🔇Unmute
አዳማ ፤ ሰኔ 17/2018 (ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል ምእራብ ወለጋ እና ጅማ ዞኖች የቡና ልማትን ከአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ጋር ለማስተሳሰር የተከናወኑ ተግባራት ውጤት ማስገኘታቸውን የየዞኖቹ ግብርና ጽህፈት ቤቶች አስታወቁ።
የጅማ ዞን ግብርና ጽህፈት ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ ሚፍታህ ገሊ ለኢዜአ እንዳሉት፤ በዞኑ ባሉ 21 ወረዳዎች የቡና ጥራትና ምርታማነትን ለማሳደግ የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወነ ይገኛል።

የቡና ልማቱን ከአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ጋር ለማስተሳሰር እየተከናወኑ ባሉ ተግባራት ውጤት መገኘቱን ገልጸዋል።
ከዚህ ውስጥም በቡና ልማት ስራ ላይ የተሳተፉ ከ400 ሺህ በላይ አርሶ አደሮች ምርታማነታቸውን በሄክታር በአማካይ ከ11 እስከ 13 ኩንታል ለማሳደግ መቻላቸውን አብራርተዋል።
በዞኑ እየተገባደደ ባለው በጀት ዓመት 300 ሺህ ቶን ቡና ተመርቶ ለማእከላዊ ገበያ እና ለሀገር ውሰጥ ፍጆታ እየቀረበ እንደሚገኝ አመልክተዋል።
በተያዘው ዓመት የቡና ልማቱን ከአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ጋር በማስተሳሰር ይበልጥ ለማስፋፋት እንዲቻል ከ700 ሚሊዮን በላይ የቡና ችግኞች ለተከላ መዘጋጀታቸውን አስታውቀዋል።
በአሁኑ ወቅትም በዞኑ 513 ቀበሌዎች በመተከል ላይ ባሉት የቡና ችግኞችም 90 ሺህ ሄክታር አዲስ መሬት የሚለማ እና ይህም በዘርፉ የነበረውን ሽፋን እንደሚያሳድግም ገልጸዋል።
የምእራብ ወለጋ ዞን የግብርና ጽህፈት ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ ቡላ ደመራ፤ በዞኑ ቡናን በክላስተር የማልማት ኢንሼቲቭ ተግባራዊ መደረጉ አርሶ አደሩ ከዘርፉ የተሻለ ምርት እንዲያገኝ እያደረገ መሆኑንም አስረድተዋል።

በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብርም 32 ሚሊዮን የተሻሻሉ የቡና ችግኞች የሚተከሉ ሲሆን በሄክታር ከ 2 ሺህ 500 እስከ 5 ሺህ ችግኝ እንደሚተከልም ነው የተናገሩት።
በዚሁ ወቅት 64 ሺህ 551 ሄክታር አዲስ መሬት እንደሚለማ ገልጸው አርሶ አደሩ ያረጁ ቡናዎችንም በመጎንደል በአዲስ እንዲተካ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን አመልክተዋል።
የኦሮሚያ ክልል ግብርና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ መሀመድ ሳኒ በበኩላቸው፤ በክልሉ የሚካሔዱ የቡና ልማት ስራዎችን ለማስፋፋት የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ ነው ብለዋል።

ይህንን ለማጠናከርም በዘንድሮ አረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ከ 2 ነጥብ 5 ቢሊዮን በላይ የቡና ችግኝ ይተከላል ብለዋል።
ጋምቤላ፤ ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መምጣቱን የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት...
Sep 4, 2026
አሶሳ፤ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ)፡- በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት ተኪ ምርቶችን የማምረት ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የክልሉ ርዕሰ ...
Sep 3, 2026
ሆሳዕና፤ ነሀሴ 5/2018 (ኢዜአ)፡-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ዜጎችን በሥራ ዕድል ተጠቃሚ ለማድረግ በተከናወኑ ሥራዎች ውጤት መመዝገ...
Aug 12, 2026
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 5/2018 (ኢዜአ)፦የመንግሥት በሙስናና ሕገ ወጥ ድርጊት የተሰማሩ አካላትን በሕግ ተጠያቂ የማድረግ ርምጃ ቀጣይነት ሊኖረው እንደሚገባ ኢዜአ...
Aug 12, 2026