የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ህይወት እና ጉዞ

የኮሪደር ልማቱ የሀዋሳ ከተማን ፀጋዎች አጉልቶ ያሳየ ነው - ከንቲባ ጥራቱ በየነ

Jun 25, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

‎‎ሀዋሳ ፤ ሰኔ 17/2018 (ኢዜአ)፦የሀዋሳ ከተማ የኮሪደር ልማት ፀጋዎቿን አጉልቶ ያሳየ መሆኑን የከተማዋ ከንቲባ ጥራቱ በየነ ገለፁ፡፡

በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የተጀመረው የኮሪደር ልማት የከተሞችን ገጽታ ከመቀየር ባለፈ የመልማት አቅማቸውን ወደ ተግባር በመለወጥ ለትውልድ የሚሻገር ሰው ተኮር የልማት ውጤቶች እንዲመዘገቡ እያደረገ ነው።

የዚሁ አካል የሆነው የሀዋሳ ከተማ የኮሪደር ልማትም ተፈጥሯዊ ሀብቶቿን በማልማት ፈጣን ዕድገት እንድታስመዘግብ አድርጓል።


የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ አቶ ጥራቱ በየነ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደገለጹት፤ የከተማዋ የኮሪደር ልማት በተፈጥሮ ከታደለቻቸው ሐይቅና ተራሮች ጋር የተሳሰረና በፕላን ላይ የተመሰረተ ሰው ተኮር ልማት እንዲተገበር አግዟል።

ልማቱ ሰፋፊ መንገዶችና አረንጓዴ ሥፍራዎች እንዲስፋፉ በማድረግ በከተማዋ የጎብኚዎች ቁጥር እንዲጨምርና ለሥራና ለኑሮ ተመራጭ ከተማ እንድትሆን ማድረጉን ተናግረዋል፡፡

በኮሪደር ልማቱ የተገነቡ የእግረኛና ብስክሌት መንገዶች ሀዋሳ ቀድሞ የነበራትን የብስክሌት ባህል ዳግም እንዲያንሰራራ ያደረገ መሆኑን ከንቲባው ጠቁመዋል፡፡

የሕፃናት መጫወቻዎች፣ የስፖርት ማዘውተሪያዎች፣ የብስክሌት መንገዶች፣ የተሽከርካሪ ማቆሚያዎች፣ የታክሲ መጫኛና ማውረጃዎች እንዲሁም ሌሎች ከተማዋን ዘመናዊነት የሚያላብሱ ሥራዎች በኮሪደር ልማቱ መካተታቸውንም ገልጸዋል፡፡

ልማቱን ከቱሪስት መዳረሻ ተፈጥሯዊ መስህቦቿ ጋር እንዲተሳሰር ለማድረግም የሐይቅ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክት ግንባታ ሥራ መጀመሩን ጠቅሰዋል፡፡


የሀዋሳ ከተማ ለመዝናኛ ተመራጭ የሚያደርጋት ተፈጥሯዊና ሰውሰራሽ መስህቦች ባለቤት እንደሆነች የተናገሩት ደግሞ የከተማዋ ነዋሪ የሆኑት ወይዘሮ ወጋየሁ ሰለሞን ናቸው።

አሁን ላይ እየተሰሩ ያሉ የሕፃናት መዝናኛ ሥፍራዎችም ይህን አቅሟን የሚያሳድጉ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡


ቀደም ሲል የቆሸሹ አካባባዎችና ለወንጀል መፈጸሚያ ምቹ የነበሩ ቦታዎች ጭምር ወደ ልማት መግባታቸው የከተማዋን እድገት ለመፋጠን ካላቸው ፋይዳ ባለፈ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን እያሳደጉ ነው ብለዋል።

የኮሪደር ልማቱ ቀደም ሲል በከተማዋ የነበረውን ጠባብ የእግረኛ መንገድ ማስቀረቱ የሚበረታታ ነው ያሉት ደግሞ አቶ ይሄይስ ወንድሙ የተባሉ የሀዋሳ ከተማ ነዋሪ ናቸው።


ይህም በእግር በመንቀሳቀስ ጤናን ለመጠበቅና የከተማዋን የተሽከርካሪ እንቅስቃሴ ለማሳለጥ ማገዙን ጠቁመዋል።

ከዚህ በተጨማሪ የዜጎችን ጤና ለመጠበቅና በከተማዋ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎች እንዲነቃቁ ማገዙን አስረድተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መጥቷል

ጋምቤላ፤ ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መምጣቱን የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት...

Sep 4, 2026

በክልሉ ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት ተኪ ምርቶችን የማምረት ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል -ርዕሰ መስተዳድር አሻደሊ ሀሰን

አሶሳ፤ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ)፡- በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት ተኪ ምርቶችን የማምረት ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የክልሉ ርዕሰ ...

Sep 3, 2026

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሥራ ዕድል ፈጠራ በተከናወኑ ሥራዎች ውጤት ተገኝቷል

ሆሳዕና፤ ነሀሴ 5/2018 (ኢዜአ)፡-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ዜጎችን በሥራ ዕድል ተጠቃሚ ለማድረግ በተከናወኑ ሥራዎች ውጤት መመዝገ...

Aug 12, 2026

በሙስናና ሕገ ወጥ ድርጊት የተሰማሩ አካላትን ተጠያቂ የማድረግ ርምጃ ቀጣይነት ሊኖረው ይገባል

አዲስ አበባ፤ነሐሴ 5/2018 (ኢዜአ)፦የመንግሥት በሙስናና ሕገ ወጥ ድርጊት የተሰማሩ አካላትን በሕግ ተጠያቂ የማድረግ ርምጃ ቀጣይነት ሊኖረው እንደሚገባ ኢዜአ...

Aug 12, 2026