮች ማሳ ለማስፋፋት ታቅዶ እንቅስቃሴ መጀመሩንም ተናግረዋል።

በሸካ ዞን የየኪ ወረዳ ግብርና ጽህፈት ቤት ባለሙያ አቶ ፍስሐ ግዛው፤ በወረዳው የቡና አመራረትን በማዘመን የውጭ ምንዛሬ አቅምን ከፍ ለማድረግ ከምርምር ማዕከሉ ጋር በትብብር እየተሰራ መሆኑን አመልክተዋል።


በወረዳው የአላሞ ቀበሌ አርሶ አደር ይንገሥ ጌታቸው ከምርምር ማዕከሉ የወሰዱትን የቡና ዝርያዎች በአምስት ሔክታር መሬታቸው ላይ እያለሙ መሆናቸውን ገልጸዋል።

የቡና ዝርያው በፍጥነት አድጎ ምርት ከመስጠቱ ባለፈ ለእንክብካቤና ለለቀማ ምቹ በመሆኑ ሥራውን ለማስፋፋት ከሚያደርጉት ጥረት ባለፈ ልምዳቸውን ለሌሎች አርሶ አደሮች እያጋሩ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ከማዕከሉ የተረከቡት የተሻሻለ የቡና ዝርያ ምርታማ በመሆኑ ነባሮቹን የቡና ማሳዎች በአዲስ እየተኩ መሆናቸውን የገለጹት ደግሞ አርሶ አደር ብርሃኑ ጌታቸው ናቸው።


በተሻሻለ የቡና ማሳ ልማት ላይ ልምድ የወሰዱ አርሶ አደሮች በበኩላቸው እንዳሉት፤ በመስክ ምልክታው በቀጣይ የቡና ምርትና ምርታማነታቸውን ለማሳደግ የሚያስችል ተሞክሮ አግኝተዋል።

ይህን ልምድ በመውሰድ ከዘንድሮ ክረምት ጀምሮ የተሻሻሉ የቡና ዝርያ ችግኞችን ከምርምር ማዕከሉ በመውሰድ ለመትከል መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መጥቷል

ጋምቤላ፤ ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መምጣቱን የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት...

Sep 4, 2026

በክልሉ ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት ተኪ ምርቶችን የማምረት ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል -ርዕሰ መስተዳድር አሻደሊ ሀሰን

አሶሳ፤ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ)፡- በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት ተኪ ምርቶችን የማምረት ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የክልሉ ርዕሰ ...

Sep 3, 2026

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሥራ ዕድል ፈጠራ በተከናወኑ ሥራዎች ውጤት ተገኝቷል

ሆሳዕና፤ ነሀሴ 5/2018 (ኢዜአ)፡-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ዜጎችን በሥራ ዕድል ተጠቃሚ ለማድረግ በተከናወኑ ሥራዎች ውጤት መመዝገ...

Aug 12, 2026

በሙስናና ሕገ ወጥ ድርጊት የተሰማሩ አካላትን ተጠያቂ የማድረግ ርምጃ ቀጣይነት ሊኖረው ይገባል

አዲስ አበባ፤ነሐሴ 5/2018 (ኢዜአ)፦የመንግሥት በሙስናና ሕገ ወጥ ድርጊት የተሰማሩ አካላትን በሕግ ተጠያቂ የማድረግ ርምጃ ቀጣይነት ሊኖረው እንደሚገባ ኢዜአ...

Aug 12, 2026