የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ህይወት እና ጉዞ

በክልሉ ያሉ ጸጋዎችን መሰረት ያደረገው ክህሎት መር የሥራ ዕድል ፈጠራ ወጣቶችን ተጠቃሚ አድርጓል

Jul 2, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ሀዋሳ፤ ሰኔ 24/2018(ኢዜአ)፡-በሲዳማ ክልል ያሉ እምቅ ጸጋዎች በመለየት የተከናወኑ ክህሎት መር የሥራ ዕድል ፈጠራ ሥራዎች ተጠቃሚ እንዳደረጓቸው ወጣቶች ገለጹ።

የክልሉ ሥራና ክህሎት ቢሮ በበኩሉ ጸጋዎችን በመለየትና ቅንጅታዊ አሰራርን በማጠናከር የወጣቱን የሥራ ዕድል ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት ውጤታማ መሆናቸውን አስታውቋል።

በክልሉ በአለታ ጩኮ ወረዳ ጭጮ ወያማ ቀበሌ በሥራ ዕድል ፈጠራ ተጠቃሚ የሆኑ ወጣቶች የሥራ እንቅስቃሴ ላይ ምልከታ ተደርጓል።


በቀበሌው ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የተመረቁ ከ200 በላይ ወጣቶች ተደራጅተው ከ62 ሄክታር በላይ መሬት ላይ በቆሎ በኩታ ገጠም እያለሙ መሆናቸውን ተናግረዋል።

አስተያየቱን ለኢዜአ የሰጠው ወጣት ፊልጶስ ይስሐቅ፣ መንግስት ከዩኒቨርሲቲ ለተመረቁ ወጣቶች የወል መሬት በማመቻቸት እና ምርጥ ዘርና ማዳበሪያ በማቅረብ በግብርና ልማት እንዲሰማሩ ማድረጉን ተናግሯል።

በተፈጠረላቸው የሥራ ዕድል ደስተኛ መሆኑን ገልጾ፣ በመጀመሪያ ዙር ያለሙት የበቆሎ ሰብል በጥሩ ቁመና ላይይገኛል ብሏል።


ሌላኛው የይርጋለም ከተማ ነዋሪ ወጣት አገኘሁ ከቦ በበኩሉ እሱን ጨምሮ 100 ወጣቶች በስምንት ማህበራት ተደራጅተው የአቮካዶ ችግኝ በማፍላት ሥራ መሰማራታቸውን ተናግሯል ።

በአካባቢው የአቮካዶ ዘይት አምራች ኩባንያዎች መኖር እና ለአረንጓዴ አሻራ ልማት የተሰጠ ትኩረት ውጤታማ እንደሚያደርጋቸው የአዋጭነት ጥናት መስራታቸውን ጠቅሶ፤ ወደስራ ሲገቡም የመነሻ ካፒታል፣ የመስሪያ ቦታ እና የተሻሻለ የአቮካዶ ዘር እንዳቀረበላቸው ገልጿል።

በአሁኑ ወቅትም 40 ሺህ የተሻሻሉ የአቮካዶ ችግኞችን አፍልተው ለገበያ ለማቅረብ መዘጋጀታቸውን ገልጸው፣በወቅቱ ገበያ አንድ ችግኝ እስከ 150 ብር እንደሚሸጥ ተናግረዋል።

በሀዋሳ ከተማ በኮሪደር ልማት ሥራ በአረንጓዴ ልማት ዘርፍ ተደራጅተው ወደሥራ እንደገቡ የተናገረው ወጣት ምንተስኖት ደሳለኝ በበኩሉ በተፈጠረው የሥራ ዕድል ተጠቃሚ እየሆኑ መምጣታቸውን ተናግሯል።


የሲዳማ ክልል ስራና ክህሎት ቢሮ ምክትል ሃላፊ አቶ ከፍያለሁ ከበደ በበኩላቸው እንዳሉት በክልሉ ያሉ የሥራ ዕድል አማራጮችን በመጠቀም በርካታ ወጣቶችን ወደሥራ ለማስገባት ተችሏል።

ለወጣቱ በሥራ ፈጠራ ላይ አጫጭር ስልጠናዎችን በመስጠት፣ ቅንጅታዊ አሰራርን በማጠናከር፣ የመስሪያና መሸጫ ቦታ እንዲሁም መነሻ ካፒታል በማመቻቸት የሚደረጉ ክትትልና ድጋፎች ውጤት ማምጣታቸን አስረድተዋል ።


በዚህም በበጀት ዓመቱ ከ564 ሚሊዮን ብር በላይ የገንዘብ ብድርና 341 ሼዶች መቅረባቸውን ጠቅሰው ሁሉም ተቋማት በተቀናጀ መልኩ ለወጣቶች የሥራ ዕድል ፈጠራ የሰጡት ትኩረት ውጤት እያመጣ ነው ብለዋል ።

የወጣቱን የሥራ ዕድል ተጠቃሚነት ለማስፋት በተደረገ ጥረት ወጣቱ ተቀጣሪ ከመሆን ይልቅ ስራን መፍጠር ላይ እያተኮረ መምጣቱን ተናግረው፣ በዘርፉ የተገኘውን ውጤት የማስፋት ሥራ ይጠናከራል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መጥቷል

ጋምቤላ፤ ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መምጣቱን የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት...

Sep 4, 2026

በክልሉ ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት ተኪ ምርቶችን የማምረት ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል -ርዕሰ መስተዳድር አሻደሊ ሀሰን

አሶሳ፤ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ)፡- በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት ተኪ ምርቶችን የማምረት ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የክልሉ ርዕሰ ...

Sep 3, 2026

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሥራ ዕድል ፈጠራ በተከናወኑ ሥራዎች ውጤት ተገኝቷል

ሆሳዕና፤ ነሀሴ 5/2018 (ኢዜአ)፡-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ዜጎችን በሥራ ዕድል ተጠቃሚ ለማድረግ በተከናወኑ ሥራዎች ውጤት መመዝገ...

Aug 12, 2026

በሙስናና ሕገ ወጥ ድርጊት የተሰማሩ አካላትን ተጠያቂ የማድረግ ርምጃ ቀጣይነት ሊኖረው ይገባል

አዲስ አበባ፤ነሐሴ 5/2018 (ኢዜአ)፦የመንግሥት በሙስናና ሕገ ወጥ ድርጊት የተሰማሩ አካላትን በሕግ ተጠያቂ የማድረግ ርምጃ ቀጣይነት ሊኖረው እንደሚገባ ኢዜአ...

Aug 12, 2026