የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ፖለቲካ እና ደህንነት

የአየር ማረፊያው ለአገልግሎት መብቃት የአካባቢውን የንግድ፣ የኢንቨስትመንትና የቱሪዝም እንቅስቃሴ በከፍተኛ ሁኔታ የሚያነቃቃ ነው-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

Jul 13, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ ፤ሐምሌ 5 /2018 (ኢዜአ)፦የአየር ማረፊያው ለአገልግሎት መብቃትም የአካባቢውን የንግድ፣የኢንቨስትመንትና የቱሪዝም እንቅስቃሴ በከፍተኛ ሁኔታ በማነቃቃት፣ ለሀገራችን የኢኮኖሚ ዕድገት አዲስ ምዕራፍ እንደሚከፍት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) አስገንዝበዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአዲስ መልክ ተሻሽሎ ደረጃው ከፍ ብሎ የተገነባውን የደብረ ማርቆስ ንጉሥ ተክለ ሃይማኖት አውሮፕላን ማረፊያ ዛሬ በይፋ መርቀዋል።


በ2 ሺህ 400 ሜትር ርዝመትና በ30 ሜትር ስፋት የተገነባው አውሮፕላን ማረፊያው፣ እንደ Q400 እና ቦይንግ 737 ያሉ ግዙፍ የሕዝብና የጭነት አውሮፕላኖችን ማስተናገድ የሚያስችል አቅም አለው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ እንደገለጹት፤ የአውሮፕላን ማረፊያው ተመርቆ ሥራ መጀመሩ የደብረ ማርቆስ ከተማ ነዋሪዎችን የዘመናት ጥያቄ የመለሰ ነው።

የአየር ማረፊያው ለአገልግሎት መብቃትም የአካባቢውን የንግድ፣ የኢንቨስትመንትና የቱሪዝም እንቅስቃሴ በከፍተኛ ሁኔታ በማነቃቃት፣ ለሀገራችን የኢኮኖሚ ዕድገት አዲስ ምዕራፍ እንደሚከፍት አስገንዝበዋል።

የአውሮፕላን ትራንስፖርት መጀመሩ እንዳለ ሆኖ በየብስ ትራንስፖርት የመንቀሳቀስ ጉዳይም በጋራ ጥረት ወደ ተሟላ ሁኔታ መመለስ እንዳለበት ገልጸዋል።


የአየር ትራንስፖርት መጀመሩ በቀን ሦስት ጊዜ በረራ በማድረግ ምቾት የሚፈጥር ቢሆንም፣ የየብስ ትራንስፖርትን መጠቀም ለሚፈልጉ ዜጎች ሰላም በእጅጉ አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል።

መንግሥት ለውይይትና ለንግግር ለሚፈልግ ለማንኛውም አካል በሩ ክፍት መሆኑን በመግለጽ፤ የማያስማሙ ጉዳዮች ካሉ በሰላማዊና በሰለጠነ የፖለቲካ አግባብ መፍታት እንደሚቻል ጥሪ አቅርበዋል።

ልማት በባህሪው ጊዜን፣ትብብርንና ጥበቃን እንደሚፈልግ ያስረዱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ የጎደለውን ልማት፣ብልፅግና፣መተማመንና መከባበር ለመሙላትና ለልጆቻችን የተሻለች ሀገር ለማስረከብ በጋራ መትጋት እንደሚገባ አሳስበዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በኢሉባቦር ዞን በኩታ ገጠም ከለማው የበቆሎ ሰብል የተሻለ ምርት ለማገኘት የእንክብካቤ ስራ ተጠናክሯል

መቱ፤ ነሐሴ 11/2018 (ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል በኢሉባቦር ዞን በክረምት እርሻ እየለማ ከሚገኘው የበቆሎ ሰብል የላቀ ምርት ለማገኘት የሰብል እንክብካቤና ጥ...

Aug 18, 2026

በሲዳማ ክልል የመንገድና ሌሎች መሰረተ ልማትን በማሻሻል ለሕዝቡ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ ናቸው

ሀዋሳ፤ ነሐሴ 2/2018 (ኢዜአ)፦ በሲዳማ ክልል የመንገድና ሌሎች መሰረተ ልማትን በማሻሻል ለሕዝቡ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ መሆና...

Aug 10, 2026

በክልሉ በበጀት ዓመቱ ውጤታማ የልማት ሥራዎች ተከናውነዋል 

አዳማ፤ ሐምሌ 12/2018 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል በበጀት ዓመቱ ሰላምና መልካም አስተዳደርን ከማረጋገጥ ጎን ለጎን ውጤታማ የልማት ሥራዎች መከናወናቸውን የክል...

Jul 20, 2026

የአየር ማረፊያው ለአገልግሎት መብቃት የአካባቢውን የንግድ፣ የኢንቨስትመንትና የቱሪዝም እንቅስቃሴ በከፍተኛ ሁኔታ የሚያነቃቃ ነው-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

አዲስ አበባ ፤ሐምሌ 5 /2018 (ኢዜአ)፦የአየር ማረፊያው ለአገልግሎት መብቃትም የአካባቢውን የንግድ፣የኢንቨስትመንትና የቱሪዝም እንቅስቃሴ በከፍተኛ ሁኔታ በማ...

Jul 13, 2026