የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ፖለቲካ እና ደህንነት

በድሬደዋ አስተዳደር ባለፉት አስር ወራት ከ17ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ ዕድል ተፈጥሯል

May 20, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ድሬደዋ፣ ግንቦት 12/2018(ኢዜአ)፡- በድሬደዋ ባለፉት አስር ወራት ከ17ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ቋሚ የስራ ዕድል መፈጠሩን የአስተዳደሩ ስራና ክህሎት ቢሮ ገለፀ።

ቢሮው በበጀት ዓመቱ በአነስተኛና ጥቃቅን ለተደራጁ ኢንተርፕራይዞች ከ112 ሚሊዮን ብር በላይ የገበያ ትስስር መፍጠሩንም ጠቁሟል።

በቢሮው የስራ ዕድል ፈጠራና የአንድ ማዕከል አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ ሰኢድ አሊ ለኢዜአ እንደገለፁት፤ በበጀት ዓመቱ የስራ ዕድል ለመፍጠርና ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በተከናወኑ የተቀናጁ ስራዎች አበረታች ውጤቶች ተገኝተዋል።

በአስተዳደሩ በተደረገው እንቅስቃሴም በበጀት ዓመቱ አስር ወራት ከ17ሺህ 300 በላይ ለሚሆኑ ከተለያዩ የትምህርት ተቋማት ለተመረቁ ወጣቶችና የህብረተሰብ ክፍሎች ቋሚ የስራ ዕድል መፈጠሩን ገልጸዋል።

ለተገኘው ውጤት በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ እየመጣ የሚገኘው እመርታ ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን በመጠቆም።

በተጨማሪም ግብርና፣ ኮንስትራክሽን እና የአገልግሎት ዘርፎች የስራ ዕድል የተፈጠረባቸው መስኮች መሆናቸውን አቶ ሰኢድ ገልጸዋል።

በአስተዳደሩ የሚገኙ የተማሩ ወጣቶችን ጥያቄዎች ከአጋር አካላት ጋር በመቀናጀት የመመለስ ስራ ተጠናክሮ መቀጠሉንም አክለዋል።


እንደ አቶ ሰኢድ ገለፃ ቢሮው በዘንድሮ በጀት ዓመት በስሩ በተደራጁት የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች በመታገዝ በአነስተኛና ጥቃቅን የተደራጁ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማነት ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ድጋፎች አድርጓል።

የብድር፣ አጫጭር የሙያና የክህሎት ስልጠና እንዲሁም ከሚመለከታቸው ሴክተሮች ጋር በመቀናጀት የመስሪያና የመሸጫ ቦታዎች ማመቻቸቱን ለአብነት ጠቅሰዋል።

በተጨማሪም ከ600 በላይ ለሚሆኑ ኢንተርፕራይዞች ከ112 ሚሊዮን ብር በላይ የገበያ ትስስር እንዲፈጥሩ በማድረግ የዕድገት ሽግግርን እንዲያፋጥኑ መሰራቱን አንስተዋል።

በስራ ዕድል ፈጠራውም ሆነ በገበያ ትስስር ሴቶች እና አካል ጉዳተኞች ትኩረት ማግኘታቸውንም ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በክልሉ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የተጀመሩ ስራዎችን ማጠናከር ይጠበቅባቸዋል- ርእሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)

ሆሳዕና ፤ ነሐሴ 21/2018 (ኢዜአ) ፦ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚጠበቅባቸውን ሚና እንዲወጡ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ...

Aug 28, 2026

በኢሉባቦር ዞን በኩታ ገጠም ከለማው የበቆሎ ሰብል የተሻለ ምርት ለማገኘት የእንክብካቤ ስራ ተጠናክሯል

መቱ፤ ነሐሴ 11/2018 (ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል በኢሉባቦር ዞን በክረምት እርሻ እየለማ ከሚገኘው የበቆሎ ሰብል የላቀ ምርት ለማገኘት የሰብል እንክብካቤና ጥ...

Aug 18, 2026

በሲዳማ ክልል የመንገድና ሌሎች መሰረተ ልማትን በማሻሻል ለሕዝቡ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ ናቸው

ሀዋሳ፤ ነሐሴ 2/2018 (ኢዜአ)፦ በሲዳማ ክልል የመንገድና ሌሎች መሰረተ ልማትን በማሻሻል ለሕዝቡ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ መሆና...

Aug 10, 2026

በክልሉ በበጀት ዓመቱ ውጤታማ የልማት ሥራዎች ተከናውነዋል 

አዳማ፤ ሐምሌ 12/2018 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል በበጀት ዓመቱ ሰላምና መልካም አስተዳደርን ከማረጋገጥ ጎን ለጎን ውጤታማ የልማት ሥራዎች መከናወናቸውን የክል...

Jul 20, 2026