የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ህይወት እና ጉዞ

የሆለታ ግብርና ምርምር ማዕከል በምርምር የፈለቁ 214 የሰብል ዝርያዎችን ለአርሶ አደሩ ተደራሽ አድርጓል

Nov 17, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ሆለታ፤ ህዳር 07/2019 (ኢዜአ)፦ የሆለታ ግብርና ምርምር ማዕከል በምርምር የፈለቁ 214 የሰብል ዝርያዎችን ለአርሶ አደሩ በማድረስ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት እያረጋገጠ መሆኑን የማዕከሉ ምክትል ዳይሬክተር ዶክተር ውድነህ ጌታሁን ገለጹ።

በኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ሥር የሚተዳደረው የሆለታ ግብርና ምርምር ማዕከል፣ በሀገሪቱ ከሚገኙ አንጋፋና ግንባር ቀደም የግብርና ምርምር ተቋማት መካከል አንዱ ነው።

ማዕከሉ በዋናነት ለደጋማው የሀገሪቱ ስነ-ምህዳር ተስማሚ የሆኑ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን በማፍለቅና በማላመድ ይታወቃል።

ባለፉት አስርተ ዓመታት ባካሄዳቸው ተከታታይ ጥናቶችም በሽታን የሚቋቋሙና ከፍተኛ ምርት የሚሰጡ የተሻሻሉ የሰብል ዝርያዎችን በማውጣት በርካታ አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ ማድረግ ችሏል።

ማዕከሉ በዋናነት በስንዴ፣ በገብስ፣ በጤፍ፣ በባቄላ፣ በአተር፣ በድንችና በቅባት እህቶች ላይ ሰፊ የምርምር ሥራዎችን የሚያከናውን ሲሆን፣ በተጨማሪም በወተት ከብቶች ዝርያ ማሻሻል፣ በእንስሳት መኖ ልማት፣ በአፈር ለምነትና ውሃ አያያዝ እንዲሁም የመነሻ ዘር ብዜትን በማስፋፋት የሀገሪቱን የግብርና ምርታማነት ለማሳደግና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት ውስጥ ጉልህ ሚና እየተጫወተ ይገኛል።

በማዕከሉ የግብርና ኢኮኖሚ ተመራማሪ ዶክተር ውድነህ ጌታሁን ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደገለጹት፣ የማዕከሉ ዋነኛ ዓላማ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን ማፍለቅ እና የፈለቁ ቴክኖሎጂዎችን የዘር ምንጭ በማባዛት ላይ ያተኮረ ነው።

ማዕከሉ በግብርናው ዘርፍ ከሚያከናውናቸው መደበኛ ተግባራት በተጨማሪ፣ በምርምር የተደገፉ የምክር አገልግሎቶችንና ወቅታዊ የግብርና መረጃዎችን ለአርሶ አደሩ ተደራሽ በማድረግ ሀገራዊ ፋይዳ ያላቸው ትላልቅ ሥራዎችን እያከናወነ መሆኑን አስታውቀዋል።

ከዋናው የምርምር ማዕከል በተጨማሪ አራት የምርምር ማዕከላት ቅንጫፎች እንዳሉት ያነሱት ዶክተር ውድነህ፤ በእነዚህ ማዕከላትም የአፈር ምርምር፣ የሰብል ጥበቃ፣ የወተት ማቀነባበሪያ፣ የእንስሳት ጤና እና የጥራት ቁጥጥር ተግባራት የሚከናወኑባቸው ትላልቅ ላቦራቶሪዎች የተደራጁ መሆኑን አንስተዋል።

በአሁኑ ወቅት ማዕከሉ በርካታ የምርምር ስራዎችን እያካሄደ መሆኑን ጠቁመው፣ በተለይም በአፈር ላይ እየተካሄደ ያለው ምርምር ከፍተኛ ትኩረት የተሰጠውና ውጤትም እየተገኘበት መሆኑን እንደ ማሳያ ጠቅሰዋል።

በምርምር የተደገፉ እና በቴክኖሎጂ የመነጩ የሰብል እና የእንስሳት ዝርያዎችን ለአርሶ አደሩ ሲያደርሱ መቆየታቸውን ገልጸው፣ በእስካሁኑ እንቅስቃሴ ወደ 214 የሰብል ዝርያዎችን በምርምር በማፍለቅ ለአርሶ አደሮቹ ተደራሽ ማድረጉንና በዚህም ምርትና ምርታማነት እንዲሻሻል ማድረጉን አስታውቀዋል።

በማዕከሉ የሰብል ምርምር የስራ ሂደት ተጠሪ እንዳሻው ግርማ በበኩላቸው በማዕከሉ የሰብል ቴክኖሎጂዎችን ማፍለቅ፣ ማላመድ እና ዝርያ ማሻሻል ትኩረት ተሰጥቶ ከሚሰራው ዋነኛው ስራ መሆኑን አንስተዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የሆለታ ግብርና ምርምር ማዕከል በምርምር የፈለቁ 214 የሰብል ዝርያዎችን ለአርሶ አደሩ ተደራሽ አድርጓል

ሆለታ፤ ህዳር 07/2019 (ኢዜአ)፦ የሆለታ ግብርና ምርምር ማዕከል በምርምር የፈለቁ 214 የሰብል ዝርያዎችን ለአርሶ አደሩ በማድረስ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት...

Nov 17, 2026

ኢትዮጵያ ከባሕር በር ውጪ ሆና ልትቀጥል አይገባም ሲሉ የኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ተናገሩ

ጭሮ ህዳር 5/2019 (ኢዜአ) ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ ካላት ስትራቴጂካዊ አቀማመጥና ከፍተኛ የሕዝብ ቁጥር አንፃር ከባሕር በር ውጪ ሆና መቀጠል አይገባትም ...

Nov 16, 2026

በኮፕ 32 ጉባኤ የፋይናንስ አቅርቦት እና የአደጋ ቅድመ ዝግጁነት እርምጃዎች የትኩረታችን ማዕከል ይሆናሉ - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፤ ህዳር 2/2019 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ የኮፕ 32 ጉባኤን በምትዘጋጅበት ወቅት፣ የፋይናንስ አቅርቦት፣ የአደጋ ቅድመ ዝግጁነትና እርምጃዎችን የትኩረ...

Nov 12, 2026

የኢትዮጵያ የልማት አቅጣጫዎች የሀገርን እድገት በማነጽ ረገድ መሰረታዊ ስኬቶችን እያስመዘገቡ ነው 

አዲስ አበባ፤ መስከረም 19/2019 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የልማት አቅጣጫዎች የሀገርን እድገት በማነጽ ረገድ መሰረታዊ ስኬቶችን እያስመዘገቡ መሆኑን ምክትል ጠቅ...

Sep 30, 2026