የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ፖለቲካ እና ደህንነት

በኢትዮጵያ ለዲጂታላይዜሽን የተሰጠው ትኩረት ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነታችንን እያሳደገልን ነው- ተማሪዎች

Jun 16, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 7 /2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ለዲጂታላይዜሽን የተሰጠው ትኩረት ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነትን እያሳደገልን ነው ሲሉ በዓለም አቀፍ የሁዋዌ አይሲቲ የፍፃሜ ውድድር በፈጠራ ዘርፍ አሸናፊ የሆኑ ተማሪዎች ገለፁ።

የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት የ5ጂ ኔትወርክን ሙሉ በሙሉ ተደራሽ ለማድረግ፣ የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያን ለማስፋፋት እንዲሁም ዜጎችን በዲጂታል ክህሎት ማብቃት ላይ ትኩረት አድርጓል።

ለስትራቴጂው መሳካት አስቻይ ከሆኑ መርሃ-ግብሮች አንዱ የሆነው የአምስት ሚሊዮን ኢትዮ-ኮደርስ መርሐ-ግብርም የሰው ኃይል አቅምን በመገንባት፣ ሀገሪቱን ከቴክኖሎጂ ተጠቃሚነት ወደ ቴክኖሎጂ ፈጣሪነት ለማሸጋገር ፋይዳው የጎላ ነው።


ከሰኔ 2 እስከ 5ቀን 2026 በቻይና ሼንዘን በተካሄደው ዓለም አቀፍ የሁዋዌ አይሲቲ የፍፃሜ ውድድር ሁለተኛ በመውጣት የብር ሜዳሊያ ያሸነፉት የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችም መርሃ ግብሩ ለዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት ድርሻ እንዳለው ተናግረዋል።

የዩኒቨርሲቲው ሦስት ተማሪዎች በፈጠራ ዘርፍ (Innovation Track) ኢትዮጵያን በመወከል ለውድድር ቀርበው ከ40 ሀገራት በላይ ከሚገኙ ከፍተኛ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ጋር በመወዳደር አሸናፊ ሆነዋል።


በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የሶፍትዌር ምህንድስና ተመራቂ ተማሪ ፍስሃ አከለ በውድድሩ ሰውሰራሽ አስተውሎት በመጠቀም የጡት ካንሰር ያለበትን ደረጃ በመለየት ለባለሙያዎች ውጤት የሚሰጥ ስርዓት ይዘው ቀርበዋል።

አብዛኛው የጡት ካንሰር ታማሚዎች ወደጤና ተቋም የሚመጡት አስጊ ደረጃ ከደረሱ በኃላ በመሆኑ የፈጠራ ስራቸው ለዚህ ችግር መፍትሄ ለመስጠት በማሰብ መሰራቱንና ፕሮጀክቱን ወደተግባር ለመቀየር እየሰሩ መሆኑን ገልጿል።


ሌላው የውድድሩ አሸናፊ ሚካኤል ወርቅነህ እንዳለው በውድድሩ ሶስት አባላትን በመያዝ በዩኒቨርሲቲ መምህራቸው መሪነት መሳተፋቸውን ገልፆ ውድድሩ ልምዶችን ለመጋራት እድል የፈጠረ መሆኑንም አንስቷል።

ኢትዮጵያ ለዲጂታላይዜሽን የሰጠችው ትኩረት ስራቸውን ለማጎልበት ጉልህ ሚና እንዳለው ጠቅሶ፤ የ5 ሚሊየን ኮደርስ ስልጠና የዲጂታል እውቀትን ለማሳደግ አስተዋፅኦ እንዳለውም ተናግሯል።

የቡድኑ አባል የሆነው የዩኒቨርሲቲው የሶፍትዌር ምህንድስና ተመራቂ ተማሪ ሚኪያስ ጎይቶም ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት ለማሳደግ የሰው ኃይልን ማብቃት ወሳኝ መሆኑንና የኮደርስ ስልጠና በዚህ ረገድ ጉልህ ድርሻ እንዳለው ገልጿል።


ተማሪዎቹን በማስተባበር ቡድኑን የመሩት የዩኒቨርሲቲው የሶፍትዌር ኢንጂነሪንግ መምህር ጌትነት ግርማ በውድድሩ በተገኘው ውጤት ዩኒቨርሲቲው ከምስራቅ አፍሪካ በዘርፉ ምርጥ ዩኒቨርሲቲ ሆኖ እንዲመረጥ አስችሏል ብለዋል።


ይህንን ተከትሎ ዩኒቨርሲቲው ፕሮግራሙን ወደሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ለማስፋት እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።


ውድድሩ ዩኒቨርሲቲው ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ትምህርት እየሰጠ መሆኑን ማረጋገጫ ነው ያሉት ደግሞ የዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ፕሮግራሞች ዳይሬክተር ሙሲን ከሊል (ዶ/ር) ናቸው።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በክልሉ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የተጀመሩ ስራዎችን ማጠናከር ይጠበቅባቸዋል- ርእሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)

ሆሳዕና ፤ ነሐሴ 21/2018 (ኢዜአ) ፦ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚጠበቅባቸውን ሚና እንዲወጡ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ...

Aug 28, 2026

በኢሉባቦር ዞን በኩታ ገጠም ከለማው የበቆሎ ሰብል የተሻለ ምርት ለማገኘት የእንክብካቤ ስራ ተጠናክሯል

መቱ፤ ነሐሴ 11/2018 (ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል በኢሉባቦር ዞን በክረምት እርሻ እየለማ ከሚገኘው የበቆሎ ሰብል የላቀ ምርት ለማገኘት የሰብል እንክብካቤና ጥ...

Aug 18, 2026

በሲዳማ ክልል የመንገድና ሌሎች መሰረተ ልማትን በማሻሻል ለሕዝቡ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ ናቸው

ሀዋሳ፤ ነሐሴ 2/2018 (ኢዜአ)፦ በሲዳማ ክልል የመንገድና ሌሎች መሰረተ ልማትን በማሻሻል ለሕዝቡ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ መሆና...

Aug 10, 2026

በክልሉ በበጀት ዓመቱ ውጤታማ የልማት ሥራዎች ተከናውነዋል 

አዳማ፤ ሐምሌ 12/2018 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል በበጀት ዓመቱ ሰላምና መልካም አስተዳደርን ከማረጋገጥ ጎን ለጎን ውጤታማ የልማት ሥራዎች መከናወናቸውን የክል...

Jul 20, 2026