የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ህይወት እና ጉዞ

በምሥራቅ ቦረና ዞን በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ61 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ወጣቶች የሥራ ዕድል ተፈጥሯል

Jul 21, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ነገሌ ቦረና፣ ሐምሌ 11/2018 (ኢዜአ)፦ በምሥራቅ ቦረና ዞን በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ61 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ወጣቶች የሥራ ዕድል መፈጠሩን የዞኑ የሥራ ዕድል ፈጠራና ክህሎት ጽሕፈት ቤት አስታወቀ።

የጽሕፈት ቤቱ የሥራ ዕድል ፈጠራ ቡድን መሪ አቶ ጎዳና ሳራ እንደገለጹት፤ በበጀት ዓመቱ በዞኑ በሚገኙ ሁሉም ወረዳዎች ለ53 ሺህ 266 ወጣቶች የሥራ ዕድል ለማመቻቸት ታቅዶ ወደ ሥራ ተገብቷል።

በተሠራው ሥራም በዕቅድ ከተቀመጠው በላይ 61 ሺህ 111 ወጣቶችን በተለያዩ አራት ዋና ዋና የሥራ ዘርፎች ማሰማራት ተችሏል ብለዋል።

እነዚህ ወጣቶች በ121 የኅብረት ሥራ ማኅበራት ተደራጅተው ወደ ሥራ የገቡ ሲሆን፣ ከእነዚህም መካከል 21 ሺህ 997ቱ ሴቶች ሲሆኑ፣ ከ6 ሺህ በላይ የሚሆኑት ደግሞ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተመራቂዎች መሆናቸውን ገልጸዋል።

ይህ የተመቻቸው የሥራ ዕድል የአርብቶ አደሩን የሥራ ባሕል በማጎልበትና በራስ አቅም የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው ጠቁመዋል።

የእንስሳት እርባታና ማድለብ፣ የአትክልትና ሥራሥር እንዲሁም የመስኖ ልማት፣ የማዕድን ልማት፣ የግብይትና ንግድ ሥራዎች፣ እና የእንጨትና ብረታብረት ውጤቶች ማምረት የሥራ ዕድሉ የተፈጠረባቸው ዘርፎች መሆናቸውን ገልጸዋል።

የጽሕፈት ቤቱ የፋይናንስ አቅርቦት ባለሙያ አቶ ቦሩ ገልገሎ በበኩላቸው፤ ለበጀት ዓመቱ የሥራ ዕድል ፈጠራ ማስፈጸሚያ የሚሆን 464 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ የብድር አቅርቦት ታቅዶ እንደነበር አስታውሰዋል።

በአጠቃላይ በበጀት ዓመቱ ከ578 ሚሊዮን 943 ሺህ ብር በላይ ብድር ማሰራጨት እንደተቻለም አመልክተዋል።

ከፋይናንስ አቅርቦቱ በተጨማሪም በገጠር ከ1 ሺህ ሄክታር በላይ የማምረቻ ቦታ፣ በከተሞች ደግሞ 150 የመሸጫ ሼዶች ለተጠቃሚዎቹ ድጋፍ መደረጉን ባለሙያው ጠቅሰዋል።

የሥራ ዕድሉ ተጠቃሚ ከሆኑት መካከል የነገሌ ቦረና ከተማ ነዋሪው ወጣት ቢኒያም አምሳሉ፤ በእንጨትና ብረታብረት ሥራ መስክ ከሁለት ባልደረቦቹ ጋር በመደራጀት የቤትና የቢሮ ዕቃዎችን እያመረቱ መሆኑን ተናግሯል።

የተደረገላቸው የማምረቻ ቦታና የብድር አገልግሎት ድጋፍ ሠርቶ ለመለወጥ ትልቅ አቅምና መነሳሳት እንደፈጠረላቸውም ገልጿል።

በተመሳሳይ በእንጨት ሥራ ዘርፍ የተሰማራው ወጣት አብዲ ሁሴን በበኩሉ፤ ከሦስት ባልደረቦቹ ጋር በመሆን ሥራ ሳይንቁና ሳይመርጡ በቁርጠኝነት በመሥራት ሕይወታቸውን እያሻሻሉ እንደሚገኙ ገልጿል።

የተመቻቸላቸው የብድር አገልግሎት ራሳቸውንና ቤተሰቦቻቸውን ከመደገፍ ባለፈ፣ ወደፊት ሌሎችንም ለመርዳት አቅደው እንዲሰሩ በር እንደከፈተላቸው አክሏል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በሰሜን ሸዋ ዞን ከ199 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የጠጠር መንገዶች ተገንብተዋል

ደብረ ብርሃን ፤ ሐምሌ 10/2018(ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በ199 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ 72 ኪሎ ሜትር የጠ...

Jul 19, 2026

በክልሉ በበጀት ዓመቱ 47 አዳዲስ አነስተኛና መካከለኛ ኢንዱስትሪዎች ወደሥራ ገብተዋል

ሐረር፤ ሐምሌ 7/2018 (ኢዜአ)፡-በሐረሪ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 47 አዳዲስ አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንዱስትሪዎች ወደ ሥራ መግባታቸውን የክልሉ ኢን...

Jul 16, 2026

የደብረ ማርቆስ ንጉሥ ተክለሃይማኖት አውሮፕላን ማረፊያ የሕዝቡን የተዳፈነ የዘመናት የልማት ጥያቄ የመለሰ ነው-ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ

አዲስ አበባ ፤ሐምሌ 5 /2018 (ኢዜአ)፦የደብረ ማርቆስ ንጉሥተክለሃይማኖት አውሮፕላን ማረፊያ የሕዝቡን የተዳፈነ የዘመናት የልማት ጥያቄ የመለሰ ነው ሲሉ የ...

Jul 14, 2026

በአማራ ክልል ከአራት ነጥብ ዘጠኝ ሚሊየን ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ ለአርሶ አደሩ ተሰራጭቷል

ደሴ፤ሐምሌ 2/2018 (ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ለመጪው መኸር ሰብል ልማት የሚውል ከአራት ነጥብ ዘጠኝ ሚሊየን ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ ለአርሶ አደሩ መ...

Jul 11, 2026