🔇Unmute
ሰቆጣ፤ ሰኔ 19/2018 (ኢዜአ)፦የዋግ ኽምራ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የዲጂታል አሰራር ስርዓት በመዘርጋት ቀልጣፋና ፍትሃዊ አገልግሎት መስጠቱ ከእንግልትና ወጪ ታድጎናል ሲሉ ተገልጋዮች ገለፁ።
በፍርድ ቤቱ የዲጂታል አገልግሎት ሲገለገሉ የነበሩት አቶ ጌጡ ግርማይ ለኢዜአ እንደገለፁት፤ በከፍተኛ ፍርድ ቤት የነበራችውን የሕግ ጉዳይ ለደሴ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ማቅረባቸውን ይናገራሉ።
የሰቆጣ ከተማ ነዋሪ የሆኑት አቶ ጌጡ በብሔረሰብ አስተዳደሩ የሚገኘው ከፍተኛ ፍርድ ቤት በዘረጋው የዲጂታል አገልግሎት በመጠቀም ጉዳያቸውን እየተከታተሉ መሆኑን ነው የሚገልጹት።
ጉዳያቸውን በዲጂታል ቴክኖሎጂ ባሉበት ቦታ ሆነው መከታተል መቻላቸውም ወደ ደሴ ከተማ ለመጓዝ የሚያስፈልጋቸውን ገንዘብ፣ ጉልበትና ጊዜ ለመቆጠብ እንዳስቻላቸው ይናገራሉ።
በብሔረሰብ አስተዳደሩ የፃግብጅ ወረዳ ነዋሪ የሆኑት ወይዘሮ ካሱ ወርቅነህ በበኩላቸው፤ ለ4ኛ ጊዜ የጠቅላይ ፍርድ ቤት አገልግሎትን ለማግኘት ወደ ከፍተኛ ፍርድ ቤቱ እንደመጡ ገልፀዋል።

የጠቅላይ ፍርድ ቤቱን አገልግሎት ለማግኘት ደሴ ከተማ ድረስ መጓዝ ይጠበቅባቸው የነበረ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ግን በተዘረጋው የዲጂታል አሰራር በአቅራቢያቸው መገልገል መቻላቸውን ጠቁመዋል።
አገልግሎቱ መጀመሩ በአጠቃላይ ለትራንስፖርት፣ ለምግብ፣ ለማረፊያና ሌሎች አገልግሎቶች ያወጡት የነበረውን እስከ 25 ሺህ ብር የሚደርስ ገንዘብ ለማዳን እንዳስቻላቸው ነው የሚናገሩት።
የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ጌታነህ ጥጋቡ እንደገለጹት፤ ፍርድ ቤቱ የዲጂታል አሰራርን በመከተል በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ መሰረታዊ ለውጥ ማምጣት ተችሏል።

በተለይም ባለጉዳዮች ለጠቅላይ ፍርድ ቤቱ በዲጂታል ቴክኖሎጂ ይግባኝ ለማቅረብ ወደ ደሴና ባህርዳር ከተሞች ያደርጉት የነበረውን ጉዞ፣ እንግልትና ወጪ ያስቀረ መሆኑን አስረድተዋል።
አገልግሎቱ መጀመሩ ባለጉዳዮች ይግባኝ የተጠየቁባቸው 220 የወንጀልና የፍትሐብሄር መዝገቦችን በዲጂታል የዳኝነት ስርዓት ውሳኔ እንዲያገኙ በማድረግ ሊያወጡ የነበረውን 4 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር ማዳን ተችሏል ብለዋል።
ይህም በአቅም ማነስ ምክንያት የይግባኝ ስርዓት ለማቅረብ የማይችሉ የህብረተሰብ ክፍሎችን ችግር በዘላቂነት የፈታ አሰራር መሆኑን ነው የተናገሩት።
ፍርድ ቤቱ የዲጂታል አሰራርን በመከተሉ ቀልጣፋና ፍትሃዊ ውሳኔ ከመስጠት ባሻገር አሰራሩን ከወረቀት ንክኪ ነጻ ማድረግ መቻሉን አስረድተዋል።
ጋምቤላ፤ ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መምጣቱን የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት...
Sep 4, 2026
አሶሳ፤ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ)፡- በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት ተኪ ምርቶችን የማምረት ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የክልሉ ርዕሰ ...
Sep 3, 2026
ሆሳዕና፤ ነሀሴ 5/2018 (ኢዜአ)፡-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ዜጎችን በሥራ ዕድል ተጠቃሚ ለማድረግ በተከናወኑ ሥራዎች ውጤት መመዝገ...
Aug 12, 2026
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 5/2018 (ኢዜአ)፦የመንግሥት በሙስናና ሕገ ወጥ ድርጊት የተሰማሩ አካላትን በሕግ ተጠያቂ የማድረግ ርምጃ ቀጣይነት ሊኖረው እንደሚገባ ኢዜአ...
Aug 12, 2026