የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ህይወት እና ጉዞ

በደቡብ ኦሮሚያ ዞን ባለፉት አራት ወራት ከ6 ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ተሰበሰበ

Nov 24, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ነገሌ ቦረና ህዳር 14/2019 (ኢዜአ) በደቡብ ኦሮሚያ ዞን የተቀናጀ የግብር አሰባሰብ ሥርዓትን በመዘርጋትና የንግዱን ማኅበረሰብ ግንዛቤ በማሳደግ ባለፉት አራት ወራት ከ6 ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የዞኑ ገቢዎች ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

በዞኑ ሙሉ በሙሉ በተግባር ላይ የዋለው ዲጂታል ቴክኖሎጂ የገቢ አሰባሰብ ሂደቱን እያሳለጠ እንደሆነም ተገልጿል፡፡

የዞኑ ገቢዎች ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ዳዲ ኩራ፤ በበጀት ዓመቱ በዞኑ 23 ነጥብ 531 ቢሊዮን ብር የሚጠጋ አጠቃላይ ገቢ ለመሰብሰብ ታቅዶ ወደ ስራ መገባቱን ገልጸዋል፡፡

በዞኑ ባሉት ከተሞችና ወረዳዎች እስካሁን በተካሄደው ስራም 6 ቢሊዮን 902 ሚሊዮን 606 ሺህ ብር የሚጠጋ ገቢ መሰብሰቡን አመልክተዋል፡፡

ባለፉት አራት ወራት ከተሰበሰበው ውስጥ 4 ቢሊዮን 56 ሚሊዮን 958 ሺህ 234 ብር በመደበኛው የገቢ አሰባሰብ መርሃ ግብር የተከናወነ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡

ከ2 ቢሊዮን 845 ሚሊዮን 436 ሺህ ብር በላይ ደግሞ ከተለያዩ የውስጥ ገቢ አቅሞችና ከማዘጋጃ ቤቶች የተሰበሰበ እንደሆነ ነው የተናገሩት፡፡

የጽህፈት ቤቱ የገቢ አሰባሰብ ባለሙያ ወይዘሮ መአዛ አሊ በበኩላቸው፤ የግብር ከፋዩን ግንዛቤ በማሳደግ ከፍተኛ ገቢ ለመሰብሰብ ጥረት እያደረጉ እንደሆነ ጠቅሰዋል፡፡

የዞኑን የገቢ አቅሞች አሟጦ ለመጠቀምም የቴሌብር፣ የዲጂታል መታወቂያና ሌሎችም የቴክኖሎጂ አሰራሮች እገዛ እያደረጉ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

የበጀት አመቱን አመታዊ ገቢ እቅድ ለማሳካት በበርካታ ገቢ ሰብሳቢ ሰራተኞችና ድጋፍ ሰጭ ሰራተኞች ርብርብ እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡

ገቢው የተሰበሰበው ከቫት፣ ከጣራና ግድግዳ፣ ከኢንቨስትመንት፣ ከቀረጥ፣ ከተርን ኦቨር ታክስና ታክስ ነክ ካልሆኑ ነገሮች ነው ብለዋል፡፡

አዲሱ የዞኖች አደረጃጀትም በተሻሻለ አሰራር ከፍተኛ ገቢ ለመሰብሰብ የሚያግዝ ከመሆኑም በላይ ጊዜና ወጭ የሚቆጥብ እንደሆነ ጠቅሰዋል፡፡

የአዲሱን ዞን እድገትና ልማት ለማፋጠን ሁሉም ግብር ከፋዮችና ባለድርሻ አካላት እቅዱን ለማሳካት ሊረባረቡ እንደሚገባም ወይዘሮ መአዛ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በነገሌ ቦረና ከተማ የህንጻ መሳሪያዎች አቅራቢና አከፋፋይ ግብር ከፋይ አቶ ወርቁ ኦዳ ግብር መክፈል የዜግነት ግደታም ጭምር ነው ብለዋል፡፡

ለመንግስት የሚከፈለው ግብር ለመሰረተ ልማት ግንባታ በመዋል ተመልሶ ህዝብረተሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርግም ጠቅሰዋል፡፡

በዲጂታል ቴክኖሎጂ የተደገፈው የግብር አከፋፈል ስርአትም ውጣ ውረድን ያስቀረ፣ ወጪና ጊዜን የሚቆጥብ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

ግዴታችንን ካለንበት ሆነን በመክፈል ቀደም ሲል ማዘጋጃ ቤት ድረስ በመሄድ ስናባክን የነበረውን ጊዜ ሙሉ በሙሉ በማስቀረቱ ለስራችን ምቹ ሁኔታ ፈጥሮልናል ብለዋል፡፡

በውጣ ውረድ ምክንያት ለቅጣት ሲዳርግ የነበረው አሰራር በመቅረቱ የግብር ግዴታዬን በወቅቱ በመክፈሌ አሁን በነጻነት እየሰራሁ ነው ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በደቡብ ምሥራቅ ኦሮሚያ ዞን የቱሪዝም መስህቦችን በማልማትና በማስተዋወቅ ሰፊ ተግባራት እየተከናወኑ ነው

ሮቤ ህዳር 09/2019 (ኢዜአ)፦ በደቡብ ምሥራቅ ኦሮሚያ ዞን የተፈጥሮ፣ ታሪካዊና ባህላዊ መስህቦችን በማልማትና በማስተዋወቅ የጎብኝዎች ቁጥርና የዘርፉ ገቢ እ...

Nov 19, 2026

የሆለታ ግብርና ምርምር ማዕከል በምርምር የፈለቁ 214 የሰብል ዝርያዎችን ለአርሶ አደሩ ተደራሽ አድርጓል

ሆለታ፤ ህዳር 07/2019 (ኢዜአ)፦ የሆለታ ግብርና ምርምር ማዕከል በምርምር የፈለቁ 214 የሰብል ዝርያዎችን ለአርሶ አደሩ በማድረስ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት...

Nov 17, 2026

ኢትዮጵያ ከባሕር በር ውጪ ሆና ልትቀጥል አይገባም ሲሉ የኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ተናገሩ

ጭሮ ህዳር 5/2019 (ኢዜአ) ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ ካላት ስትራቴጂካዊ አቀማመጥና ከፍተኛ የሕዝብ ቁጥር አንፃር ከባሕር በር ውጪ ሆና መቀጠል አይገባትም ...

Nov 16, 2026

በኮፕ 32 ጉባኤ የፋይናንስ አቅርቦት እና የአደጋ ቅድመ ዝግጁነት እርምጃዎች የትኩረታችን ማዕከል ይሆናሉ - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፤ ህዳር 2/2019 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ የኮፕ 32 ጉባኤን በምትዘጋጅበት ወቅት፣ የፋይናንስ አቅርቦት፣ የአደጋ ቅድመ ዝግጁነትና እርምጃዎችን የትኩረ...

Nov 12, 2026