የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ህይወት እና ጉዞ

በኦሮሚያ ክልል በበጀት ዓመቱ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማትን ውጤታማ ማድረግ ያስቻሉ ተግባራት ተከናውነዋል

Jul 16, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዳማ፤ ሐምሌ 8/2018 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል በበጀት ዓመቱ ሰላምን በማስፈን ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማትን ውጤታማ ለማድረግ ያስቻሉ ተግባራት መከናወናቸውን የክልሉ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አወሉ አብዲ ገለጹ።

የክልሉ 2018 ዓ.ም የመንግሥትና የፓርቲ ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ በአዳማ አባገዳ አዳራሽ እንደቀጠለ ነው፡፡

የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዚዳንትአቶ አወሉ አብዲ መግለጫ ሰጥተዋል።

በበጀት ዓመቱ በተለይም በክልሉ ሰላምና ጸጥታን በማጠናከር ረገድ ውጤታማ ሥራ መሠራቱን ተናግረዋል።

በበጀት ዓመቱ በተለያየ መልኩ የፀረ-ሰላም ኃይሎች የሰላምና ልማት ሥራዎችን ለማደናቀፍ ቢሞክሩም ሕዝቡና የክልሉ የጸጥታ ኃይል በጋራ ሆነው ለሰላም መስፈን በሠሩት ሥራ የልማት ሥራዎችን ማስቀጠል ተችሏል ብለዋል።

በሰፈነው ሰላም የልማት ስራዎችን በተሳካ ሁኔታ ማስቀጠል መቻሉን ተናግረው አሁንም የተገኘውን ሰላም ለማጽናት ጠንካራ የጸጥታ ኃይል የመገንባቱ ሥራ ይቀጥላል ሲሉ ተናግረዋል።

በክልሉ በማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዘርፎችም በተለይ የመንግሥት የልማት ድርጅቶችን ውጤታማ ከማድረግና የክልሉን ገቢ ከማሳደግ አንጻር ውጤት መገኘቱንም አመልክተዋል።

እንደ ምክትል ፕሬዚዳንቱ ገለጻ፣ በ2012 ዓ.ም 70 ቢሊዮን ብር የነበረውን የክልሉን ገቢ በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት 341 ቢሊዮን ብር ማድረስ ተችሏል።

በዚህም ለክልሉ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት ሥራዎች የሚያስፈልገውን ወጪ በራስ አቅም ለመሸፈን አቅም እየተገነባ መሆኑን አስረድተዋል።

በተመሳሳይ በ'ቡሳ ጎኖፋ' ሥርዓት አማካኝነት የኦሮሞ ሕዝብ የቀደመ የመረዳዳት ባህልን እንዲያጠናክር በማድረግ ችግሮችን በራስ አቅም ተደጋግፎ ለማለፍ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ጠቅሰዋል።

በበጎ ፈቃድ አገልግሎትም በተለይ በአረንጓዴ አሻራ፣ አቅመ ደካሞችን በማገዝ እና በሌሎች መንገዶች አብሮነትን ያጠናከሩ ሥራዎች ተሰርተዋል ብለዋል።

በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚስተዋለውን ሌብነት፣ የሥነ ምግባር ጉድለትና ብልሹ አሠራር ለማስቀረት የመንግሥት አገልግሎትን ለማሻሻልና ለማዘመን መሰራቱን ገልጸው፣ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን ተደራሽ በማድረግ የተሻለ ውጤት መመዝገቡን ተናግረዋል።

በመጀመሪያው ዙር አምስት የክልል ከተሞች ላይ የተጀመረው የአንድ ማዕከል አገልግሎት፤ በሁለተኛው ዙር 26 ከተሞችን ጨምሮ በአሁኑ ወቅት በ96 ከተሞች ላይ መስፋፋቱን አንስተዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መጥቷል

ጋምቤላ፤ ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መምጣቱን የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት...

Sep 4, 2026

በክልሉ ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት ተኪ ምርቶችን የማምረት ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል -ርዕሰ መስተዳድር አሻደሊ ሀሰን

አሶሳ፤ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ)፡- በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት ተኪ ምርቶችን የማምረት ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የክልሉ ርዕሰ ...

Sep 3, 2026

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሥራ ዕድል ፈጠራ በተከናወኑ ሥራዎች ውጤት ተገኝቷል

ሆሳዕና፤ ነሀሴ 5/2018 (ኢዜአ)፡-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ዜጎችን በሥራ ዕድል ተጠቃሚ ለማድረግ በተከናወኑ ሥራዎች ውጤት መመዝገ...

Aug 12, 2026

በሙስናና ሕገ ወጥ ድርጊት የተሰማሩ አካላትን ተጠያቂ የማድረግ ርምጃ ቀጣይነት ሊኖረው ይገባል

አዲስ አበባ፤ነሐሴ 5/2018 (ኢዜአ)፦የመንግሥት በሙስናና ሕገ ወጥ ድርጊት የተሰማሩ አካላትን በሕግ ተጠያቂ የማድረግ ርምጃ ቀጣይነት ሊኖረው እንደሚገባ ኢዜአ...

Aug 12, 2026