የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ህይወት እና ጉዞ

በደቡብ ወሎ ዞን በግብርናው ዘርፍ የተገኘው አበረታች ውጤት ተጠናክሮ ይቀጥላል

Jul 9, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ደሴ፤ ሐምሌ 1/ 2018 (ኢዜአ):- በደቡብ ወሎ ዞን በግብርናው ዘርፍ ቴክኖሎጂንና አዳዲስ አሰራሮችን ተግባራዊ በማድረግ የተገኘው አበረታች ውጤት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አሊ መኮነን ገለፁ።

በዞኑ 15 የእርሻ ትራክተሮች ለአርሶ አደሩ ተከፋፍለዋል።


የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አሊ መኮነን በርክክቡ ወቅት እንደገለጹት፤ በዞኑ ባለፉት የለውጥ ዓመታት ግብርናውን በማዘመን ምርታማነትን ለማሳደግ የተደረገው ጥረት አበረታች ውጤት ተመዘግቦበታል።

ዞኑ በሜካናይዜሽን ለሚካሄድ የሰብል ልማት ምቹ መሆኑን ጠቁመው፣ እየተመዘገበ ያለውን ውጤት ለማስቀጠልም 15 የእርሻ ትራክተሮችን ለወረዳዎች ማስረከብ መቻሉን አስረድተዋል።

በዚህም በምግብ ራስን ከመቻል ባለፈ ጥራትና ብዛት ያለው ምርት በማምረት ለኢንዱስትሪ ግብዓትና ለውጭ ገበያ ለማቅረብ የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል።

የዞኑ ግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ አህመድ ጋሎ በበኩላቸው፣ በዞኑ ግብርናውን ከኋላ ቀር አሰራር በማውጣት ወደ ዘመናዊ የአስተራረስ በዘዴ በመከተል ምርታማነትን ለማሳደግ እየተሰራ ነው።


በዚህም አርሶ አደሩ የምግብ ዋስትናውን ከማረጋገጥ ባለፈ ለኢንዱስትሪ ግብዓትና ለገበያ የሚተርፍ ምርት ማምረት የሚያስችል አቅም መፍጠሩን ተናግረዋል።

ይህም የምርት ማሳደጊያ ቴክኖሎጂዎችንና አዳዲስ አሰራሮችን በተገቢው ሁኔታ በመተግበር የመጣ ውጤት መሆኑን አስረድተዋል።

የመጣውን ውጤት አጠናክሮ ለማስቀጠልም ዛሬ የተሰራጩትን ጨምሮ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 37 የእርሻ ትራክተሮችን በማሰራጨት በአጠቃላይ በዞኑ ያሉ የትራክተሮች ቁጥርን 89 መድረሱን አረጋግጠዋል።

"በዘመናዊና የተሻሻለ የግብርና አሰራር ምርታማነትን በማሳደግ የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ተችሏል" ያሉት ደግሞ የለጋምቦ ወረዳ ግብርና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሁሴን ሙላት ናቸው።


አርሶ አደሩ ሜካናይዜሽን አሰራርን እየተላመደ በመምጣቱ የቴክኖሎጂ ጥያቄው መስፋቱን ጠቁመው፣ ዛሬ የተረከቧቸውን ሁለቱን ጨምሮ 15 ትራክተሮች በስራ ላይ እንደሚገኙ አስገንዝበዋል።

በርክክቡ ወቅት በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የአማራ ክልል የገጠር ክላስተር አስተባባሪ ድረስ ሳህሉ (ዶ/ር)፤የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ደረጀ ማንደፍሮ እና ሌሎች አመራሮችና ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መጥቷል

ጋምቤላ፤ ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መምጣቱን የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት...

Sep 4, 2026

በክልሉ ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት ተኪ ምርቶችን የማምረት ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል -ርዕሰ መስተዳድር አሻደሊ ሀሰን

አሶሳ፤ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ)፡- በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት ተኪ ምርቶችን የማምረት ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የክልሉ ርዕሰ ...

Sep 3, 2026

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሥራ ዕድል ፈጠራ በተከናወኑ ሥራዎች ውጤት ተገኝቷል

ሆሳዕና፤ ነሀሴ 5/2018 (ኢዜአ)፡-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ዜጎችን በሥራ ዕድል ተጠቃሚ ለማድረግ በተከናወኑ ሥራዎች ውጤት መመዝገ...

Aug 12, 2026

በሙስናና ሕገ ወጥ ድርጊት የተሰማሩ አካላትን ተጠያቂ የማድረግ ርምጃ ቀጣይነት ሊኖረው ይገባል

አዲስ አበባ፤ነሐሴ 5/2018 (ኢዜአ)፦የመንግሥት በሙስናና ሕገ ወጥ ድርጊት የተሰማሩ አካላትን በሕግ ተጠያቂ የማድረግ ርምጃ ቀጣይነት ሊኖረው እንደሚገባ ኢዜአ...

Aug 12, 2026