የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ፖለቲካ እና ደህንነት

በምዕራብ ወለጋ ዞን በበጀት ዓመቱ ለ156 ሺህ ሰዎች ሥራ ተፈጥሯል

Jul 16, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ጊምቢ፣ሐምሌ 9/2018 (ኢዜአ)፡- በምዕራብ ወለጋ ዞን በተጠናቀቀው በጀት አመት ለ156 ሺህ ዜጎች የስራ ዕድል መፈጠሩን የዞኑ ሥራ ፈጠራና ክህሎት ጽህፈት ቤት ገለጸ፡፡

የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ደረጀ ጉድና ለኢዜአ እንደገለጹት፤ በበጀት አመቱ ስራ አጥ ወገኖችን በማህበር በማደራጀት ወደ ስራ እንዲገቡ ተደርጓል።


በዞኑ በ2018 በጀት ዓመት ለ108 ሺህ ስራ አጥ ወገኖች የስራ ዕድል ለመፍጠር ታቅዶ አፈፃሙን ከፍ በማድረግ ለ156 ሺህ ዜጎች የስራ ዕድል ታጠቃሚ እንዲሆኑ ተደርጓል ብለዋል፡

በዞኑ የስራ አጥነት ችግር ለማቃለል ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት የተከናወኑ ተግባራት አፈፃፀሙን ለማሳደግ እንዳስቻሉ ነው የተናገሩት።

የስራ ዕድል የተፈጠረላቸው ወገኖች በግብርና፣ በንግድ፣ በማኑፋክቸሪንግ፣ በእንስሳት ልማት፣በውበት ስራ እና በሌሎች ዘርፎች መሰማራታቸውን ነው የገለጹት።

የስራ እድል ለተመቻቸላቸው ዜጎች ከ1 ቢሊዮን ብር ብድር እንዲያገኙ የተደረገ ሲሆን በተሰማሩበት መስክ ዉጤታማ እንዲሆኑም የድጋፍና የክትትል ስራ ሲሰራ ቆይቷል ብለዋል።


ከስራ እድሉ ተጠቃሚዎች መካከል መፊዛ አብዲ ከሌሎች ጓደኞቿ ጋር በመሆን ዝሪያቸው የተሻሻሉ በጎችን በማድለብ ስራ ላይ መሰማራታቸውን ነው የምትናገረው።

በተሰማሩበት መስክ የተሰጣቸው ሥልጠና፣ ድጋፍ አና ክትትልም ውጤታማ እንዲሆኑ የሚያደርግ በመሆኑ የተሻለ ስኬት ለማስመዝገብ እየሰሩ መሆኑን ነው የገለፀችው።


በማኅበር ተደራጅተው የመሥሪያ ቦታና የብድር አገልግሎት ተጠቃሚ በመሆን በዶሮ እርባታ ስራ ላይ መሰማራታቸውን የገለፀው ወጣት እዮብ ቶለሳ በዘርፉ ውጤታማ ስራዎችን እየሰራን ነው ብሏል።

በተለይም ከቅርብ አመታት ወዲህ በመንግስት ተቀርጾ ተግባራዊ እየተደረጉ ያሉ የልማት ኢንሼቲቮች ወጣቱ የስራ ዕድል ተጠቃሚ እያደረገ መሆኑን አመልክቷል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በክልሉ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የተጀመሩ ስራዎችን ማጠናከር ይጠበቅባቸዋል- ርእሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)

ሆሳዕና ፤ ነሐሴ 21/2018 (ኢዜአ) ፦ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚጠበቅባቸውን ሚና እንዲወጡ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ...

Aug 28, 2026

በኢሉባቦር ዞን በኩታ ገጠም ከለማው የበቆሎ ሰብል የተሻለ ምርት ለማገኘት የእንክብካቤ ስራ ተጠናክሯል

መቱ፤ ነሐሴ 11/2018 (ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል በኢሉባቦር ዞን በክረምት እርሻ እየለማ ከሚገኘው የበቆሎ ሰብል የላቀ ምርት ለማገኘት የሰብል እንክብካቤና ጥ...

Aug 18, 2026

በሲዳማ ክልል የመንገድና ሌሎች መሰረተ ልማትን በማሻሻል ለሕዝቡ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ ናቸው

ሀዋሳ፤ ነሐሴ 2/2018 (ኢዜአ)፦ በሲዳማ ክልል የመንገድና ሌሎች መሰረተ ልማትን በማሻሻል ለሕዝቡ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ መሆና...

Aug 10, 2026

በክልሉ በበጀት ዓመቱ ውጤታማ የልማት ሥራዎች ተከናውነዋል 

አዳማ፤ ሐምሌ 12/2018 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል በበጀት ዓመቱ ሰላምና መልካም አስተዳደርን ከማረጋገጥ ጎን ለጎን ውጤታማ የልማት ሥራዎች መከናወናቸውን የክል...

Jul 20, 2026