🔇Unmute
ወልቂጤ፤ ሰኔ 18/2018 (ኢዜአ)፦ ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ከመማር ማስተማር ሥራው በተጓዳኝ የአካባቢውን ማህበረሰብ ኑሮ ለማሻሻል የሚያግዙ የምርምር ሥራዎችን እያከናወነ መሆኑን አስታወቀ።
ዩኒቨርሲቲው በተለያዩ የትምህርት መስኮች በመጀመሪያና በሁለተኛ ዲግሪ ያሰለጠናቸውን 363 ተማሪዎች ዛሬ አስመርቋል።

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት አብዱልሙህሲን ሃሰን (ዶ/ር) በምረቃ ሥነ ስርዓቱ ላይ እንደገለፁት፤ ዩኒቨርሲቲው የኢንዱስትሪውን ችግር በቅርበት ተገንዝቦ የሚፈታ አምራች የሰው ሀይል እያፈራ ነው።
ከመማር ማስተማሩ ሥራው በተጓዳኝ የአካባቢውን ማህበረሰብ ኑሮ ለማሻሻል የሚያግዙ የምርምር ሥራዎችን እያከናወነ መሆኑን ጠቁመው፣ የጀፎረን ሀገር በቀል እውቀት በዓለም ቅርስነት ለማስመዝገብ የሚያስችል ጥናት ማካሄዱንም ገልጸዋል።

የአካባቢውን ማህበረሰብ በኢኮኖሚና ማህበራዊ ዘርፎች ተጠቃሚነቱን ለማሳደግ የሚያከናውናቸውን የምርምር ስራዎች በቀጣይም እንደሚያጠናክር አመልክተዋል።
የዛሬው ምሩቃንም በትምህርት ቆይታቸው ያገኙትን ዕውቀት ተጠቅመው በቀጣይ የራሳቸውንና የህብረተሰቡን ኑሮ ለመለወጥ መትጋት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።
በምረቃ ሥነ ሥርአቱ ላይ የተገኙት የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነርና የዩኒቨርሲቲው የቦርድ ሰብሳቢ ደበሌ ቃበታ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ዩኒቨርሲቲው በእውቀት የበቃ ዜጋን ለማፍራት የጀመረውን ጥረት ማጠናከር እንዳለበት ገልጸዋል፡፡

ዩኒቨርስቲው በቅድመና ድህረ ምረቃ ትምህርት ሀገሪቱ የምትፈልገውን የሰው ሀይል እያፈራ መሆኑ ገልጸው፣ በተለይ የአለም ተለዋዋጭነትን ታሳቢ በማድረግ የምርምር ስራዎችን ማጠናከር እንዳለበት አመልክተዋል፡፡
ዩኒቨርሲቲው በተለይ በኢንዱስትሪ እና በቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ገልጸው፣ ምሩቃንም በዩኒቨርሲቲ ቆይታቸው የቀሰሙትን ዕውቀት ለሀገር ልማትና ብልጽግና እንዲያውሉ አሳስበዋል።
በሶፍትዌር ኢንጂነሪንግ ትምህርት የዋንጫ ተሸላሚው ባስያኤል ጌቱ፤ በትምህርት ቆይታው ሙሉ ጊዜውን ለትምህርት በመስጠቱ ውጤታማ ለመሆን መቻሉን ተናግሯል።

በዩኒቨርሲቲው ሙሉ ጊዜውን ለንባብ እና ለአዳዲስ ፈጠራዎች ትኩረት መስጠቱና በትጋት በመማሩ ለሽልማት መብቃቱን ተናግሯል።
በህግ ትምህርት ከፍተኛ ውጤት ያመጣው ኤፍሬም ሀይለማርያም በበኩሉ፣ በቀጣይም በህግ ትምህርት ባገኘው እውቀት ሀገሩንና ድጋፍ የሚሹ የህብረተሰብ ክፍሎቸን ለማገልግል መዘጋጀቱን ተናግሯል።

በተማሪዎች ምረቃ ሥነ ስርአቱ ላይ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና የተመራቂ ቤተሰቦች ተገኝተዋል።
አምቦ፤ ሰኔ 6/2018(ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ሸዋ ዞን ባለፉት ዓመታት በተከናወኑ የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ስራዎች ለንብ ማነብ ምቹ ሁኔታ በመፍጠሩ...
Jun 14, 2026
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 3/2018(ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል የበጋ መስኖ ልማት በምግብ ራስን ከመቻል ባለፈ የአርስ አደሩን ተጠቃሚነት እያሳደገ መሆኑን የክልሉ ምክት...
Jun 11, 2026
ሐረማያ፤ ግንቦት 20/2018 (ኢዜአ)፦ ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት የሚያሳድጉ የምርምር ቴክኖሎጂዎችን እያጎለበተ እንደሚገኝ አስታወቀ። ዩኒቨ...
Jun 1, 2026
ሆሳዕና፣ግንቦት 17/2018 (ኢዜአ)፦በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት የሚያሳድጉ የሕብረት ሥራ ማህበራትን ደግፎ የማብቃት ሥራው ተጠናክሮ እ...
May 26, 2026