🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ግንቦት 11/2018 (ኢዜአ)፦የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከዓለም የከተሞች ፎረም ተሳትፎ ጎን ለጎን የአዘርባጃን የአሳን ቀላል የአንድ ማዕከል ዲጂታል አገልግሎትን ጎብኝተዋል።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ የኢትዮጵያ ልዑክ ከዓለም የከተሞች ፎረም ተሳትፎ ጎን ለጎን የአዘርባጃንን የ“አሳን” (ASAN-Azerbaijan Service and Assessment Network) ቀላል የአንድ ማዕከል ዲጂታል አገልግሎት መጎብኘቱን ጠቁመዋል።
ከንቲባዋ ባስተላለፉት መልዕክት፥ በኢትዮጵያ እስከአሁን በመሶብ ዲጂታል የአንድ ማዕከል አገልግሎት ከፍተኛ ለውጥ የመጣ ቢሆንም፣ አሁንም ልምድ ሊሆኑ በሚችሉ ጉዳዮች ላይ ውይይት መደረጉን ገልጸዋል።

ከ14 ዓመታት በፊት የተጀመረውና በቀን 40 ሺህ አፕሊኬሽን ላይ አገልግሎት የሚያሳልጠው “አሳን”፣ በአውቶቡሶች የሚሰጥ የገጠር አካባቢዎች ተንቀሳቃሽ የአገልግሎት ማዕከል በተደራጀ፣ ፈጣንና ቀላል መንገድ አገልግሎት የሚሰጥ መሆኑን ጠቁመዋል።
በኢትዮጵያም ከ41 በላይ ማዕከላት ተገንብተው ስራ የጀመሩ ሲሆን፣ ከነዚህም ውስጥ በአዲስ አበባ 6 ማዕከላት እና 1 ተንቀሳቃሽ አውቶቡስ የዲጂታል የአንድ ማዕከል አገልግሎት በመስጠት ላይ እንደሚገኙም ነው ከንቲባዋ ያወሱት።
በጉብኝቱ ወቅትም የ“አሳን” ሰራተኞች አገልግሎት ሲሰጡ ፈገግታ እና ትህትና አንዱ የአገልግሎት መለኪያ መሆኑን፣ የመከታተያ ካሜራዎች የተገጠሙ መሆኑን እና በጥሩ ሁኔታ የሚያገለግል ሰራተኛ ተመዝኖ የተገልጋዩ የዕርካታ መጠን ከፍተኛ ከሆነ ከደሞዝ በተጨማሪ ቦነስ እንደሚከፈለው ለመታዘብ መቻላቸውን ተናግረዋል።

በዛው ልክ ደግሞ በመስፈርቱ መሰረት ያላገለገለ ሰራተኛ ወዲያው እንደሚባረርና ለነገ ተስፋ አድገው ህዝባቸውን በከፍተኛ ትጋትና አክብሮት የሚያገለግሉ በርካታ በጎ ፍቃደኛ ወጣቶችንም መመልከታቸውን ገልጸዋል።
የእኛም ቢሮክራሲ በተጀመረው አግባብ ሙሉ በሙሉ እንደሚለወጥ እናምናለን ያሉ ሲሆን ይህ እንዲሳካም በትጋት እንደሚሰራ ከንቲባዋ አረጋግጠዋል።
ሆሳዕና ፤ ነሐሴ 21/2018 (ኢዜአ) ፦ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚጠበቅባቸውን ሚና እንዲወጡ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ...
Aug 28, 2026
መቱ፤ ነሐሴ 11/2018 (ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል በኢሉባቦር ዞን በክረምት እርሻ እየለማ ከሚገኘው የበቆሎ ሰብል የላቀ ምርት ለማገኘት የሰብል እንክብካቤና ጥ...
Aug 18, 2026
ሀዋሳ፤ ነሐሴ 2/2018 (ኢዜአ)፦ በሲዳማ ክልል የመንገድና ሌሎች መሰረተ ልማትን በማሻሻል ለሕዝቡ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ መሆና...
Aug 10, 2026
አዳማ፤ ሐምሌ 12/2018 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል በበጀት ዓመቱ ሰላምና መልካም አስተዳደርን ከማረጋገጥ ጎን ለጎን ውጤታማ የልማት ሥራዎች መከናወናቸውን የክል...
Jul 20, 2026