የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ህይወት እና ጉዞ

በዞኑ በበጋ መስኖ ልማት የአርሶ አደሩን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ማሳደግ ተችሏል

Jul 2, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ደብረ ማርቆስ ፤ ሰኔ 24/ 2018 (ኢዜአ):-በምስራቅ ጎጃም ዞን የበጋ መስኖ ልማት ስራን በማስፋፋት የአርሶ አደሩን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ማሳደግ መቻሉን የዞን ግብርና መምሪያ ገለጸ።

የዞኑ ግብርና መምሪያ የመስኖ ልማት ባለሙያ አቶ ካሳሁን ዘለቀ ለኢዜአ እንደገለጹት፤የበጋ መስኖ ልማት ስራ አርሶ አደሩ የዝናብ ወቅትን ጠብቆ ከማምረት እንዲወጣ በማድረግ ለውጥ ለማስመዝገብ አስችሏል።

አርሶ አደሩ በበጋ መስኖ ልማት ስራ በስፋት እንዲሰማራ የተከናወነውን የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራ ጨምሮ በወቅቱ ግብአት እንዲቀርብለት መደረጉም ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነቱን ለማሳደግ ያስቻለ መሆኑን አንስተዋል።

ለአብነትም በዘንድሮው በጋ ወራት ከ 50 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬትን በመስኖ በማልማት ከ4 ነጥብ 7 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት መገኘቱን ጠቁመዋል።

የመስኖ ልማቱ ይበልጥ ምርታማነትን ለማሳደግ እንዲያስችልም ከ67 ሺህ ኩንታል በላይ ማዳበሪያና ምርጥ ዘር ጥቅም ላይ መዋሉን አስረድተዋል።

በመስኖ ልማት ስራው 100 ሺህ አርሶ አደሮች የተሳተፉ ሲሆን የተገኘው ምርት ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር ከ1 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ብልጫ አለው ብለዋል።

ለተገኘው ስኬት የግብርና ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ጨምሮ የባለሙያዎች የተጠናከረ ድጋፍ ተጠቃሽ ነው ብለዋል።

በበጋው ወራት መስኖ ልማት በመሳተፍ ተጠቃሚ ከሆኑ አርሶ አደሮች መካከል የማቻከል ወረዳ የየውላ ቀበሌ አርሶ አደር አዲሱ ይዘንጋው ፤ ባላቸው አንድ ሄክታር መሬት ላይ ስንዴ እና በቆሎ በማልማት ተጠቃሚ መሆናቸውን ነው የገለጹት።

የመስኖ ልማት ስራው ከዝናብ ጥገኝነት በመውጣት እና በሁለት ዙር በማምረት ከቤት ፍጆታ አልፎ ለገበያ የሚቀርብ ምርት እንዲያገኙ በማድረግ ተጠቃሚ እንዳደረጋቸው አስረድተዋል።

ከባለሙያዎች ያገኙትን ግንዛቤና ግብአት በመጠቀም በመስኖ ልማት ስራ በመሰማራት በግማሽ ሄክታር መሬት ላይ የጓያና የጓሮ አትክልትን አልምተው ተጠቃሚ መሆናቸውን ያነሱት ደግሞ በዞኑ የአነደድ ወረዳ የወጀል ቀበሌ አርሶ አደር እንዳላማው ጫኔ ናቸው።

የበጋ መስኖ ስራ የተለያዩ ሰብሎችን በማልማትና በማስፋፋት ኑሮዋቸውን ለመቀየር እንዳስቻላቸውም ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መጥቷል

ጋምቤላ፤ ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መምጣቱን የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት...

Sep 4, 2026

በክልሉ ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት ተኪ ምርቶችን የማምረት ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል -ርዕሰ መስተዳድር አሻደሊ ሀሰን

አሶሳ፤ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ)፡- በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት ተኪ ምርቶችን የማምረት ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የክልሉ ርዕሰ ...

Sep 3, 2026

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሥራ ዕድል ፈጠራ በተከናወኑ ሥራዎች ውጤት ተገኝቷል

ሆሳዕና፤ ነሀሴ 5/2018 (ኢዜአ)፡-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ዜጎችን በሥራ ዕድል ተጠቃሚ ለማድረግ በተከናወኑ ሥራዎች ውጤት መመዝገ...

Aug 12, 2026

በሙስናና ሕገ ወጥ ድርጊት የተሰማሩ አካላትን ተጠያቂ የማድረግ ርምጃ ቀጣይነት ሊኖረው ይገባል

አዲስ አበባ፤ነሐሴ 5/2018 (ኢዜአ)፦የመንግሥት በሙስናና ሕገ ወጥ ድርጊት የተሰማሩ አካላትን በሕግ ተጠያቂ የማድረግ ርምጃ ቀጣይነት ሊኖረው እንደሚገባ ኢዜአ...

Aug 12, 2026