የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ህይወት እና ጉዞ

የኢትዮጵያ የቴክኖሎጂ ሉዓላዊነት ጉዞ አንዱ መገለጫ -መሶብ

Aug 13, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

(በሙሴ መለሰ)

የመንግሥት አገልግሎቶችን ለማግኘት በተለያዩ መሥሪያ ቤቶች መመላለስ፣ የወረቀት ክምርና ረጅም ሰልፍ የኢትዮጵያውያን የቆየ የዕለት ተዕለት ፈተና ነበር።

ይህንን የዜጎች እንግልት በዘላቂነት ለመቅረፍ እና አሰራርን ለማዘመን ታስቦ የተመሠረተው መሶብ የተቀናጀ የአንድ ማዕከል አገልግሎት፣ በሀገሪቱ ታሪክ ውስጥ አዲስ ምዕራፍ ከፍቷል።

የተቀናጀው የ"አዲስ መሶብ" ሱፐር አፕ (Super App) ዲጂታል መድረክ ደግሞ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አማካኝነት ሚያዝያ ወር 2017 ዓ.ም በይፋ ተመርቆ ወደ ሙሉ ሥራ መግባቱ ይታወሳል።

የመሶብ ዋና ዓላማ ተበታትነው የነበሩ ልዩ ልዩ የመንግሥት አገልግሎቶችን በዲጂታል ቴክኖሎጂ አጋዥነት በአንድ ጣሪያ ስር ማገናኘት ነው።

ዜጎች ጊዜና ገንዘባቸውን ሳይባክኑ ፈጣን አገልግሎት እንዲያገኙ ማድረግ፣ የሰዎችን ቀጥተኛ ንክኪ በመቀነስ ሙስናና ብልሹ አሰራርን መዋጋት፣ እንዲሁም ግልጽነትን ማስፈን የተቋሙ መሠረታዊ ምሰሶዎች ናቸው።

በረጅም ጊዜ ስትራቴጂካዊ ዕቅዱ ደግሞ እያንዳንዱ ዜጋ በብሔራዊ የፋይዳ (Fayda) መታወቂያው ብቻ በመጠቀም ሁሉንም የመንግሥት አገልግሎቶች በአንድ አካውንት እንዲያገኝ ማድረግ እና ሥርዓቱን ለአፍሪካ ሀገራት እንደ መሪ ተሞክሮ ማቅረብን ያለመ ነው።

ይህ የዲጂታል መድረክ እና አጠቃላይ የቴክኖሎጂ ሥርዓቱ ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች ሀገር በቀል እውቀት የበለጸገ ሲሆን፣ ጥቅም ላይ የዋሉት የሶፍትዌር ቴክኖሎጂዎች ለሁሉም ክፍት የሆነ (Open-source) መሆናቸው ተቋሙን ከከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ወጪ አድኖታል።

በማዕከላቱ ውስጥ የሚሰሩ ባለሙያዎች ጥብቅ የሆነ የምልመላ ፈተና እና ልዩ ስልጠናዎችን አልፈው የሚገቡ በመሆናቸው የአገልግሎት ጥራቱ ከብልሹ አሰራር የፀዳ እንዲሆን አስችሏል።

መጀመሪያ ላይ በ12 ተቋማትና በ41 አገልግሎቶች ብቻ የተጀመረው ይህ ዘመናዊ አሰራር፣ በአጭር ጊዜ ውስጥ እያሳየ ባለው ፈጣን እድገት በአሁኑ ወቅት የትስስር አቅሙን በከፍተኛ ደረጃ ማሳደግ ችሏል።

አሁን ባለው ተጨባጭ ቁመና መሶብ 27 ዋና ዋና የመንግሥት ተቋማትን ሙሉ በሙሉ በዲጂታል መስመር ማገናኘት የቻለ ሲሆን፣ እነዚህ ተቋማት በአንድ ላይ በመቀናጀት ከ288 በላይ የተለያዩ ዲጂታል አገልግሎቶችን በጥራትና በፍጥነት እያቀረቡ ይገኛሉ።

ተገልጋዮች እንደ ፓስፖርት፣ ውክልና፣ የንግድ ፈቃድ እና የሰነዶች ማረጋገጫ ያሉ ወሳኝ ጉዳዮቻቸውን በአንድ ማዕከል ወይም በሞባይል መተግበሪያቸው ማከናወን ይችላሉ።

ይህንን ተደራሽነት ለማረጋገጥ በሀገር አቀፍ ደረጃ ከ100 በላይ ቋሚና ተንቀሳቃሽ ማዕከላት የተቋቋሙ ሲሆን፣ እስካሁንም ከ1 ነጥብ 2 ሚሊዮን በላይ ዜጎችን በማስተናገድ የአገልግሎት እርካታውን በፌዴራል ደረጃ ወደ ከ98 በመቶ በላይ ማድረስ ተችሏል።

በቅርብ ቀናት ውስጥ የወጡ አዳዲስ ወቅታዊ መረጃዎች ደግሞ ተቋሙ አገልግሎቱን ይበልጥ ተደራሽ እና ተለዋዋጭ እያደረገው መሆኑን ያሳያሉ።

