የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ህይወት እና ጉዞ

ህዝቡ የጸረ ሙስና ትግሉ ባለቤት እየሆነ መጥቷል

Aug 17, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዳማ፤ ነሐሴ 09/2018 (ኢዜአ)፦ በሀገሪቱ ግንዛቤ ለመፍጠር በተሰሩ ስራዎች ህዝቡ የጸረ ሙስና ትግሉ ባለቤት እየሆነ መምጣቱን የፌዴራል ሥነ ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ሳሙኤል ኡርቃቶ (ዶ/ር) አስታወቁ።

ኮሚሽኑ ያሰናዳው በ17ኛው ሀገር አቀፍ የሥነምግባርና የፀረ- ሙስና ኮሚሽኖች ትስስር ጉባኤ ዛሬ በአዳማ ተካሂዷል።

የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ሳሙኤል ኡርቃቶ(ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፤ ባለፉት ዓመታት በፀረ ሙስና እና ስነ ምግባር ረገድ በተከናወኑ ተግባራት ዋነኛውና ትልቁ ማእቀፍ የሆነው የትውልድ ሥርዓት ግንባታ ጥሩ አቅጣጫ ይዟል።


በዚህ ረገድ በፀረ ሙስና ትግል ዙሪያ በየደረጃው ለሚገኘው ሕዝብ ግንዛቤን ለማስረፅ በተሰራው ስራ ህዝቡ የሙስና ትግሉ ባለቤት እየሆነ መምጣቱን ገልጸዋል።


ህዝቡ ሙስና በሀገሪቱ የመልካም አስተዳደር፣ የኢኮኖሚ፣ የማህበራዊ እና የሰላም አለመረጋጋትን ከሚፈጥሩ ችግሮች መካከል አንዱ እና ዋነኛው ተግዳሮት መሆኑን በጽኑ አቋም በማመን መንግሥት ችግሩን እንዲገታ ያላውን አቋም በተለያዩ መድረኮች ማሳወቁ ለፀረ ሙስና ትግሉ ትልቅ አቅም ነው ብለዋል።

አሁን ላይ መንግሥት በሙስና ላይ የያዘው አቋምና እርምጃ ችግሩን ለማስወገድ ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰው፤ በተለይም ትግሉን ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ ጊዜው የሚጠይቀውን የአሰራር፣ የትብብርና የቅንጅት ስራን ተግባራዊ ማድረግ ወሳኝ መሆኑን አመላክተዋል።

ኮሚሽኑ ባለፈው በጀት ዓመት የፀረ ሙስና ትግሉ በሥነ ምግባር ግንባታ፣ ሙስናን አስቀድሞ መከላከልና ሕግ ማስከበር እንዲሁም የአንድ ዕቅድ የአንድ ሪፖርት ስትራቴጂዎች በመካከለኛ ዘመን ዕቅድ ጋር በማስተሳሰር ውጤታማ አፈጻጸም ማከናወኑን አብራርተዋል።

የክልልና የከተማ አስተዳደር የሥነ ምግባርና የፀረሙስና ኮሚሽኖች ቀደም ሲል 16 ዙር ሀገር አቀፍ የትስስር ጉባኤዎች መካሄዳቸው ለጸረ ሙስና ትግሉ ፍሬያማ እንዲሆን ምቹ መደላድል መፍጠሩንም አንስተዋል።

በ17ኛው ጉባዔም በ2018 በጀት ዓመት ሲከናወኑ በነበሩ የሥነ ምግባር ግንባታና ሙስና መከላከል ስራዎች በጥልቀት በመወያየት ጠንካራና ደካማ ጎኖችን በመለየት በቀጣይ የተሻለ ስራ ለመስራት የሚያስችል አቅጣጫ መቀመጡን ኮሚሽነሩ አስታውቀዋል።

በጉባዔው ላይ የ2018 በጀት ዓመት የሥራ ሪፖርት ያቀረቡት በኮሚሽኑ የዲጂታል ሙስና መረጃ አስተዳደር መሪ ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን በላይነህ፤ የ2018 በጀት ዓመት የፀረ-ሙስና ትግል በዘርፍ-ተኮር፣ ችግር ፈቺ እና ተቋማዊ አሰራር ላይ በማተኮር መከናወኑን አስታውቀዋል።

በዓመቱ የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና መከላከል ሥራዎች ለማስፈጸም የአቅም ግንባታና ሥልጠናዎች፣ የሙስና መከላከል ጥናቶች፣ የአስቸኳይ ሙስና መከላከል ተግባራት፣ የሀብት ማሳወቅና ምዝገባ ሥራዎች በፌዴራል ተቋማትና በሕዝባዊ ድርጅቶች በተጠናከረ ሁኔታ መፈጸማቸውን ለአብነት ጠቅሰዋል።

ኮሚሽኑ ከሕግ አስከባሪ ተቋማት ጋር ትስስሩን በማጠናከር ከተለያዩ ምንጮች የሙስና ወንጀል መረጃ በመሰብሰብና በመተንተን ለሚመለከታቸው አካላት ማቅረቡንም አውሰተዋል።

በመድረኩ ላይ ከአዲስ አበባና ድሬዳዋ አስተዳደርን ጨምሮ ከሁሉም ክልሎች የተውጣጡ ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሥራ ዕድል ፈጠራ በተከናወኑ ሥራዎች ውጤት ተገኝቷል

ሆሳዕና፤ ነሀሴ 5/2018 (ኢዜአ)፡-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ዜጎችን በሥራ ዕድል ተጠቃሚ ለማድረግ በተከናወኑ ሥራዎች ውጤት መመዝገ...

Aug 12, 2026

በሙስናና ሕገ ወጥ ድርጊት የተሰማሩ አካላትን ተጠያቂ የማድረግ ርምጃ ቀጣይነት ሊኖረው ይገባል

አዲስ አበባ፤ነሐሴ 5/2018 (ኢዜአ)፦የመንግሥት በሙስናና ሕገ ወጥ ድርጊት የተሰማሩ አካላትን በሕግ ተጠያቂ የማድረግ ርምጃ ቀጣይነት ሊኖረው እንደሚገባ ኢዜአ...

Aug 12, 2026

የ25 ዓመት የኤሌክትሪክ ማከፋፈያ እና ማሻሻያ ማስተር ፕላን ጥናት ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ሐምሌ 20/2018 (ኢዜአ):-የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት እስከ ፈረንጆቹ 2049 ድረስ የሚተገበር የ25 ዓመታት ሀገር አቀፍ የኤሌክትሪክ ማስ...

Jul 28, 2026

የኢትዮጵያ የመንገድ መሰረተ ልማቶች የሕዝብን የኢኮኖሚ ትስስር በማሳለጥ የብልፅግና ድልድይ እየገነቡ ነው

አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 16/2018 (ኢዜአ) ፦የኢትዮጵያ መንገድ መሰረተ ልማቶች የሕዝብን የኢኮኖሚ ትስስር በማሳለጥ የብልፅግና ድልድይ እየገነቡ መሆኑን የከተማ...

Jul 24, 2026