የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ፖለቲካ እና ደህንነት

የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና ከዲጂታል ዓለም ጋር ለመተዋወቅ ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል

Jan 23, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ወላይታ ሶዶ፤ ጥር 14 /2018(ኢዜአ)፦የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና ከዲጂታል ዓለም ጋር ይበልጥ ለመተዋወቅና በዘርፉ የራሳቸውን ሥራ ፈጥረው ለመንቀሳቀስ ምቹ ሁኔታ እንደፈጠረላቸው የወላይታ ሶዶ ከተማ ሰልጣኞች ተናገሩ።

መንግስት በመላው ኢትዮጵያ ለአምስት ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያን የኮደርስ ስልጠና ለመስጠት ግብ ጥሎ እየሰራ ነው።

በወላይታ ሶዶ ከተማም 18 ሺህ 400 ዜጎችን በኢትዮ ኮደርስ ለማሰልጠን እየተሰራ ይገኛል።

የኮደርስ ስልጠና የወሰዱ የከተማዋ ነዋሪዎች ስልጠናው ከዲጂታል ዓለም ጋር ይበልጥ እንዲተዋወቁና የራሳቸውን ሥራ በመፍጠር ተጠቃሚ ለመሆን ምቹ ሁኔታ እንደፈጠረላቸው ተናግረዋል።

አስተያየታቸውን ለኢዜአ ከሰጡት ሰልጣኞች መካከል አቶ ደምሴ አሻ፤ በኮደርስ በተለያዩ ዘርፎች የወሰዷቸው ስልጠናዎች የቴክኖሎጂ እውቀታቸውን በማሳደግ በዲጂታል ዓለም እኩል ለመንቀሳቀስ የሚያስችል ክህሎት እንዳስጨበጧቸው ገልጸዋል።


በአሁኑ ወቅትም ባገኙት እውቀት የራሳቸውን ሥራ ፈጥረው እየተንቀሳቀሱ መሆናቸውን ገልጸው፣ በተጨማሪም በተለያዩ ተቋማት ያሉ ሠራተኞችን በማሰልጠን ተጨማሪ ገቢ እያገኙ መምጣታቸውን ተናግረዋል።

ስልጠናው በዲጂታል ቴክኖሎጂ ዘርፍ ያለኝን እውቀት አሳድጎልኛል ያሉት ደግሞ ሒሩት አርጃ ናቸው።


በኢትዮ ኮደርስ የፕሮግራሚንግ ስልጠና መውሰዳቸውንና በአሁኑ ወቅት በሰውሰራሽ አስተውሎት ስልጠናቸውን እየተከታተሉ መሆናቸውን ገልጸው፣ ከስልጠናው ዲጂታል ዓለምን የሚመጥን እውቀት መቅሰማቸውን ተናግረዋል።

ስልጠናው የኮምፒውተርና የዲጂታል እውቀቴን በማሳደግ ከዓለም ጋር ይበልጥ የምቀራረብበትን ዕድል ሰጥቶኛል ያሉት ደግሞ አቶ ሙሉጌታ ዶላ ናቸው።


በስልጠናው ያገኙት እውቀት በዲጂታል ዓለም ተወዳዳሪ እንደሚያደርጋቸው ተናግረው፣ ያገኙት እውቀት ከተቋማዊ አሰራር ጋር በማስተሳሰር ውጤታማ ሥራ ለማከናወን እንዳስቻላቸውም ገልጸዋል።

የወላይታ ሶዶ ከተማ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ መምሪያ ኃላፊ አቶ ተሻለ ታደሰ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ መምሪያው ስልጠናውን ተደራሽ በማድረግ ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ የተጀመረውን ሥራ ለማገዝ እየሰራ ነው።


የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና ከተጀመረ ወዲህ በከተማው ከ10 ሺህ በላይ ሰዎች ስልጠናቸውን አጠናቅቀው የምስክር ወረቀት ማግኘታቸውን ገልጸው፣ ከነዚህ ውስጥ 3ሺህ 480 የሚሆኑት ባለፉት ስድስት ወራት ስልጠናውን የወሰዱ ናቸው ብለዋል።

በተያዘው ዓመት ዕቅዱን ለማሳካትም የአንድ ጀንበር ምዝገባ ንቅናቄ በማካሄድና በሁሉም አካባቢዎች ያሉ ዜጎችን ለማሰልጠን በልዩ ትኩረት እየተሰራ መሆኑን አስታውቀዋል።

‎ስልጠናው በዲጂታል ክህሎት የዳበረ ማህበረሰብ ለመፍጠርና የዲጂታል ዓለምን በፍጥነት የሚላመድ ትውልድ ለማፍራት የጎላ ጠቀሜታ እንዳለው ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በክልሉ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የተጀመሩ ስራዎችን ማጠናከር ይጠበቅባቸዋል- ርእሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)

ሆሳዕና ፤ ነሐሴ 21/2018 (ኢዜአ) ፦ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚጠበቅባቸውን ሚና እንዲወጡ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ...

Aug 28, 2026

በኢሉባቦር ዞን በኩታ ገጠም ከለማው የበቆሎ ሰብል የተሻለ ምርት ለማገኘት የእንክብካቤ ስራ ተጠናክሯል

መቱ፤ ነሐሴ 11/2018 (ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል በኢሉባቦር ዞን በክረምት እርሻ እየለማ ከሚገኘው የበቆሎ ሰብል የላቀ ምርት ለማገኘት የሰብል እንክብካቤና ጥ...

Aug 18, 2026

በሲዳማ ክልል የመንገድና ሌሎች መሰረተ ልማትን በማሻሻል ለሕዝቡ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ ናቸው

ሀዋሳ፤ ነሐሴ 2/2018 (ኢዜአ)፦ በሲዳማ ክልል የመንገድና ሌሎች መሰረተ ልማትን በማሻሻል ለሕዝቡ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ መሆና...

Aug 10, 2026

በክልሉ በበጀት ዓመቱ ውጤታማ የልማት ሥራዎች ተከናውነዋል 

አዳማ፤ ሐምሌ 12/2018 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል በበጀት ዓመቱ ሰላምና መልካም አስተዳደርን ከማረጋገጥ ጎን ለጎን ውጤታማ የልማት ሥራዎች መከናወናቸውን የክል...

Jul 20, 2026