የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ህይወት እና ጉዞ

የአዲስ አበባ ጽዳትና የአረንጓዴ ውበት ለአፍሪካ ዘመናዊ የከተማ ግንባታ ትልቅ ተሞክሮ ነው

Nov 26, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፣ ህዳር 16/2019(ኢዜአ)፦ የአዲስ አበባ ጽዳትና የአረንጓዴ ልማት ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ዘመናዊ የከተማ ግንባታና የሕዝብ ጤና አጠባበቅ ትልቅ ተሞክሮ መሆኑን የ5ኛው ዓለም አቀፍ የአፍሪካ የሕዝብ ጤና ጉባኤ ተሳታፊዎች ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኅዳር 14 እስከ 18 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ የሚቆየውን 5ኛውን ዓለም አቀፍ የአፍሪካ የሕዝብ ጤና ጉባኤ (CPHIA 2026) በይፋ መክፈታቸው ይታዎቃል።

በአዲስ አበባ አዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል እየተካሄደ በሚገኘው ጉባኤ ላይ ከ100 በላይ ከሆኑ ሀገራት የተውጣጡ ከ30 ሺህ በላይ ሰዎች እየተሳተፉ ይገኛል።

በአፍሪካ ትልቁ አህጉራዊ የጤና ጉባኤ በትናንትናው የሁለተኛ ቀን ውሎውም "አህጉራዊ የዝግጁነት፤ የመከላከልና የምላሽ አቅምን ተቋማዊ ማድረግ" በሚል መሪ ሐሳብ የውይይት መድረክ ተካሂዷል።

በመድረኩም የተለያዩ ሀገራት በጤና ዘርፍ የታዩ ውጤቶችን፣ ተግዳሮቶችንና ቀጣይ የትኩረት መስኮችን የሚያመላክቱ ልምድና ተሞክሮዎችን በማቅረብ ውይይት ተደርጎባቸዋል።

“የአፍሪካ የጤና ደኅንነትና ሉዓላዊነት፤ ከጤና ጥገኝነትና ተጋላጭነት ወደ ባለቤትነትና ጽናት የሚደረግ ሽግግር” በሚል መሪ ሃሳብ ዛሬም በሶስተኛ ቀን ውሎ መካሄዱን ቀጥሏል።

ከጉባኤው ተሳታፊዎች መካከል ከሴኔጋል የመጡት ሼይክ ሲዲያ ጋዬ ለኢዜአ እንዳሉት፤ ጉባኤው የአህጉሪቷን የሕዝብ ጤና ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ ከፍተኛ አቅም ይፈጥራል።

በኢትዮጵያ ቆይታቸውም የአዲስ አበባ ንጽህና፣ ጽዳት፣ ውበትና የመንገዶች ደህንነት ቀልብን የሚስብ ማራኪ ገጽታ የተላበሱ መሆናቸውን ገልጸዋል።

በዓለም ዙሪያና በተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ተዘዋውረው የመመልከት ዕድል እንደነበራቸው በመጠቆም፤ አዲስ አበባ ከተመለከቷቸው ከተሞች መካከል በንጽህናዋና በማራኪ የከተሜነት ገጽታዋ እንዳስደመመቻቸው ተናግረዋል።

የከተሞችና የአካባቢ ንጽህና ለሕዝብ ጤና አጠባበቅ ሥርዓት እጅግ መሠረታዊ ጉዳይ ነው ያሉት ተሳታፊው፣ የኢትዮጵያ ተሞክሮም ለበርካታ የአፍሪካ ሀገራት በምርጥ ተሞክሮነት የሚቀርብ ነው ብለዋል።

ከናይጄሪያ የመጣችው ዶክተር ሩት ሳቦ በበኩላቸው፤ አዲስ አበባ በአጭር ጊዜ ያስመዘገበችው ለውጥ ቀልብን የሚስብ አስደናቂ ውጤት መሆኑን ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና መንግሥታቸው ከተማዋን በማራኪና የተሰናሰለ መሠረተ ልማት ውብ ገጽታ እንድትላበስ ለወሰዱት ቁርጠኝነትም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

የአዲስ አበባ የአረንጓዴ ልማት፣ የፕላስቲክ አጠቃቀምና አወጋገድ የፖሊሲ እርምጃና መሠረተ ልማቶች ኢትዮጵያ ለዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ግብ መሳካት ያላትን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው ብለዋል።

የአዲስ አበባ አስደናቂ የከተሜነት ገጽታ ለበርካታ የአፍሪካ ከተሞች የሥነ-ምኅዳር ደኅንነት ትልቅ ትምህርት የሚያስተላልፍ ነው ያሉት ደግሞ ሌላኛው የጉባኤው ተሳታፊ ናይጀሪያዊ ዶክተር ኤፎሳ ኤዛሞ ናቸው።

ንጹሕ አካባቢ መኖሩ ለሕዝብ ጤናማ ኑሮን ከማስፈን ባለፈ ማኅበረሰቡ በተሻለ ሁኔታ እንዲኖር፣ እንዲበለጽግና የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግብ የሚያግዝ መሆኑን አስረድተዋል።

የኢትዮጵያ ዘመናዊ የከተሜነት ግንባታ ተሞክሮም ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ትልቅ ትምህርት የሚሰጥ መሆኑን አመልክተዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በደቡብ ምሥራቅ ኦሮሚያ ዞን የቱሪዝም መስህቦችን በማልማትና በማስተዋወቅ ሰፊ ተግባራት እየተከናወኑ ነው

ሮቤ ህዳር 09/2019 (ኢዜአ)፦ በደቡብ ምሥራቅ ኦሮሚያ ዞን የተፈጥሮ፣ ታሪካዊና ባህላዊ መስህቦችን በማልማትና በማስተዋወቅ የጎብኝዎች ቁጥርና የዘርፉ ገቢ እ...

Nov 19, 2026

የሆለታ ግብርና ምርምር ማዕከል በምርምር የፈለቁ 214 የሰብል ዝርያዎችን ለአርሶ አደሩ ተደራሽ አድርጓል

ሆለታ፤ ህዳር 07/2019 (ኢዜአ)፦ የሆለታ ግብርና ምርምር ማዕከል በምርምር የፈለቁ 214 የሰብል ዝርያዎችን ለአርሶ አደሩ በማድረስ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት...

Nov 17, 2026

ኢትዮጵያ ከባሕር በር ውጪ ሆና ልትቀጥል አይገባም ሲሉ የኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ተናገሩ

ጭሮ ህዳር 5/2019 (ኢዜአ) ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ ካላት ስትራቴጂካዊ አቀማመጥና ከፍተኛ የሕዝብ ቁጥር አንፃር ከባሕር በር ውጪ ሆና መቀጠል አይገባትም ...

Nov 16, 2026

በኮፕ 32 ጉባኤ የፋይናንስ አቅርቦት እና የአደጋ ቅድመ ዝግጁነት እርምጃዎች የትኩረታችን ማዕከል ይሆናሉ - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፤ ህዳር 2/2019 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ የኮፕ 32 ጉባኤን በምትዘጋጅበት ወቅት፣ የፋይናንስ አቅርቦት፣ የአደጋ ቅድመ ዝግጁነትና እርምጃዎችን የትኩረ...

Nov 12, 2026