በቀን የሥራ ሰዓት መስተናገድ ለማይችሉ ሠራተኞችና ነጋዴዎች ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር ከተለመደው የሥራ ሰዓት ውጭ የምሽት አገልግሎት (Night Service) በይፋ ተጀምሯል።

ከዚህ በተጨማሪ ወደ ማህበረሰቡ በቀጥታ በመሄድ አገልግሎት የሚሰጡት እና የራሳቸውን ኃይል በከፊል ከፀሐይ ብርሃን የሚያመነጩት ዘመናዊ ተንቀሳቃሽ አውቶቡሶች (Mobile Mesob Bus) በተለይ ለአረጋውያንና ለአካል ጉዳተኞች የቤት ለቤት አገልግሎት መስጠት ጀምረዋል።

የጤናው ዘርፍ አገልግሎቶችንም ለማካተት ከቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታል ጋር አዲስ ስምምነት የተፈራረመ ሲሆን፣ ወደ ሀገር ለሚገቡ ባለሃብቶችና ዳያስፖራዎች ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር በቦሌ ዓለም አቀፍ አየውሮፕላን ማረፊያ አዲስ ማዕከል እየተገነባ ይገኛል።

በአዲስ አበባ ከተማም ከ480 በላይ የአገልግሎት መስኮቶች የሚኖሩት አንድ ግዙፍ ማዕከላዊ የኮምፕሌክስ ሕንፃ ግንባታ በፍጥነት እየተከናወነ ነው።

“ዩኒፋይድ መሶብ” የተሰኘው የኦንላይን መድረክ ዜጎች በሞባይል ስልካቸው የመንግሥት አገልግሎቶችን በቀላሉ እንዲያገኙ የሚያስችል ሥርዓትም ተግባራዊ ሆኗል።

በአሁኑ ወቅት መሶብ ከሀገር ውስጥ አልፎ ዓለም አቀፍ ትኩረትን እየሳበ ይገኛል።

ተቀማጭነታቸውን በአዲስ አበባ ያደረጉ የአፍሪካ ሀገራት አምባሳደሮች እና የቤኒን ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ሚኒስትር ማሁና አክፕሎጋን ማዕከሉን በይፋ የጎበኙ ሲሆን፣ መሶብ ለአፍሪካ ሀገራት በቴክኖሎጂ የተደገፈ የመንግሥት አገልግሎት ሥርዓት ለመገንባት እንደ ትልቅ የምርጥ ተሞክሮ ማሳያ እየተወሰደ ነው።

በቀጣይም ከጅቡቲ፣ ደቡብ ሱዳን እና ኬንያ ጋር በዲጂታል አገልግሎት ዙሪያ የጋራ ትስስር በመፍጠር የአህጉር አቀፍ የዲጂታል ሥርዓት የመገንባት ስትራቴጂ ተነድፎ እየተሰራ ይገኛል።

በአጠቃላይ መሶብ ሀገር በቀል ቴክኖሎጂን በመጠቀም የመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥን በማዘመን እና የሕዝብን እንግልት በመቀነስ ረገድ ውጤታማነቱን በተግባር ያረጋገጠ ስኬታማ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ማሳያ ነው።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሥራ ዕድል ፈጠራ በተከናወኑ ሥራዎች ውጤት ተገኝቷል

ሆሳዕና፤ ነሀሴ 5/2018 (ኢዜአ)፡-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ዜጎችን በሥራ ዕድል ተጠቃሚ ለማድረግ በተከናወኑ ሥራዎች ውጤት መመዝገ...

Aug 12, 2026

በሙስናና ሕገ ወጥ ድርጊት የተሰማሩ አካላትን ተጠያቂ የማድረግ ርምጃ ቀጣይነት ሊኖረው ይገባል

አዲስ አበባ፤ነሐሴ 5/2018 (ኢዜአ)፦የመንግሥት በሙስናና ሕገ ወጥ ድርጊት የተሰማሩ አካላትን በሕግ ተጠያቂ የማድረግ ርምጃ ቀጣይነት ሊኖረው እንደሚገባ ኢዜአ...

Aug 12, 2026

የ25 ዓመት የኤሌክትሪክ ማከፋፈያ እና ማሻሻያ ማስተር ፕላን ጥናት ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ሐምሌ 20/2018 (ኢዜአ):-የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት እስከ ፈረንጆቹ 2049 ድረስ የሚተገበር የ25 ዓመታት ሀገር አቀፍ የኤሌክትሪክ ማስ...

Jul 28, 2026

የኢትዮጵያ የመንገድ መሰረተ ልማቶች የሕዝብን የኢኮኖሚ ትስስር በማሳለጥ የብልፅግና ድልድይ እየገነቡ ነው

አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 16/2018 (ኢዜአ) ፦የኢትዮጵያ መንገድ መሰረተ ልማቶች የሕዝብን የኢኮኖሚ ትስስር በማሳለጥ የብልፅግና ድልድይ እየገነቡ መሆኑን የከተማ...

Jul 24, 2026