የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ፖለቲካ እና ደህንነት

የህዝቡን የልማት ጥያቄዎች የመለሱ ውጤታማ ስራዎች ተከናውነዋል-ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ

Jul 16, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ሀረር ፤ሐምሌ 9/2018 (ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል በበጀት ዓመቱ የህዝቡን የልማት ጥያቄዎች መሰረት በማድረግ ውጤታማ ስራዎች መከናወናቸውን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ አስታወቁ።

ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ የክልሉ ምክር ቤት 6ኛ ዙር 5ኛ ዓመት 10ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ ባቀረቡት ሪፖርት እንዳመለከቱት፥ በክልሉ በበጀት ዓመቱ የተቀመጡ የልማት እቅዶችን ለማሳካት ጥረት ተደርጓል።


በየደረጃው ያለው አመራር፤ ፈፃሚና መላው ህብረተሰብ እቅዱን ለማሳካት ከፍተኛ ተሳትፎና ጥረት ሲያደርግ መቆየቱን አንስተዋል።

በዚህም በኢኮኖሚና ማህበራዊ ዘርፎች ፈጣንና ዘላቂ ልማት ለማምጣት፤ የአገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻልና ለማዘመን እንዲሁም የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት አበረታች ስራዎች መከናወናቸውን አንስተዋል።

በከተማና በገጠና የኮሪደር መሠረተ ልማቶችን የማስፋፋት ተግባራት ዋነኛ የትኩረት አቅጣጫ ሆነው በመከናወናቸው ውጤት መገኘቱን ጠቅሰዋል።

የትምህርት ጥራት፣ተሳትፎና ተደራሽነትን የማጎልበት እንዲሁም የተማሪዎች ውጤት የማሻሻል ስራም ውጤታማ መሆኑን አንስተዋል ።

በክልሉ ዘላቂ ሰላምና ጸጥታ ለማስፈንና የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ እንዲሁም የፍትሕ አገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል በተከናወኑ ተግባራት አመርቂ ውጤት መገኘቱን አመልክተዋል።


ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ ተረጂነትን ለማስቀረት፣ የስራ እድል ፈጠራን ለማጎልበት፣ ክልሉ የሚያመነጨውን ገቢ ከመሰብሰብ፣ በጤናና በሌሎች የተከናወኑ ተግባራት አበረታች መሆናቸውንም ጠቅሰዋል ።

እንዲሁም በክልሉ የሚከናወኑ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ስራዎችም ከጊዜ ወደ ጊዜ ከፍተኛ እድገት ማሳየታቸውን ተናግረዋል።

ለሁለት ተከታታይ ቀናት በሚቆየው የምክር ቤቱ ጉባኤ የተለያዩ ሪፖርቶች፣ እቅዶችና ሹመቶች ይጸድቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በክልሉ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የተጀመሩ ስራዎችን ማጠናከር ይጠበቅባቸዋል- ርእሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)

ሆሳዕና ፤ ነሐሴ 21/2018 (ኢዜአ) ፦ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚጠበቅባቸውን ሚና እንዲወጡ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ...

Aug 28, 2026

በኢሉባቦር ዞን በኩታ ገጠም ከለማው የበቆሎ ሰብል የተሻለ ምርት ለማገኘት የእንክብካቤ ስራ ተጠናክሯል

መቱ፤ ነሐሴ 11/2018 (ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል በኢሉባቦር ዞን በክረምት እርሻ እየለማ ከሚገኘው የበቆሎ ሰብል የላቀ ምርት ለማገኘት የሰብል እንክብካቤና ጥ...

Aug 18, 2026

በሲዳማ ክልል የመንገድና ሌሎች መሰረተ ልማትን በማሻሻል ለሕዝቡ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ ናቸው

ሀዋሳ፤ ነሐሴ 2/2018 (ኢዜአ)፦ በሲዳማ ክልል የመንገድና ሌሎች መሰረተ ልማትን በማሻሻል ለሕዝቡ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ መሆና...

Aug 10, 2026

በክልሉ በበጀት ዓመቱ ውጤታማ የልማት ሥራዎች ተከናውነዋል 

አዳማ፤ ሐምሌ 12/2018 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል በበጀት ዓመቱ ሰላምና መልካም አስተዳደርን ከማረጋገጥ ጎን ለጎን ውጤታማ የልማት ሥራዎች መከናወናቸውን የክል...

Jul 20, 2026