🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ ህዳር 8/2019(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የሰው ሰራሽ አስተውሎት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ልማት ለአፍሪካዊያን የሚተርፍ ተምሳሌታዊ አቅም ነው ሲሉ የአፍሪካ ሀገራት ሰልጣኞች ተናገሩ።
የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ለተውጣጡ የዘርፉ ባለሙያዎች በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ሥራ ፈጠራ (Start-up) ዙሪያ ሥልጠና እየሰጠ ይገኛል።

ኢትዮጵያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን በማቋቋም እና "ዲጂታል ኢትዮጵያ" ስትራቴጂን በመተግበር በዘርፉ ላይ ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ እያፈሰሰች ትገኛለች።
ይህም ከቴክኖሎጂ ተጠቃሚነት ባለፈ ለአፍሪካ ሀገራት የቴክኖሎጂ መፍትሔዎችን፣ ሶፍትዌሮችንና ሥልጠናዎችን የምታቀርብ የአፍሪካ የቴክኖሎጂ ማዕከል እየሆነች መጥታለች።
ኢዜአ ያነጋገራቸው ከአፍሪካ ሀገራት የተወጣጡ ሰልጣኝ ባለሙያዎች እንዳሉት፤ ኢትዮጵያ አህጉራዊ ትስስርን ለማጠናከርና የአፍሪካን አቅም በቴክኖሎጂ ለማሳደግ እያደረገች ያለው ጥረት የሚደነቅ ነው።
ከናይጀሪያ የመጣው አባዮሚ ኦሽኖዎ፤ ስልጠናው አፍሪካውያን ከቴክኖሎጂ ተጠቃሚነት ባሻገር አህጉራዊ መፍትሔ የሚያፈልቁ ሙያተኞች የሚፈሩበትን ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥር ገልጿል።
ኢትዮጵያ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ዘርፍ የገነባችው አቅም እና እያከናወነቻቸው ያሉ ተግባራት ለመላው አፍሪካ ምሳሌ የሚሆኑ መሆናቸውን ጠቅሷል።
በኢንስቲትዩቱ የተዘጋጀው የፓን-አፍሪካኒዝም ሰው ሰራሽ አስተውሎት የሥራ ፈጣሪዎች ሥልጠና የሰልጣኞችን የቴክኒክ ክህሎት በማሻሻል የአፍሪካን ትስስር ለማጠናከር ጉልህ ሚና እንዳለው ተናግሯል።
አህጉራዊ ሥልጠናዎችን በማዘጋጀት ኢትዮጵያ በአፍሪካ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ እና የዲጂታል ሽግግር የመሪነት ሚናዋን በተግባር እየተወጣች መሆኗንም አመላክቷል።

ዩጋንዳዊቷ በረንጋህ ናሙቢሊ በበኩሏ፤ ኢትዮጵያ አህጉራዊ ትስስርን ለማጠናከርና የአፍሪካን የቴክኖሎጂ አቅም ለማሳደግ እያደረገች ያለው ጥረት የሚደነቅ መሆኑን ገልጻለች።
ኢትዮጵያ በዘርፉ ያካበተችውን ልምድና ቴክኖሎጂ ለአፍሪካ ሀገራት ማካፈሏ አህጉራዊ የዲጂታል ትብብርን ለማጠናከር እንደሚያግዝም ተናግራለች።
ከሥልጠናው ያገኘችው እውቀትና ክህሎት ወደ ሀገሯ ስትመለስ ዘርፉን ለማገዝ ትልቅ አቅም እንደሚፈጥርላት አመልክታለች።

ሩዋንዳዊው ጋዮስ ካይራንጋ፤ ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ስታርታፖች እየሰጠች ያለው ስልጠና አፍሪካውያን የራሳቸውን መፍትሔዎች በራሳቸው እንዲፈጥሩ የሚያስችል ነው ብሏል።
ኢትዮጵያ እየወሰደች ያለው ኢኒሼቲቭ አህጉሪቱ በቴክኖሎጂ እና በሰው ሰራሽ አስተውሎት ዘርፍ የጀመረችውን ተግባር ይበልጥ የሚያጠናክር መሆኑን ገልጿል።

ኢትዮጵያዊቷ ወለላ በቀለ በበኩሏ፤ ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ከተውጣጡ ሰልጣኞች ጋር አብሬ በመሰልጠኔ በምሠራው ፕሮጀክት ላይ ገንቢ ሀሳቦችን እንዳገኝና ልምድ እንድቀስም ረድቶኛለች ብላለች።
ሥልጠናው የፈጠራ ሃሳቦቻችንን ወደ ተግባራዊ የንግድ ሥራና ገበያ በመቀየር ራሳችንንም ሆነ ሀገራችንን ተጠቃሚ የምናደርግበትን ዕድል ፈጥሮልናል ነው ያለችው።
ሆለታ፤ ህዳር 07/2019 (ኢዜአ)፦ የሆለታ ግብርና ምርምር ማዕከል በምርምር የፈለቁ 214 የሰብል ዝርያዎችን ለአርሶ አደሩ በማድረስ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት...
Nov 17, 2026
ጭሮ ህዳር 5/2019 (ኢዜአ) ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ ካላት ስትራቴጂካዊ አቀማመጥና ከፍተኛ የሕዝብ ቁጥር አንፃር ከባሕር በር ውጪ ሆና መቀጠል አይገባትም ...
Nov 16, 2026
አዲስ አበባ፤ ህዳር 2/2019 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ የኮፕ 32 ጉባኤን በምትዘጋጅበት ወቅት፣ የፋይናንስ አቅርቦት፣ የአደጋ ቅድመ ዝግጁነትና እርምጃዎችን የትኩረ...
Nov 12, 2026
አዲስ አበባ፤ መስከረም 19/2019 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የልማት አቅጣጫዎች የሀገርን እድገት በማነጽ ረገድ መሰረታዊ ስኬቶችን እያስመዘገቡ መሆኑን ምክትል ጠቅ...
Sep 30, 2026