የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ፖለቲካ እና ደህንነት

በደቡብ ወሎ ዞን ከ 46 ሺህ በላይ ለሚሆኑ አርሶ አደሮች የ2ኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ተሰጠ 

Jul 3, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ደሴ ፤ ሰኔ 25/2018 (ኢዜአ):- በደቡብ ወሎ ዞን ከ46 ሺህ በላይ ለሚሆኑ አርሶ አደሮች የ2ኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ካርታ መስጠቱን የዞኑ መሬት መምሪያ አስታወቀ።

በመምሪያው የገጠር መሬት አስተዳደር ቡድን መሪ አቶ ምሳው አክቤ ለኢዜአ እንደገለጹት፣ በዞኑ የሚገኙ አርሶ አደሮችን ዘላቂ የመሬት ባለቤትነት ለማረጋገጥ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት ውጤታማ ናቸው።

ከዚህ ውስጥም በበጀት ዓመቱ ለ46 ሺህ 311 አርሶ አደሮች የ2ኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ካርታ በመስጠት መሬታቸውን በዘላቂነት አልምተው እንዲጠቀሙ ተደርጓል ነው ያሉት።


የይዞታ ካርታው የአርሶ አደሩን ይዞታ በሳይንሳዊ መንገድ በመለካትና ማረጋገጫ በመስጠት የብድርና ሌሎች አገልግሎቶችን ለማግኘት ሰፊ እድል የፈጠረ እንደሆነም አስረድተዋል።

በተጨማሪም አርሶ አደሩ በይዞታው በሚያገኘው የብድር አገልግሎት የግብርና ስራውን ለማዘመን የሚያስችለው ከመሆኑ ባለፈ ሌሎች የገቢ ማስገኛ ስራዎች ላይ እንዲሰማራ የሚያደርግ ነው ብለዋል።

በዚህም በበጀት ዓመቱ ብቻ አራት ሺህ 693 አርሶ አደሮች ከ127 ሚሊዮን ብር በላይ ብድር ተጠቃሚ እንዲሆኑ መደረጉን አስረድተዋል።

በዞኑ ደሴ ዙሪያ ወረዳ የ032 ቀበሌ ነዋሪ አርሶ አደር መሀመድ ሰይድ ፣የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ማግኘቴ መሬቱን በተሻለ መንገድ ለማልማትና ተጨማሪ ሀብት ለማፍራት አስችሎኛል ብለዋል።

ቀደም ሲል የነበረው ይዞታ ትክክለኛ ልኬት ያልነበረው በመሆኑ ከሌላ ባለመብት ጋር የመገፋፋት ሁኔታ ይፈጠር እንደነበር አስታውሰው ፣ አሁን ችግሩ ሙሉ ለሙሉ መፈታቱን ገልጸዋል።

"የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ካርታው ወሰንና ልኬትን በትክክል ያስቀመጠ በመሆኑ የመሬታችንን ዘላቂ ዋስትና ያረጋገጠ ነው" ያሉት ደግሞ የወረኢሉ ወረዳ ነዋሪ አርሶ አደር ጀማል ዋሴ ናቸው።

ይህም ይገባኛል በሚል ይፈጠሩ የነበሩ ግጭቶችንና አለመግባባቶችን በማስቀረቱ ምርታማነታችን ለመጨመር ያግዘናል ነው ያሉት።

በደቡብ ወሎ ዞን ባለፈው በጀት ዓመት ከ61 ሺህ በላይ አርሶ አደሮች የ2ኛ ደረጃ የመሬት ማረጋገጫ ካርታ መስጠት መቻሉን ከመምሪያው የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በክልሉ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የተጀመሩ ስራዎችን ማጠናከር ይጠበቅባቸዋል- ርእሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)

ሆሳዕና ፤ ነሐሴ 21/2018 (ኢዜአ) ፦ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚጠበቅባቸውን ሚና እንዲወጡ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ...

Aug 28, 2026

በኢሉባቦር ዞን በኩታ ገጠም ከለማው የበቆሎ ሰብል የተሻለ ምርት ለማገኘት የእንክብካቤ ስራ ተጠናክሯል

መቱ፤ ነሐሴ 11/2018 (ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል በኢሉባቦር ዞን በክረምት እርሻ እየለማ ከሚገኘው የበቆሎ ሰብል የላቀ ምርት ለማገኘት የሰብል እንክብካቤና ጥ...

Aug 18, 2026

በሲዳማ ክልል የመንገድና ሌሎች መሰረተ ልማትን በማሻሻል ለሕዝቡ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ ናቸው

ሀዋሳ፤ ነሐሴ 2/2018 (ኢዜአ)፦ በሲዳማ ክልል የመንገድና ሌሎች መሰረተ ልማትን በማሻሻል ለሕዝቡ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ መሆና...

Aug 10, 2026

በክልሉ በበጀት ዓመቱ ውጤታማ የልማት ሥራዎች ተከናውነዋል 

አዳማ፤ ሐምሌ 12/2018 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል በበጀት ዓመቱ ሰላምና መልካም አስተዳደርን ከማረጋገጥ ጎን ለጎን ውጤታማ የልማት ሥራዎች መከናወናቸውን የክል...

Jul 20, 2026