የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ህይወት እና ጉዞ

በአማራ ክልል ከአራት ነጥብ ዘጠኝ ሚሊየን ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ ለአርሶ አደሩ ተሰራጭቷል

Jul 10, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ደሴ፤ሐምሌ 2/2018 (ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ለመጪው መኸር ሰብል ልማት የሚውል ከአራት ነጥብ ዘጠኝ ሚሊየን ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ ለአርሶ አደሩ መሰራጨቱን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ።

የቢሮው ኃላፊ አቶ ደረጀ ማንደፍሮ ለኢዜአ እንደገለጹት፣ ለዘንድሮው የመኸር ሰብል ልማት ስምንት ነጥብ ስድስት ሚሊየን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ለአርሶ አደሩ ለማቅረብ ታቅዶ ወደ ሥራ ተገብቷል።

እስካሁን ባለው ሒደትም ከአምስት ነጥብ አራት ሚሊዮን ኩንታል በላይ ማዳበሪያ ወደ አካባቢው የገባ ሲሆን ከዚህ ውስጥም አራት ነጥብ ዘጠኝ ሚሊዮን ኩንታል የሚሆነውን ለአርሶ አደሩ ማሰራጨት መቻሉን ገልጸዋል።


የማዳበሪያ ስርጭቱ ቀድመው ለሚዘሩ እንዲሁም በክረምት ለተሽከርካሪ አስቸጋሪ ለሆኑ አካባቢዎች ቅድሚያ በመስጠት የተከናወነ መሆኑን አስረድተዋል።

ማዳበሪያንና ሌሎች ግብአቶችን በወቅቱ ተደራሽ በማድረግ የክልሉን ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ሰፊ ጥረት እየተደረገ እንደሚገኝም ነው ያስረዱቱ።

የደቡብ ወሎ ዞን ግብርና መምሪያ ምክትል ኃላፊ አቶ ደመቀ አድማሱ በበኩላቸው፣ በዞኑ ለዘንድሮው መኸር እርሻ ለማቅረብ ከታቀደው 644 ሺህ ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ውስጥ 517 ሺህ ኩንታሉን ማስገባት ተችሏል።


ከዚህ ውስጥም 387 ሺህ ኩንታል የሚሆነውን ለአርሶ አደሩ ማሰራጨት መቻሉን ገልጸዋል።

በሰሜን ወሎ ዞን ለመኸር ምርቱ ለማቅረብ ከታቀደው 217 ሺህ ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ውሰጥ 160 ሺህ ኩንታሉን ለአርሶ አደሩ ማሰራጨት ተችሏል ያሉት ደግሞ የዞኑ ግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ ተገኝ አባተ ናቸው።


በምርት ዘመኑ በተሻሻሉ ዘመናዊ አሰራሮች 231 ሺህ ሄክታር መሬት በማልማት ከ 7 ነጥብ አንድ ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ለመሰብሰብ እንዲቻል ወደ ስራ መገባቱን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መጥቷል

ጋምቤላ፤ ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መምጣቱን የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት...

Sep 4, 2026

በክልሉ ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት ተኪ ምርቶችን የማምረት ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል -ርዕሰ መስተዳድር አሻደሊ ሀሰን

አሶሳ፤ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ)፡- በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት ተኪ ምርቶችን የማምረት ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የክልሉ ርዕሰ ...

Sep 3, 2026

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሥራ ዕድል ፈጠራ በተከናወኑ ሥራዎች ውጤት ተገኝቷል

ሆሳዕና፤ ነሀሴ 5/2018 (ኢዜአ)፡-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ዜጎችን በሥራ ዕድል ተጠቃሚ ለማድረግ በተከናወኑ ሥራዎች ውጤት መመዝገ...

Aug 12, 2026

በሙስናና ሕገ ወጥ ድርጊት የተሰማሩ አካላትን ተጠያቂ የማድረግ ርምጃ ቀጣይነት ሊኖረው ይገባል

አዲስ አበባ፤ነሐሴ 5/2018 (ኢዜአ)፦የመንግሥት በሙስናና ሕገ ወጥ ድርጊት የተሰማሩ አካላትን በሕግ ተጠያቂ የማድረግ ርምጃ ቀጣይነት ሊኖረው እንደሚገባ ኢዜአ...

Aug 12, 2026